ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የገና በዓል ያለምንም ማጉረምረም ሌሎችን የመርዳት ዕድል የሰጠናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሳስ 11/2013 ዓ.ም ያደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ በሉቃስ ወንጌል (1፡26-38) ላይ በተጠቀሰው መልአኩ ገብርኤል ማርያምን ያበሰረበት የኢየሱስ መወለድ አስቀድሞ በተነገረበት የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የገና በዓል ያለምንም ማጉረምረም ሌሎችን የመርዳት ዕድል የሰጠናል ማለታቸው ተገልጿል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

በዚህ በአራተኛው እና በመጨረሻው የስብከተ ገና ሳምንት ሰንበት እለት (የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ማለት ነው) ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል የኢየሱስ መወለድ አስቀድሞ የተነገረበትን ሁኔታ እንደገና ያስታውሰናል። መልአኩ ማርያምን “ደስ ይበልሽ” ካላት በኋላ “እነሆ፤ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ”  (ሉቃ 1፡28, 31) በማለት ያናገራታል። ድንግል ማርያም ደስ እንዲላት የታሰበ የንጹህ ደስታ ብስራት ይመስላል። በዚያን ጊዜ ከነበሩት ሴቶች መካከል የመሲሑ እናት የመሆን ሕልም ያልነበራት የትኛው ሴት ናት? ነገር ግን እነዚህ ቃላት ከደስታ ጋር ማርያም ታላቅ ፈተና እንደ ሚገጥማት ይተነብያሉ። እንዴት? ምክንያቱም በዚያ ቅጽበት እሷ “ታጭታ ነበር” (ሉቃስ 1፡ 27)፣ አላገባችም ነበር፣ ነገር ግን ለዮሴፍ ታጨችታ ነበር። በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ የታጨ ሰዎች የሙሴ ሕግ እንደ ሚለው በዝምድና መልክ ወይም አብሮ መኖር እንደሌለበት ደንግጓል። ስለሆነም ወንድ ልጅ በመውለዷ ማርያም ህጉን ትተላለፍ ነበር፣ እናም በሴቶች ላይ የሚደርሰው ቅጣት አሰቃቂ ነበር (ዘዳግም 22፡20-21)። በእርግጠኝነት መለኮታዊው መልእክት የማርያምን ልብ በብርሃን እና በብርታት ይሞላት ነበር። ሆኖም እራሷን ወሳኝ የሆነ ውሳኔ የማደረግ አጋጣሚ ገጥሟት ነበር - ለእግዚአብሔር “እነሆኝ” ለማለት ፣ ሁሉንም ነገር ፣ ሕይወቷን እንኳን አደጋ ላይ በመጣል ፣ ወይም ግብዣውን ላለመቀበል እና ተራ ህይወቷን ለመቀጠል በእነዚህ ጭንቀቶች ውስጥ ገብታ ነበር።

ታዲያ ምን አደረገች? እሷም “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” (ሉቃ 1 38)  በማለት ትመልሳለች። ነገር ግን ቅዱስ ወንጌል በተጻፈበት ቋንቋ በቀላሉ “ይሁን” ማለት አይደለም። አገላለፁ ጠንካራ ፍላጎትን ያሳያል ፣ የሆነ ነገር እንዲከሰት ፍላጎቱን ያሳያል። በሌላ አገላለጽ ማርያም “መከሰት ካለበት ይከሰት ... አለበለዚያ መሆን ካልቻለ ደግሞ…” በማለት አልመለሰችም። በምፍጹም እንዲህ አላለችም። እሷ ደካማ እና ታዛዥነትን ቀለል አድርጋ መቀበሏን አይገልጽም ፣ ይልቁንም ጠንካራ የሆነ ፍላጎት እንዳላት ትገልጻለች። እሷ አላቅማማችም፣ ነገር ግን በንቃት ትቀበላለች። እራሷን ከእግዚአብሄር ጋር ታስተሳስራላች። ጌታዋን ሙሉ በሙሉ እና ወዲያውኑ ለማገልገል ተዘጋጅታ በፍቅር ላይ ያለች ሴት ናት። እሷ ስለእሱ ለማሰብ ትንሽ ጊዜ ወይም ምናልባትም ስለሚሆነው ነገር ተጨማሪ ማብራሪያዎችን መጠየቅ ትችል ነበር። ምናልባት አንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎችን ማዘጋጀት ትችል ነበር ... ይልቁኑ ጊዜ አልወሰደችም ፣ እግዚአብሔር እንዲጠብቅ አላደረግችውም፣ እንዲዘገይ አልፈለገችም ወዲያውኑ እሺ አለች።

ምን ያህል ጊዜ - አሁን ስለራሳችን እናስብ - ህይወታችን ስንት ጊዜ ነው ጊዜያትን በማራዘም በመንፈሳዊ ሕይወትም ጭምር ማለት ነው የተገነባው! ለምሳሌ መጸለይ ለኔ ጥሩ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ነገር ግን ዛሬ “ነገ ፣ ከነገ ወዲያ” በማለቴት ዛሬ… ነገ ጊዜ የለኝም፣ ነገሮችን ለሌላ ጊዜ አስተላልፈናል-ነገ አደርገዋለሁ እያለን ራሳችንን የምናታልለው ስንት ጊዜ ነው? አንድን ሰው መርዳት አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁ ፣ አዎ እኔ ማድረግ አለብኝ ነገ አደርገዋለሁ በማለት ጉዳዩን እናሸጋግረዋለን። ዛሬ የገናን በዓለ ለማክበር በምንዘጋጅበት ወቅት ማርያም ነገሮችን ለሌላ ጊዜ እንዳናስተላልፍ እና “እነሆኝ” እንድንል ተጋብዘናለች። “መጸለይ አለብኝ!” “አዎ ፣ እሻለሁ እናም እጸልያለሁ”። ሌሎችን መርዳት አለብኝ? አዎ"። እንዴት ላድርገው? አሁኑኑ ሳልዘገይ ማድረግ አለብኝ። እያንዳንዱ “እነሆኝ” አንድ ነገር ያስከፍላል ፣ እያንዳንዱ “እነሆኝ” የራሱ ዋጋ አለው ፣ ነገር ግን ሁልጊዜ ያ ደፋር እና ፈጣን “እነሆኝ” ከአስከፈላት ዋጋ ባሻገር “እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” በማለቷ ለእኛ መዳንን አስገኝቶልናል።

ታዲያ እኛ “እነሆኝ” የምንለው ምንድነው? በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት የበሽታው ወረርሽኝ ምንም ነገር እንዳናከናውን በሚያደርገን ወቅት ከማጉረምረም ይልቅ ለተቸገረ አንድ ሰው አንድ ነገር እናድርግ፣ ለራሳችን እና ለጓደኞቻችን እጥፍ ድርብ የሆነ ስጦታ ማደረግ ሳይሆን የተቸገረ አንድ ሰው እንርዳ። ሌላ አንድ ተጨማሪ ምክር ደግሞ ኢየሱስ በእኛ ውስጥ እንዲወለድ ፣ ልባችንን እናዘጋጅለት፣ ወደ ፀሎት እንሂድ ፣ እራሳችንን በሸማችነት መጠመድ አንፍቀድ። “አህ ስጦታዎችን መግዛት አለብኝ ፣ ይህንን እና ያንን ማድረግ አለብኝ” አንበል። ነገሮችን የማድረግ እና በብዛት የመሸመት እብደት የበለጠ እና የበለጠ ተጋላጭ እንድንሆን ያደርገናል። አስፈላጊ የሆነው ኢየሱስ ብቻ ነው። ሸማቾች በቤተልሔም በግርግም ውስጥ አይገኙም-እውነታው የሚያሳየን በእዚያ የሚገኙት ድሆች እና ፍቅር ብቻ ነው። እንደ ማሪያም እንዲሆን ልባችንን እናዘጋጅ ፣ ከክፉ ነገር ነፃ የወጣን እግዚአብሔርን ለመቀበል ዝግጁ የሆንን ሰዎች እንሁን።

“እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” የሚለው ቃል  ይህ የስብከተ ገና የመጨረሻ እሁድ (የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር ደንብ መሰረት ማለት ነው) የድንግል ማርያም የመጨረሻ ቃል ነው ፣ እናም ወደ ገና በዓል እውነተኛ እርምጃ ለመውሰድ የቀረበልን ግብዣ ነው። ምክንያቱም የኢየሱስ ልደት ሕይወታችንን የማይነካ ከሆነ - የእኔ ፣ ያንተ ፣ ያንቺ ፣  የእኛ ፣ የሁላችን - ሕይወታችንን የማይነካ ከሆነ በከንቱ ያልፋል ማለት ነው። አሁን በምንጸልየው የብስራተ ገብርኤል ጸሎት እኛም “ቃልህ በእኔ ይፈጸም” በማለት እንጸልያለን፣ እራሳችንን ለገና በዓል በደንብ ለመዘጋጀት ወደነዚህ የመጨረሻ ቀናት በምንመጣበት አቀራረብ  እመቤታችን በሕይወታችን እንድንናገር እንድትረዳን አማለጅነቷን ልንማጸናት ይገባል።

20 December 2020, 11:37