ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ምንም ዓይነት ወረርሽኝ የእግዚአብሔርን ብርሃን ሊያጠፋ አይችልም አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕዳር 27/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለው ጸሎት ከተደገመ በኋላ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በስፍራው ማለትም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አስቸጋሪውን ወቅታዊውን ብርዳማ የሆነ የአየር ንበረት እና ዝናብ ተቋቁመው እርሳቸው በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ የሚያደርጉትን አስተንትኖ ለማዳመጥ በስፍራው የተገኙ ምዕመናን በቅድሚያ አመስግነዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“በእነዚህ ቀናት ውስጥ በብዙ ቤቶች ውስጥ ሁለት የገና በዓል ምልክቶች እየተዘጋጁ ናቸው እነዚህም ልጆችን እና ጎልማሶችንም ያስደስታቸዋል በተለይም በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የተስፋ ምልክቶች ሁነው እንደ ሚያገለግሉ” የገለጹት ቅዱስነታቸው በእነዚህ ውጫዊ ምልክቶች ማለትም የጋና ዛፍ በመስራት ላይ ብቻ መጠመድ አይኖርብንም፣ ነገር ግን ወደ ኢየሱስ ትርጉሙ ማለትም ልጁን ለእኛ ወደ ገለጠልን የእግዚአብሔርን ፍቅር መመልከት እና በዓለም ላይ የእግዚአብሔር ፍቅር እንዲያበራ እና ማለቅያ ወደ ሌለው ፍቅር የሚመራን ምልክት ሊሆን ይገባዋል ብለዋል።

ምንም ዓይነት ወረርሽኝ ቢከሰትም እንኳን ይህንን በእግዚአብሔር ፍቅር የተሰጠንን ብርሃን ሊያሸንፍ እንደ ማይችል ልንገነዘብ እንደ ሚገባ የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህ የፍቅር ብርሃን የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ልባችን እንዲገባ እንፍቀድ፣ በከፍተኛ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ልንጸልይ ይገባል ብለዋል። በዚህ መንገድ እግዚአብሔር በእኛ እና በእኛ መካከል እንደ አዲስ ይወለዳል ካሉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እንደ ሚያደርጉት መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ሳምንታዊውን መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

06 December 2020, 11:52