ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 08/2013 ዓ.ም 84ኛ አመት ልደታቸውን አከበሩ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 08/2013 ዓ.ም 84ኛ አመት ልደታቸውን ማክበራቸው ተገለጸ። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በታኅሳስ 17/1936 ዓ.ም የአርጄንቲና ዋና ከተማ በሆነችው በቦይነስ አይረስ መወለዳቸውን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን በማገልገል ላይ እንደ ሚገኙ ይታወቃል።

የእዚህ ዘገባ አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1969 ዓ.ም ማዕረገ ክህነት እንደ ተቀበሉ ከታሪካቸው ለመረዳት የተቻለ ሲሆን አሁንም እ.አ.አ በ1973 ዓ.ም በአርጄንቲና የኢየሱሳዊያን ማኅበር አለቃ በመሆን መመረጣቸው ይታወሳል። እ.አ.አ በ1992 ዓ.ም የጵጵስና ማዕረግ መቀበላቸው የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ 1998 ዓ.ም የቦነስ አይረስ ሊቀ ጳጳስ በመሆን መሾማቸው ይታወሳል። እ.አ.አ በ2001 ዓ.ም በወቅቱ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከነበሩት ከዮሐንስ ሁለተኛ እጅ የካርዲናልነትን ማዕረግ መቀበላቸው የሚታወስ ሲሆን እ.አ.አ በመጋቢት 13/2013 ዓ.ም ደግም 266ኛው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመሆን መሾማቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በመጋቢት 04/2013 ዓ.ም. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተመረጡበትን 7ኛውን ዓመት እንደ ሚያከብሩ ይታወቃል። ቅዱስነታቸው በእነዚህ ሰባት ዓመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በተለየ ሁኔታ ቤተ ክርስቲያን ሚስዮናዊ የሆነ ተግባሯን አጠናክራ እንድትቀጥል እና ለሁሉም የሰው ልጆች በቅዱስ ወንጌል የሚገኘውን ደስታ እንድትመሰክር፣ በማንኛውም የቅዱስ ወንጌል የማብሰር ሂደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ በቀጥታ ተሳታፊ ይሆን ዘንድ በመፍቀድ ማከናውን እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አበክረው መናገራቸው እና አሁንም ቤተ ክርስቲያን በእዚሁ መንገድ እንድትቀጥል ማሳሰባቸውን በፍጹም አላቋረጡም።

ቅዱስነታቸው በእነዚህ ሰባት ዓመታት ውስጥ በላቲን ቋንቋ Lumen fidei  በአማሪኛው “የእመንት ብርሃን” የተሰኘ እና በእምነት ዙሪያ ላይ ያጠነጠን ጳጳሳዊ መልእክት እና Laudato si በአማሪኛው “ውዳሴ ለአንተ ይሁን”” በሚል አርእስት የጋራ የመኖሪያ ቤታችንን ስለ መንከባከብ (የአይር ንብረት ለውጥ) በማስመልከት የጻፉት ደግሞ ሁለተኛው ጳጳሳዊ መልእክት ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በእነዚህ ሰባት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ሶስት ጳጳሳዊ መልእክቶችን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን እነዚህም Evangelii gaudium  በአማሪኛ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ” የሚለው በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በእዚህም ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ መሆን እንዳለባት እና ቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊ ተልዕኮዋን ለማከናውን እና ሰዎችን ወደ እግዚኣብሔር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መሄድ እንዳለባት የሚያሳስብ ቃለ ምዕዳን ሲሆን በሁለተኛነት ደግሞ amoris laetitia በአማሪኛው “የፍቅር ሐሴት” በሚል አርእስት ይፋ ያደረጉት ጳጳሳዊ መልእክት በቤተሰብ ውስጥ ሊኖር ስለሚገባው ፍቅር፣ በቤተሰብ ውስጥ ስለሚታዩ ተግዳሮቶች፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለቤተሰብ ማድረግ ሰለሚጠበቅባቸው ሐዋሪያዊ እንክብካቤ የሚያወሳ ድህረ ሲኖዶስ አዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ለንባብ ማብቃታቸው ይታወሳል። በእዚህ ቃለ ምዕዳን በተለይም የሐይማኖት አባቶች በቤተሰብ ውስጥ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች በጥንቃቄ እና ብስለት በተሞላበት መልኩ፣ በጥንቃቄ በመመርመር በቤተሰብ ውስጥ የሚያግጥሙ ችግሮችን በችኮላ ከማውገዝ ይልቅ በእግዚኣብሔር ምሕረታዊ ጸጋ በመታገዝ የመፍትሄ ሐሳቦችን መጠቆም እንደ ሚገባቸው እና ይህንንም ክህሎት ቄሳውስት ማዳበር እንዲችሉ ቤተሰብን የተመለከተ ትምህርቶች ከዘረዓ ክህነት ጀምሮ መስጠት አስፍላጊ መሆኑን የሚገልጽ ጳጳሳዊ መልእክት ሲሆን በቅርቡ በመስከረም 24/2013 ዓ.ም ደግሞ በጣሊያነኛ ቋንቋ “fratelli tutti” ሁላችንም ወንድማማቾች ነን በሚል አርእስት ይፋ በአደርጉት ጳጳሳዊ መልእክት ወንድማማችነት እና ማህበራዊ ወዳጅነትን በተመለከተ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱን እያሳሰባቸው የመጡትን ጥያቄዎች እና በተጨማሪም ጳጳሳዊ መልእክቱ እ.ኤ.አ. በየካቲት ወር 2019 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ እና ታላቁ ኢማም  አህመድ አል-ታይብ ‘ሰብዓዊ ወንድማማችነት ለዓለም ሰላም እና አብሮ ለመኖር’ በሚል አርእስት በጋራ በተፈራረሙት ሰነድ ላይ ያጠነጠነ ጳጳሳዊ መልእክት ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።

ቅዱስነታቸው በእነዚህ ሰባት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው 23 የሚሆኑ በላቲን ቋንቋ motu proprio በአማሪኛው በግርድፉ ሲተረጎም (አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ እንደራሴ በመሆኑ፣ በእዚህ በተሰጠው መንፈሳዊ ስልጣን በራሱ ተነሳሽነት ወቅታዊ ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የይሚጽፋቸው ሰነዶች፣ የሚያደርጋቸው ሹመቶች፣ ውሳኔዎች የተመለከቱ ጉዳዮችን ያመለክታል) በእዚህም መሰረት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ግላዊ ተነሳሽነት 23 መልእክቶች መጻፋቸው ይታወቃል። እነዚህም በእርሳቸው የግል ተነሳሽነት የተጻፉ 23 መልእክቶች ወይም ባላቲን “motu proprio” ሞቱ ፕሮፕሪዮ መልእክታቸው “የቅድስት መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች መማክርት ጥልቅ የሆነ ታድሶ እንዲያደርጉ የሚያሳስቡ መልእክቶች፣ በቅድስት መነበር ውስጥ በተለይም ደግሞ በፋይናንስ እና በኢኮኖሚ ጉዳዮች ዙሪያ ግልጽነት እና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያሳስቡ መልእክቶች፣ በአንድ ባል እና በአንድ ሚስት መካከል የሚፈጠሩ ችግሮችን እንዴት ለመፍታት እንደ ሚቻል // ዘላቂ የሆነ መፍትሄ ማስቀመጥን የተመለከተ መልእክት፣ ለስርዓተ አምልኮ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውሉ መጽሐፍት በእየአንዳንዱ ሀገር ብጹዕን ጳጳሳት እውቅና አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በሚመጣጠን መልኩ ውጤታማ እንዲሆኑ ክለሳ እንዲደረግባቸው የሚጠይቅ መልእክት እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ አርእስቶችን ያቀፉ 23 ሞቱ ፕሮፕሪዮ በራሳቸው ተነሳሽነት በጣም ተጨባጭ እና ወቅታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ገንቢ የሆኑ ሐሳቦችን በማንሳት ለምፍቴ ማቅረባቸው ያታወቃል።

ቅዱስነታቸው በእነዚህ ሰባት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ጊዜያቸው ቤተሰብን በተመለከት ሁለት ጳጳሳዊ ሲኖዶሶች እንዲደረጉ ማድረጋቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም ወቅታዊ በሆነ መልኩ በቤተሰብ መካከል አሁን ስለሚታዩ ተግዳሮቶች በማንሳት እና ትኩረት በመስጠት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ብጹዕን ጳጳሳት በቤተሰብ ጉዳይ እንዲመክሩ በማድረግ ወቅታዊ ለሆኑ ችግሮች ወቅታዊ የሆነ ምላሽ በሀገረ ስብከት ደረጃ የሚሰጥበትን የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲቀይስ በር መክፈታቸው ይታወሳል።

