ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ እ.አ.አ በ 2016 ዓ.ም በፖላንድ አገር የሚገኘውን አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው የናዚ የማጎሪያ ካፕ በጎበኙበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ እ.አ.አ በ 2016 ዓ.ም በፖላንድ አገር የሚገኘውን አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው የናዚ የማጎሪያ ካፕ በጎበኙበት ወቅት 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙትን ዘግናኝ ተግባራት ማስታወስ ሰብዓዊነት ነው አሉ!

በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው በመባል በሚታወቀው ስፍራ ላይ በጀርመን ናዚ በተገነባው እና ከመላው አውሮፓ የተሰበሰቡ አይሁዳዊያን የታጎሩበት፣ የተጨፈጨፉበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 76ኛው አመት በጥር 20/2013 ዓ.ም በመላው ዓለም ተዘክሮ ማለፉ ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥር 20/201ዓ ዓ.ም በቫቲካን ይህ ቀን በተዘከረበት ወቅት ይህንን የጭፍጨፋ ቀን መዘከር ሰብዓዊ የሆነ ተግባር እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን የእዚህ ዓይነቱ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተሰምቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ግድያ ማስታወስ በወቅቱ የተከናወነው ዘግናኝ የሆነ ተግባር እንዳይደገም እንደ እንደ ሚረዳ አክለው ገልጸዋል። 

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርው በመባል በሚታወቀው ስፍራ ላይ በጀርመን ናዚ በተገነባው እና ከመላው አውሮፓ የተሰበሰቡ አይሁዳዊያን የታጎሩበት፣ የተጨፈጨፉበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 76ኛው አመት እየተዘከረ እንደ ሚገኝ ቅዱስነታቸው ማናገራቸው የተገለጸ ሲሆን በእዚህ አስከፊ በሆነ ሁኔታ ሕይወታቸውን ላጡ፣ በሁኔታው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጎጂ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ማቀረባቸው የተገለጸ ሲሆን በክርስቶስ ቃል እንድንታመን፣ ራሳችንን ለአብ ምሕረት እንድንከፍት እና በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በመታገዝ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እንደ ሚገባ ገልጸው በዓለማችን ዙሪያ እንዲህ ያሉ አሰቃቂ የሚባሉ ድርጊቶች ተመልሰው እንዳይፈጠሩ በትጋት መሥራት እና መጸለይ ይገባል ብለዋል።

በሰው ልጆች ላይ የተፈጸሙትን ዘግናኝ ነገሮች ማስታወስ ድርጊቱ ዳግም እንዳይከሰት ያደርጋል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ ዕለት ጥር 20/2013 ዓ.ም ካደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል የጀርመን ናዚ አይሁዳዊያን በማጎሪያ ካፖች ውስጥ ያጎረበት፣ የጨፈጨፈበት፣ የተወሰኑት ደግሞ ነጻ የወጡበት 76ኛው አመት እየተዘከረ እንደ ሚገኝ የገለጹ ሲሆን “ዛሬ በጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባዎች እና በናዚ አገዛዝ ለተሰደዱት እና የተገደሉ ሰዎችን ሁሉ እንዘክራለን” ብለዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት የሶቪዬት ቀይ ለበሽ ጦር ትልቁ የሆነውን የናዚ ማጎሪያ እና የሞት ካምፕ - ኦሽዊ ቪዚ-ቢንከርው - ነፃ ያወጣበት ቀን በተመለከተ ይህ ዘግናኝ የሆነ ድርጊት የተፈጸመበት እለት በአመቱ የሚዘከርበት ዓለም አቀፍ የመታሰቢያ ቀን እንደ ሆነ ይታወቃል።

መጻይ ጊዜ የተሻለ እንዲሆን የሚያደረግ መታሰቢያ ነው!

ይህንን ዘግናኝ የሆነ ጊዜ ማስታወሱ የሰው ልጅ መገለጫ ነው። ማስታወሱ የሥልጣኔ ምልክት ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተናግረዋል። ሁኔታውን ማስታወሱ ለተሻለ የወደፊት ሰላምና ወንድማማችነት ቅድመ ሁኔታ ነው በማለት እክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመቀጠል “ማስታወስ ማለት እነዚህ ነገሮች እንደገና አንዳይከሰቱ ማደረግ ማለት ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም አንድን ህዝብ ለማዳን ከታሰቡ የርዕዮተ-ዓለም ሀሳቦች ጀምሮ አንድን ህዝብ እና ሰብአዊነትን ማጥፋት ተገቢ የሆነ ነገር እንዳልሆነ የምንረዳበትን አጋጣሚ ስለሚከፍትልን ነው” ብለዋል። “ይህ የሞት ፣ የመጥፋትና የጭካኔ መንገድ እንዴት እንደሚጀመር በትኩረት መከታተል አለብን” በማለት አስጠንቅቀዋል።

የርዕሰ ሊቀ ጳጳሱ ቃል ባለፈው ዓመት የመታሰቢያ ቀን በተዘከረበት ወቅት ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ይህንን ሐሳብ ያስተጋቡ ሲሆን “ለልባችን ይህ ተግባር ‘በጭራሽ! መደገም የለበትም ብለን በመናገር” አንድ ጊዜ የጸሎት እና የመታሰቢያ ጊዜ ወስደን ቀኑ እንዲዘከር ጥሪ ማቅረባቸው” የሚታወስ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስለ እልቂቱ መታሰቢያ  “በዚህ እጅግ አሳዛኝ ገጠመኝ ወቅት ግድየለሽነት ተቀባይነት የለውም፣ እናም ይህንን ዘግናኝ የሆነ ተግባር የማስታወስ ችሎታ ሊኖረን የገባል” ማለታቸው ይታወሳል።

እ.አ.አ በ 2016 ወደ በፖላንድ አገር አውሽ ቪዚ ቢንኬርናው የተደረገው ጎብኝ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.አ.አ. በ 2016 ዓ.ም ወደ ፖላንድ ባደረጉት ጉብኝት በታዋቂው የናዚ የሞት ካምፕ ተገኝተው የአውሽ ቪዚ-ቢርኬናው መታሰቢያ እና ሙዚየም ጎብኝተው እንደ ነበረ የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ 2016 ዓ.ም ከእዚህ ቀደም የነበሩ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በቅደም ተከተል ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና ቤኔዲክቶስ 16ኛ በመቀጠል ቦታውን የጎበኙ ሦስተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ናቸው።

በወቅቱ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጉብኝት በማጎሪያ ካፕ በር በኩል ወደ ውስጥ በመግባት የጀመረ ሲሆን በዝምታ “ሥራችሁ ነፃ ያወጣችኋል ”በሚል መሪ ቃል ጥልቅ የሆነ የጸጥታ አስተንትኖ ማደረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ የዛሬ 76 ዓመት ገደማ በካምፑ ውስጥ ለሚኖሩ አብረውት ለታሰሩ እስረኞች ሕይወቱን አሳልፎ በሰጠው በቅዱስ ማክሲሚልያን ኮልቤ የታሰረበት ክፍል ውስጥ ገብተው በዝምታ ቅዱስነታቸው የጸለዩ ሲሆን ከእዚያን በኋላ ደግሞ ከእዚህ ዘግናኝ እና ሰቃቂ ጥቃት በተአምር ከተረፉ ሰዎች ጋር ቅዱስነታቸው ተገናኝተው እንደ ነበረ መዘገባችን ይታወሳል።

28 January 2021, 10:00