ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሕይወት ውስጥ ጨለማ አለ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን ግን ያንን ጨለማ የማጥፋት ኃይል አለው አሉ።

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት የገና በዓል ከተከበረ እነሆ ሁለተኛ ሳምንት ላይ የምንገኝ ሲሆን በታኅሳስ 28/2013 ዓ.ም ሰባሰገል ሕጻኑ ኢየሱስ የተወለደበትን ሥፍራ ለማየት እና ለሕጻኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመስገድ ስጦታዎችን ይዘው በኮከብ መሪነት ሕጻኑ ኢየሱስ ወዳለበት ሥፍራ የሂደቡት እለት ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል። በእለቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱ ጴጥሮስ ባዚሊካ መስዋዕተ ቅዳሴ ያሳረጉ ሲሆን በእለቱ ያሳረጉትን መስዋዕተ ቅዳሴ ካጠናቀቁ በኋላ እኩለ ቀን ላይ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ገብርኤል ጽሎት ከደገሙ በኋላ ባዳርጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት በሕይወት ውስጥ የጨለማ ጊዜ አለ፣ የእግዚአብሔር ብርሃን ግን የበለጠ ብርሃን አለው ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ሐዋርያዊ መቀመጫቸው ከሚገኝበት ከቫቲካን ሆነው ቅዱስነታቸው ባደረጉት አስተንትኖ ወደ ዓለማችን በመጣው ታላቅ ብርሃን ላይ አስተንትኖ አድርገዋል። ኢየሱስ ለሰባሰገል የተገለጸበት እለት የሚከበረው በዓል የገናን ተመሳሳይ ምስጢር ማለትም የክርስቶስ ልደት በድጋሚ የሚያብራራ እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን ቤተክርስቲያን የብርሃን እይታ እና የጌታ መገለጥ ለሁሉም ህዝቦች ታከብራለች ብለዋል። ያ ብርሃን አሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በወንጌል አዋጅ በምስክርነት አማካኝነት በፍቅር እና በእምነት ብርሃን ለሌሎች መመስከር ይገባል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስ በኢሳይያስ ራእይ (60: 1-6) ላይ በማሰላሰል ነቢዩ በዘመኑ ስለሰጠው መግለጫ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ጠቃሚ ነው ያሉ ሲሆን “ምድርን የሸፈነው ጨለማ ፣ በሕዝቦች ላይ ያንዣበበው ጨለማ” በታላቅ ብርሃን ድል እንደ ሚደረግ የሚገልጽ ምልክት ነው ብለዋል።

ነቢዩ ኢሳይያስ በእንደዚህ ዓይነት ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ “እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም የሰጠውና በሕዝቦች ሁሉ ጎዳና ላይ የሚያበራ” ብርሃን እንደሚመጣ ማሳወቁን አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ ማራኪ ራዕይ ተስፋን እንደሚጋብዝ ተናግረዋል ፣ እናም የእግዚአብሔር ብርሃን ሁሉንም ጨለማ ድል እንደ ሚያደርግ ያስታውሰናል ብለዋል።

በአድማስ ላይ የሚታየው ኮከብ

ሰባሰገል ኢየሱስን ማምለካቸውን በተመለከተ ወንጌላዊው ማቴዎስ እንደተናገረው  (ማቴ 2 1-12) በኢሳያስ የተተነበየው ብርሃን የቤተልሔም ሕፃን እንደ ሆነ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የጠቆሙ ሲሆን ምንም እንኳን ሁሉም ሰው ንጉሥነቱን ባይቀበልም ኢየሱስ ወደ አለም የመጣ ብርሃን ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት “በአድማስ ላይ የተገለጠው ኮከብ ፣ እርሱ እግዚአብሔር የፍቅሩን ፣ የፍትህንና የሰላሙን መንግሥት የሚከፍተው በእርሱ የሚጠበቅ መሲሕ ነው” ያሉ ሲሆን እሱ የተወለደው ለአንዳንዶች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ወንዶችና ሴቶች ፣ ለሁሉም ሕዝቦች ነው ብለዋል።

በእኛ በኩል የሚያበራ

ነገር ግን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የክርስቶስ ብርሃን በሁሉም ቦታ እና በሁሉም ሰው ላይ እንዴት ሊበራ ይችላል? በማለት ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ይህም እውን ሊሆን የሚችለው “በወንጌሉ አዋጅ” ነው ብለዋል። አክለውም ሲገልጹ እግዚአብሔር  ወደእኛ ለመምጣት ይህንን ተመሳሳይ “ዘዴ” ተጠቅሟል ያሉት ቅዱስነታቸው እርሱ ሥጋ ለብሶ ሰው በመሆኑ  እግዚአብሔር ወደ እኛ እንዴት እንደ ቀረበ የሚያሳይ እንደ ሆነ ገልጸው በተመሳሳይ መልኩም እኛም ለሌሎች ቅርብ መሆን ይኖርብናል ብለዋል።

“ኮከቡ ክርስቶስ ነው” እኛ ደግሞ ቤዛችን የሆነው ኢየሱስ ለሁሉም ሰው በነፃ ስለሚያቀርበው የመልካምነት እና ማለቂያ የሌለው የምህረት ሀብቶች ምስክሮች እንደመሆናችን መጠን እኛም ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ኮከብ መሆን እንችላለን እንድህም መሆን አለብን” ብለዋል።

በክርስቶስ መመራት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ክርስቲያን የክርስቶስን ብርሃን እንዲቀበል እና እራሳችንን እንደ ሰባሰገል ለመምራት እና በክርስቶስ ለመለወጥ እንድንፈቅድ ሁሉንም ሰው ያሳሰቡ ሲሆን ይህ የእምነት ጉዞ ነው ፣ በጸሎት እና የእግዚአብሔርን ሥራዎች ማሰላሰል ፣ ይህም ያለማቋረጥ በእያንዳንዱ አዲስ ደስታ እና አስደናቂ ነገር እኛን ይሞላል" ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው አስተንትኖዋቸውን አጠናቀዋል።

07 January 2021, 12:22