ከታኅሳስ 01/2008 ዓ.ም. እስከ ኅዳር 11/2009 ዓ.ም. ደርስ ለ349 ቀናት ያህል የቆዬ ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ኢዩቤልዩ ማወጃቸው የሚታወስ ሲሆን ይህንን ልዩ ቅድሱ የምሕረት ዓመት በወቅቱ በክርስቲያኖች እና በሙስሊም እምነት ተከታዮች መካከል በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብሊክ በተነሳው እርስ በእርስ ግጭት ተጎሳቁላ በነበረች ሀገር በመገኘት የሁለቱንም የሐይማኖት ተወካዮች በአንድነት ፊት ለፊት አቀራርበው በማናጋገር እርቅ እንዲፈጥሩ መነገዱን በመክፈት በእዚያው በመካከለኛው የአፍሪካ ሪፖብልክ በባንጉዊ ከተማ በሚገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካቴድራል ተገኝተው ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ኢዩቤሊዪን ማስጀመራቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም 349 ቀናት ውስጥ ምዕመናን  መንፈሳዊ እና አካላዊ የምሕረት ተግባራት የሚፈጸሙበት ወቅት መሆኑን ገልጸው፣ በእዚህ ልዩ ቅዱስ የምሕረት አመት ክርስቲያኖች እርቅን እና ሰላምን ይፈጥሩ ዘንድ ማሳሰባቸው ይታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰባት አመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ከጣሊያን ውጭ 22 ሐዋሪያዊ ጉብኝቶችን ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በእነዚህም ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው በአፍሪካ አእጉር የሚገኙትን ኬኒያን፣ ሁጋንዳን እና የመካከለኛው አፍሪካ ሪፖብሊክ አንስቶ በኩባ በአሜሪካ፣ በላቲን አመሪካ በምስራቅ አውሮፓ እና በኤሺያ አህጉር በመጓዝ የሰላም እና የአንድነት መልእክት ማስተላለፋቸው የሚታወቅ ሲሆን 900 የካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙባትን አዛረበጃንን ጨምሮ አብዛኛው የማኅበረሰብ ክፍል የሙስሊም ተከታይ ወደ ሆኑባቸው ባንግላዲሽ እና የቡዳ እመንት ተከታይ ወደ ሚበዛባት ማያን ማር (የቀድሞ ስሟ በርማ) ድረስ በመሄድ የሰለም እና የአንድነት መልእክታቸውን ማስተላለፋቸው ያትወሳል። በጣሊያን ውስጥ ብቻ 17 የጣሊያን ከተሞችን በተለይም ደግሞ በተፈጥሮ አደጋ ለምሳሌም በርዕደ መሬት አደጋ ጉዳት የደረሱባቸውን እና ከአፍሪካ እና ከተለያዩ ሀገራት የተውጣቱ ስደተኞ ወደ አውርፓ አህጉር መግቢያ በር አድርገው የሚጠቀሙበትን የላፓዱዛ ዴሰትን ጭምር በመጎብኘት ለስደተኞች ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጥ ሰብዐዊ መብታቸው እንዲከበር ለዓለም ድምጻቸውን ማሰማታቸው እና ዓለም ለስደተኞች ከፍተኛ ትኩረርት እንዲሰጥ ማሳሰባቸው የሚታወስ ሲሆን ስደተኞችም በበኩላቸው በእንግድነት የሚቀበሉዋቸውን ሀገሮች ማሕበራዊ ሕግጋቶችን በማክበር እንዲኖሩ፣ በእንግድነት የተቀበላቸውን ማኅበረሰብ ወግ እና ባሕል እንዲጠብቁ ማሳሰቢያ መስጠታቸውም ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእነዚህ ሰባት የጵጵስና አመታት  ዘወትር ረቡዕ እለት ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ 8 ልዩ ልዩ አርእስቶችን መዳሰሳቸው የሚታወቅ ሲሆን በእነዚህ የጠቅላላ የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ “የእመታችን መገለጫ ከሆነው የጸሎተ ሐይማኖት አንስተው ሰባቱን ምስጢራት፣ የመነፍስ ቅዱስ ስጦታዎችን የተመለከቱ፣ ቤተ ክርስቲያንን፣ ቤተሰብን፣ ምሕረትን፣ የክርስቲያን ተስፋን እና በመጨረሻም  ባልፈው ሳምንት እስከ ተጠናቀቀው በመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት ዙሪያ እስካደርጉት  አስተምህሮ ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ጉዞ ወቅት በመነፈሳዊነት እንዲጓዙ የሚያበረታቱ አስተምህሮዎችን ማደርጋቸው ያታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሰባት ዓመታት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ እስከ ትላንትናው እለት ድረስ 600 ያህል ስብከቶችን ማደርጋቸው የሚታወስ ሲሆን የእዚሁ ስብከት አካል በሆነው በትላንትናው እለት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት 600ኛው ስብከታቸው ላይ “ክርስትያኖች በሕይወት ጉዞዋቸው የሚያጋጥማቸውን ችግሮች መጋፈጥ እንጂ መሸሽ የለባቸውም” ማለታቸው ይታወሳል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ at pontefix በተሰኘው የቲዊተር ገጻቸው በእየ እለቱ በሚያስተላልፉት ምልእክት በዓለም ዙሪያ 46 ሚልዮን ተከታይ እንዳላቸው የሚታወቅ ሲሆን በተጨማሪም Instagram በተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ 5 ሚልዮን ተከታዮች እንዳልቸው ይታወቃል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ መነበር ተተኪ በመሆን ከሰባት አመት በፊት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን 266ኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው መመረጣቸው የሚታወቅ ሲሆን በትውልድ አርጄንቲናዊ የሆኑ የ83 አመት እድሜ ባለጸጋ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ምዕረጋቸውን ከመቀበላቸው በፊት የነበራቸውን ካርዲናል በርጎሊዮ የሚለውን የመጠሪያ ስማቸውን በመቀየር በ13ኛ ክፍለ ዘመን የኖረውን እና የድኾች አባት በመባል የሚታወቀውን የአዚዚውን የቅዱስ ፍራንቸስኮ ፈለግ ለመከተል በማሰብ የእርሱ የመጠሪያ ስም የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስናቸው ዘመን መጠሪያ እንዲሆን በመምረጣቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መስረ ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም በሯን ክፍት ያደርገች፣ ልሁሉም የሰው ልጆች በቅዱስ ወንጌል የሚገኘውን ደስታ ማወጅ እና ማብሰር እንደ ሚገባት ምኞታቸው መሆኑን በተለያዩ አጋጣሚዎች መግለጻቸው ይታወቃል።

“ቤተ ክርስቲያን ሁሉንም የሰው ልጆች ማስተናገድ የሚትችል የሰው ልጆችን እንደ ሕይወታቸው ፈተና እና ድካም ቦታ ልትሰጣቸው የምትችል ቤተ ክርስቲያን እንደ ሚመኙ መግለጻቸው የሚታወቅ ሲሆን በጠቃላይ  ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም የሰው ልጆች ተደራሽ መሆን ይገባታል፣ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ የሕይወት ጫናዎች ምክንያት ከቆሰሉ ሰዎች ጋር በመሆን የፈውስ ሂደት አካል ልትሆን ይገባታል የሚል ጽኑ አቋም እንደ ሚያንጸባርቁ ያታወቃል። አንድ በምቾት ውስጥ ያለች ቤተ ክርስቲያን በራሷ ምቾት ብቻ ራሱና ቆልፋ የምትኖር ከሆነ ያቺ ቤተ ክርስቲያን ጤናማ ቤተ ክርስቲያን ልትባል አትችልም በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህንን የመስለ አሉታዊ ባሕርይ ያልቸው አብያተ ክርስቲያናት ይህንን አፍራሽ የሆነ ባሕሪይ በማስወገድ ሰውን ከእግዚኣብሔር ለማገናኘት የተሰጣትን ተልዕኮ በመወጣት በእምነት የሚገኘውን ውበት እና ደስታ ለሰው ዘር በሙሉ ማሳየት እንደ ሚኖርባት ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ Evangelii gaudium  በአማሪኛ ሲተረጎም “በወንጌል የሚገኝ ደስታ”በሚል አርእስት በጻፉት ቃለ ምዕዳን በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን በእዚህም ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያን በጉዞ ላይ መሆን እንዳለባት እና ቤተ ክርስቲያን ሐዋሪያዊ ተልዕኮዋን ለማከናወን እና ሰዎችን ወደ እግዚኣብሔር ለመመለስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እና በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ወደ ሕዝቡ መሄድ እንዳለባት የሚያሳስብ ቃለ ምዕዳን ለንባብ ማብቃታቸው የሚታወቅ ሲሆን ይህ ቃለ ምዕዳን ቤተ ክርስቲያንን መስፈስ ቅዱስ እንድያስገርማት  መፈቅድ ይገባታል የሚል ጭብጥ ያዘለ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን በቀጣይንት ድምጹዋን እንድታሰማ እና አዳዲስ ነገር በቤተ ክርስቲያን እንዲከሰት የሚያደርገው መነፍስ ቅዱስ ስለ ሆነ መነፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን እንድያንቀሳቅስ ልንፈድለት ይገባል የሚል አጠቃላይ የሆነ ምልእክት የያዘ ቃለ ምዕዳን ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእዚህ በሰባት አመት የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና አመታት  በዋነኛነት እና በማዕከላዊነት “ምሕረት” የሚለውን ቃል በተደጋጋሚ መጥቀማቸው የሚታወቅ ሲሆን በእዚህም መሰረት “የሰማይ አባታችሁ መሐሪ እንደ ሆነ እናንተም ምሕረት አድራጊዎች ሁኑ” የሚለው የክርስቲያኖች የእለት ተእለት መፈክር ሊሆን ይገባል በማለት በተደጋጋሚ ማስታወሳቸው ይታወሳል። ሁላችንም የመጨረሻ ቀን ፍርድ እንደ ሚጠብቀን በመጨረሻው ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከማልኣክቱ ጋር በዙፋኑ ላይ ቁጭ ብሎ በጎቹን ከፊየሎቹ በመለየት በማቴዎስ ወንጌል 25 እንደ ተጠቀሰው ተርቤ አብልታችሁኛል፣ ተጠምቼ አጠጥታችኃኛል፣ ታርዤ አልብሳችሁኛል፣ እንግዳ ሆኜ መጥቼ ተቀብላችሁኛል. . .ወዘተ በማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያቀርብልን ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ከአሁኑ መዘጋጀት ይኖርብናል በማለት በተደጋጋሚ የተናግሩ ሲሆን በመጨረሻው ሰዓተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰጥን ፍርድ አሁን በሕይወት እያለን በምናከናውነው የምሕረት ወይም የበጎ አድርጎት ተግባር ላይ በተመሰረተ መልኩ በመሆኑ ከአሁኑ በጎ ተግባራርትን ማከናወን ይኖርብናል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በእዚሁ በሰባት አመት የጵጵስናቸው አመታት  በቤተ ክርስቲያን የቄስውስት ብቻ ሳትሆን መላው ምዕመን በተገቢው መልኩ ይሳተፉ ዘንድ መፈቀድ እንደ ሚገባ በተደጋጋሚ ማሳሰባቸው የሚታወቅ ሲሆን ምዕመናን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያልቸውን ሚና በሚገባ እንዲወጡ ማስቻል ያስፈልጋል በማንኛውም የቤተ ክርስቲያን ውሳኔዎች ውስጥ ምዕመናን በትኩረርት እንዲሳተፉ ማድረግ ይገባል የሚል ጽኑ አቋም እንዳላቸው የታወቃል። በተለይም ደግሞ ሴቶች በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ አስተዋጾ ስላላቸው ይህንን አዎንታዊ የሆነ ሚና እንዲጫወቱ መፍቀድ ያስፈልጋል በማለት በተደጋጋሚ የተናገሩት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ ማሪያም ከኢየሱስ ደቀ-መዛሙርት በላይ እንደ ነበረች በማንሳት ሴቶች ለቤተ ክርስቲያን ሊያበረክቱት የሚችሉትን ከፍተኛ አስተዋጾ ቅዱስነታቸው በተደጋጋሚ አመላክተዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጵእሳት ፍራንቸስኮ በእዚሁ በሰባት አመት የጵጵስናቸው ዘመን ክርስቲያኖች ሁሉ ቅዱስ ወንጌልን በማብሰር ሂደት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጾ መጫወት እንደ ሚገባቸው በመገለጽ ክርስቲያኖች በመነፍስ ቅዱስ በመሞላት ቅዱስ ወንጌልን “በድፍረት፣ ጮክ ብሎ እና በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ለማወጅ መዘጋጀት ይገባቸዋል ማለታቸውም የሚታወስ ሲሆን “በተለይም ደግሞ በተለያዩ ምክንያቶች በስቃይ ላይ የሚገኙትን ሰዎች ተጨባጭ በሆነ መልኩ በማገዝ፣ ተስፋ እንዳይቆርጡ በማድረግ ተፋቸው እንዲለመልም የሚያደርጉ የምሕረት ተግባራርትን ማከናወን ይገባል በማለት በተደጋጋሚ መናገራቸው ይታወቃል።

17 December 2020, 12:39