ፈልግ

በናይጄሪያ በጭካኔ በተሞላ ጥቃት ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ ብዙዎቹ ጠፍተዋል። በናይጄሪያ በጭካኔ በተሞላ ጥቃት ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ ብዙዎቹ ጠፍተዋል። 

በናይጄሪያ በጭካኔ በተሞላ ጥቃት ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ ብዙዎቹ ጠፍተዋል።

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ውስጥ በሩዝ ማምረቻ እርሻዎች ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ ሰዎች ባልታወቁ ሰዎች መገደላቸው የተገለጸ ሲሆን በዚህ አሰቃቂ ጥቃት ሰለባ የነበሩ ሰዎች የቀብር ሥነ ሥርዓቶች መከናወኑም ተገልጿል። ጥቃቱን የፈጸመው ቡድን አስካሁን በይፋ ያልታወቀ ሲሆን ነገር ግን የአገሪቷ ባለስልጣናት ይህንን ጥቃት የፈጸመው ቡድን ላለፉት 10 አመታት በላይ ክልሉን ሲያሸብሩ የነበሩ እና የቦታውን የተወሰነ ክፍል የሚቆጣጠሩ የቦኮ ሃራም ታጣቂዎች ጥቃቱን መፈጸማቸውን አክለው ገልጸዋል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የመንደሩ ነዋሪዎች እሁድ ዕለት ሕዳር 20/2013 ዓ.ም በእዚህ አክራሪ የእስልምና እምነት ተከታይ አሸባሪ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት የተገደሉን 43 የእርሻ ሰራተኞችን የቀበሩ ሲሆን የፀጥታ ኃይሎች ደግሞ እስካሁን ድረስ ደብዛቸው የጠፋ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን ፍለጋ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።

ቅዳሜ እለት ጠዋት ላይ በሞተር ሳይክል ተጭነው የመጡ በርካታ ታጣቂዎች ዛባርማሪ በመባል በሚታወቀው መንደር ውስጥ በእርሻ ሥራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሰራተኞ መካከል 30 የሚሆኑትን በቢላ አንገታቸውን በመቅላት እና ሌሎቹን ደግሞ በመሳሪያ የገደሏቸው መሆኑን እና የተወሰኑትን ደግሞ አፍነው መውሰዳቸውን የአይን እማኞች ገልፀዋል። ነዋሪዎቹ እንዳሉት ቢያንስ 70 ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል፣ ከተገደሉት መካከል ደግሞ 10 ሴቶች ይገኙበታል።

በጅምላ በተፈጸመው የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ወቅት የተናገሩት የቦርኖ ግዛት ርዕሰ መስተዳድር ባባጋና ዙሎም የፌዴራል መንግሥት ለነዋሪዎች የበለጠ ጥበቃ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። በአከባቢው የሚገኙ ሕዝቦች በቤታቸው ውስጥ ሁነው ቢቀመጡ በረሃብ የመሞት አደጋ የሚያጋጥማቸው ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ነብሳቸውን ከእራብ አደጋ ለመታደግ ወደ እርሻ ቦታ በሚሄዱበት ወቅት ደግሞ ይህንን የመሰለ በአሸባሪዎች የመገደል አደጋ እንደ ሚያጋጥማቸው የቦርኖ ግዛት ርዕሰ መስተዳድር ባባጋና ዙሎም አክለው ገልጸዋል።

በናይጄሪያ የምግብ ዋጋ ባለፈው ዓመት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ፣ በጎርፍ ፣ በድንበር መዘጋት እና በአንዳንድ የምግብ አምራች አካባቢዎች የፀጥታ ችግር ምክንያት የአገሪቷ ሕዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ለችግር መጋለጡም ይታወቃል።

ቦኮ ሀራም

ለጥቃቱ በይፋ ኃላፊነት የወሰደ ወገን ባይኖርም ቅሉ እንደዚህ ዓይነት እልቂቶች ከዚህ ቀደም በቦኮ ሃራም ወይም በአክራሪ በእስላማዊው ቡድን አማካይነት የምዕራብ አፍሪቃ ግዛት ውስጥ በተደጋጋሚ መፈጸሙ የሚታወቅ ሲሆን ባለፉት አስር ዓመታት ውስጥ አክራሪው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ቢያንስ 30,000 ሰዎችን በገደሉበት አካባቢ ውስጥ ይህ የቦኩ ሃራም አክራሪ ቡድን በሰፊው በሥፍራው እንደ ሚንቀሳቀስ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ አሸባሪ ቡድን በተቃጣው አደጋ ከ2.5 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ይታወሳል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚህ ሳምንት መጨረሻ በቦርኖ ግዛት በጄሬ አካባቢያዊ መንግስት ውስጥ ቢያንስ 110 ሰዎች መገደላቸውን ገምቷል።

የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ ግድያውን በከፍተኛ ሁኔታ በማውገዝ  “መላው አገሪቱ ተጎዳች” ብለው መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን ዘንድሮ በሰላማዊ ዜጎች ላይ “ለደረሰው እጅግ የከፋ ቀጥተኛ ጥቃት የሚያበሳጭ እና አስደንጋጭ” መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ አስተባባሪ ማስጠንቀቂያቸውን ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ በናይጄሪያ በአሸባሪዎች በተቃጣው ጥቃት ምክንያት ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች ጸሎት ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን እንደ እዚህ ያሉ አሰቃቂ የሽብር ጥቃቶች ይቆሙ ዘንድ አለም አቀፉ ማሕበረሰብ የበኩሉን አስተዋጾ እንዲያደርግ ቅዱስነታቸው ጥሪ አቅርበዋል።

02 December 2020, 13:40