ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ  ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ቤተሰብ የጸሎት ቤት በሚሆንበት ጊዜ ጥልቅ የሆነ ፍቅር በእዚያ ይኖራል አሉ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ አሁን ያልንበት ወቅት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወልደበት እለት የሚከበርበት የገና በዓል ወቅት እንደ ሆነ የምታወቅ ሲሆን በታኅሳስ 18/2013 ዓ.ም ደግሞ የኢየሱስ፣ የማርያም እና የዮሴፍ የቅዱስ ቤተሰብ በዓል በታላቅ መንፈሳዊነት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን በዓል ምክንያት በማደረግ በቫቲካን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጽ ሲሆን ማለታቸው ተዘግቧል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

የገናን በዓል ካከበርን (የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ማለት ነው) ከጥቂት ቀናት በኋላ ዛሬ የምናከናውነው ሥርዓተ አምልኮው ትኩረታችንን በኢየሱስ ፣ በማርያምና ​​በዮሴፍ ቅዱስ ቤተሰብ ላይ እንድናደርግ ይጋብዘናል። የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሁሉም ሕጻናት ልጆች የቤተሰቡ ሙቀት እንደ ሚያስፈልገው በምያሳየው እውነት ላይ ማሰላሰሉ መልካም ነው። በትክክል በዚህ ምክንያት የናዝሬት ቤተሰብ ሁሉም የአለም ቤተሰቦች አስተማማኝ የማጣቀሻ ነጥባቸውን እና የተረጋገጠ መነሳሳትን የሚያገኙበት ሞዴል የሆነ ቤተሰብ ነው። በፀደይ ወቅት በናዝሬት ሰው ሆኖ የበቀለው የእግዚአብሔር ልጅ ሲሆን በወቅቱ በድንግል ማርያም ማኅፀን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ የተፀነሰበት ወቅት ነበር። በናዝሬት የእንግዳ መቀበያ ቤት ሳያገኙ ቀርተው በግርግም ውስጥ ተወልዶ የኢየሱስ ልጅነት በደስታ የተከናወነ ሲሆን በማሪያም የእናትነት እንክብካቤ እና በዮሴፍ የአባትነት እንክብካቤ ተከቦ ነበር፣ እርሱም ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ርህራሄ ማየት ችሏል።

የቅዱስ ቤተሰብን አብነት በመከተል ቤተሰብ ትምህርት ቤት መሆኑን የሚያሳዩ እሴቶችን እንደገና እንድናገኝ ተጠርተናል፤ የተስፋ አድማሶችን በመክፈት ግንኙነቶችን ሁል ጊዜ በሚያድስ ፍቅር መመስረት ያስፈልጋል። ቤተሰብ የጸሎት ቤት በሚሆንበት ጊዜ ፣ ​​ፍቅር ጥልቅ እና ንፁህ በሚሆንበት ጊዜ ፣ ክርክር በይቅርታ ሲያሸንፍ ፣ የዕለት ተዕለት የኑሮ ውድነት በጋራ ርህራሄ እና በእግዚአብሄር ፈቃድ በሰላማዊ መንገድ በመታዘዝ ልባዊ ህብረት ማግኘት ይቻላል። በዚህ መንገድ ቤተሰቡ እግዚአብሔር እንዴት በደስታ መስጠት እንዳለባቸው ለሚያውቁ ሰዎች ሁሉ የሚሰጣቸውን ደስታ ይካፈላሉ። በተመሳሳይ ጊዜም ​​ራሱን ወደ ውጭ በማውጣት ለሌሎች ለወንድሞቹ አገልግሎት ለዘለቄታው አዲስ የሆነና የተሻለ ዓለም ለመገንባት  ለመተባበር ራሱን ለመክፈት መንፈሳዊ ኃይል ያገኛል ፤ ስለሆነም አዎንታዊ ተነሳሽነት መግለጽ የሚችል፣ ስብከተ ወንጌልን በሕይወቱ መስበክ የሚችል ሰው ምሳሌ ይሆናል።

የዛሬ አምስት አመት ገደማ ይፋ የሆነው እና በመጪው እ.አ.አ መጋቢት 19/2021 ዓ.ም ይፋ የሆነበት 5ኛው ዓመት የሚዘከርለት በላቲን ቋንቋ “Amoris laetitia” (የፍቅር ሐሴት) በሚል አርእስት የተጻፈው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ላይ እንደተገለጸው የጠበቀና የቤተሰብ ፍቅርን ተስማሚ አድርጎ በማቅረብ ይህንን ገቢራዊ እንድናደርግ ለዚህ አስቸኳይ ጥሪ ያቀርብልናል።

ይህ ልዩ ዓመት በላቲን ቋንቋ “Amoris laetitia” (የፍቅር ሐሴት) በተሰኘው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያ ሰነድ ይዘቶች ላይ አስተያየት እና ሐዋርያዊ መሳሪያዎችን ጥልቀት ባለው መልኩ ለመረዳት እድሉን ይሰጠናል። ለቤተክርስቲያኗ ማህበረሰቦች እና ለቤተሰቦቻቸው በጉዞአቸው አብረው እንዲጓዙ ያደረጋል። ከአሁን ጀምሮ ሁሉም ሰዎች የምዕመናንን፣ የቤተሰብን እና የሕይወትን ጉዳይ በበላይነት የሚቆጣጠረው ጳጳሳዊ ምክር ቤት አስተባባሪነት እና ተነሳሽነት በዓመቱ ውስጥ የምንራመድበት ሁኔታ በማመቻቸት በሚካሄደው አመት ውስጥ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ እገብዛለሁ። ይህንን ጉዞ ከመላው ዓለም ከመጡ ቤተሰቦች ጋር ማከናወን አንችል ዘንድ ለናዝሬት ቅዱስ ቤተሰብ በተለይም የማርያም እኞኛ እና አስተዋሽ አባት ለሆነው ለቅዱስ ዮሴፍ በአደራ እንሰጣለን።

የአዳዲስ ሰብአዊነት እርሾ እንድንሆን፣ ተጨባጭ እና ሁለንተናዊ የመተባበር መንፈስ እንዲኖር አሁን የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ገብርሄል ጸሎት በምንጸልይበት ወቅት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለም ውስጥ የሚኖሩ ቤተሰቦችን ሁሉ በቅዱስ ቤተሰብ የወንጌላዊነት ፍላጎት እንዲማረኩ እንድትረዳቸው አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባል።

27 December 2020, 12:43