ፈልግ

በእንዶኔዢያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የነብስ አድን ፍለጋ በእንዶኔዢያ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የነብስ አድን ፍለጋ  

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮስ በኢንዶኔዥያ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎድ ሰዎች ጸሎት ቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 09/2013 ዓ.ም በቫቲካን በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያም ያበሰረበትን “የብስራተ ገብርኤል” ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በቅርቡ በኢንዶኔዥያ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎድ እና እንዲሁም በአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት ማቅረባቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኢንዶኔዥያ ሱላዌሲ ግዛት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ሰዎች እንዲሁም ባለፈው ሳምንት በኢንዶኔዥያ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ ሰለባዎች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሀሳባቸውን ወደ “በኢንዶኔዥያ ወደ ምትገኘው ሲልሉዌይ ደሴት ህዝቦች በማደረግ በከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ህዝቦች” ጸሎት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን “ለሟቾች፣ ለቆሰሉት እና በአደጋው ምክንያት ስራ ላጡ ሁሉ እፀልያለሁ” ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት “ጌታ እንዲያጽናናቸው እና እነሱን ለማገዝ የሚሞክሩትን ሁሉ እዲያበረታቸው ጸልያለሁ” ብለዋል። የመሬት መንቀጥቀጡ  የተከሰተው በጥር 7/2013 ዓ.ም ሲሆን የተከሰተውም በኢንዶኔዥያ ውስጥ በምዕራብ ሱላዋይሲ ግዛት ነው፣ ርዕደ መሬቱ  በመሬት መንቀጥቀት መለኪያ መሳሪያ ሬክቴር ስኬል ሲለካ 6.2  በሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ ግዛቲቱ መመታቷ ተገልጿል።  የኢንዶኔዥያ የአደጋ መከላከል ማሕበር አደጋውን በተመለከተ ባወጣው ዘገባ ቢያንስ 46 ሰዎች በአደጋው መሞታቸውን የተገለጸ ሲሆን 826 ሰዎች መቁሰላቸውን ሪፖርት አድርጓል ፤ ቁጥራቸው አሁንም ድረስ ግልፅ ባለመሆኑ በርካታ ሰዎች ጠፍተዋል ተብሏል። አርብ ዕለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመሬት መንቀጥቀጡ ለተጎዱ የሀዘን ቴሌግራም መላካቸው ይታወሳል። በውስጡም “በዚህ የተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱት ሁሉ ልባዊ አጋርነታቸውን ገልፀው“ ለሟቾች የዘላለም ሕይወት፣ የተጎዱ ሰዎች እንዲድኑ እና ያዘኑ ሁሉ መጽናናትን እንዲያገኙ ”እየጸልያለሁ ብለዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው ሳምንት በኢንዶኔዥያ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ሰለባዎችም የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው በእዚህ አደጋ 62 ሰዎችን የያዘ ቦይንግ 737-500 አውሮፕላን ከጃካርታ ዋናው አውሮፕላን ማረፊያ ከተነሳ ከደቂቃዎች በኋላ ቅዳሜ  ጥር 8/2013 ዓ.ም ጃቫ ባህር ላይ መከስከሱ ይታወሳል፣ ቅዱስነታቸው በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ጸሎት አድርገዋል።

17 January 2021, 13:41