ፈልግ

በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤዎቻቸውን ባቀረቡበት ወቅት በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤዎቻቸውን ባቀረቡበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የበለጠ ፍትሃዊ እና ወንድማዊ የሆነ አለም መገንባት ይኖርብናል አሉ!

በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤዎቻቸውን በሕዳር 25/2013 ዓ.ም ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት በዚህ በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በተከሰቱት ተግዳሮቶች ወቅት ፣ የመወያየት መንፈስን ለመገንባት እና የማባከን ባህል ለመዋጋት በመተባበር እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከፍተኛ እሳቤዎችን እና አስፈላጊ ዓላማዎችን ለማሳካት እንደ ሚሰሩ ያላቸውን ተስፋ የገለጹ ሲሆን የተሻለ ፍታሃዊ እና በመንድማማችነት መንፈስ የተሞላ ዓለም ለመገንባት እያንዳንዳችን መሥራት ይኖርብናል ብለዋል።

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ - ቫቲካን ከተማ

አስር የአለም አገራት እና አዲስ እና ልዩ ልዑኮቻቸውን ወደ ቅዱስት መንበር መላካቸው የተገለጸ ሲሆን አምባሳደሮቹ የሹመት ደብዳቤያቸውን ባቀረቡበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሱ አቀባበል ተደርገውላቸዋል። እነዚህ በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል ተሹመው የሹመት ደብዳቤዎቻቸውን ያቀረቡት አገራት ከዮርዳኖስ፣ ካዛክስታን ፣ ዛምቢያ ፣ ሞሪታኒያ ፣ ኡዝቤኪስታን ፣ ማዳጋስካር ፣ ኢስቶኒያ ፣ ሩዋንዳ ፣ ዴንማርክ እና ህንድ የመጡ አባሳደሮች እንደ ሆኑም ተገልጿል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

በአቀባበሉ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባደረጉት ንግግር እንደ ገለጹት እነዚህ በቫቲካን አዲስ የተሾሙ የተለያዩ አገራትን በመወከል የተሾሙ አዳዲስ አባሳደሮች የሚጀምሩት አዲስ ተልእኮ “ለመላው የሰው ልጅ ቤተሰብ ታላቅ ፈተና” በሆነበት የኮሮና ቫይረስ ወቅት እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን ይህንን የኮሮና ወረርሽኝ በተቀናጀ እና ወንድማማችነት በተሞላው መንፈስ ልንዋጋው ይገባል ብለዋል።

ድሆችን አንርሳ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አክለው እንደ ገለጹት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳይከሰት በፊት እንኳን ዓለማችን በከፍተኛ ችግር ውስጥ የምትገኝ ፕላኔት መሆኗን የገለጹ ሲሆን “በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ባሉ ግጭቶች ፣ አመጾች እና አሸባሪዎች ሳቢያ አስቸኳይ ሰብዓዊ ችግሮች ” የተስተናገደበት ወቅት እንደ ነበረ ገልጸዋል። የኢኮኖሚ ቀውሶች እና የአየር ንብረት ለውጥ እየተፈጠሩ መሆናቸውን የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ረሃብ እና የጅምላ የስደተኞች ፍልሰት” እና “የተፈጥሮ አደጋዎች ፣ ረሃብ እና ድርቅ” እየጨመሩ መሄዳቸው እንደሚያሳስባቸው ቅዱስነታቸው አክለው ገጸዋል። እነዚህ ሁሉ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ በፊት የነበሩ ችግሮች ወረርሽኙ ከተከሰተ በኋላ “በህብረተሰባችን ውስጥ ቀድሞውኑ የሚታዩት ልዩነቶች እና ችግሮች እየተባባሱ መሄዳቸውን” የገለጹ ሲሆን በእውነቱ ድሆች እና በጣም ተጋላጭ የሆኑት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ችላ የማለት፣ የመገለል እና የመርሳት አደጋ” አስከትሏል ብለዋል።

መወያየት እና መተባበር ያስፈልገናል

ስለዚህ በአንድ ጀልባ ውስጥ ለመሳፈር አብሮነታችንን ለማረጋገጥ፣ ይህንን መከራ ለመሻገር እና ለማሸነፍ አንድ መሆን ያስፈልጋል በማለት የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ንግግራቸውን ሲቀጥሉ በዛሬው ጊዜ ምናልባትም ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ሉላዊ እየሆነች በመምጣት ላይ ባለችው ዓለማችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እየተሻሻለ ነገር ለመፍጠር ይቻል ዘንድ በአስቸኳይ ቅን እና አክብሮት የተሞላበት ውይይት እና ትብብር ማደረግ ያስፈልጋል፣ በምድራችን ላይ የሚንፀባርቁትን ከባድ አደጋዎች በመፍታት አንድ ሊያደርገን የሚችል ሁኔታዎችን በመፍጠር ለወጣቱ ትውልድ የተሻለ ሁኔታ እና ዕድል መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ወቅት ትኩረት የሰጡት በቅርቡ በመስከረም 24/2013 ዓ.ም ይፋ ባደረጉት “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚለው እርሳቸው ይፋ ባደረጉት ሐዋርያዊ መልእክት ላይ የነበረ ሲሆን  “የእያንዳንዱን ሰው ክብር በማወቅ በዓለም ዙሪያ ለሁሉም የወንድማማችነት ምኞትን እናነቃቃለን” የሚል ምኞት እንዳላቸው ገልጸዋል። የቅድስት መንበር በዓለም ላይ ካለው ቁርጠኝነት አንፃር ፣ በዓለም አቀፍ የጋራ ጥቅም አገልግሎት እንዲሁም በሕዝቦችና በሕዝቦች ሕይወት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ የሥነ ምግባር ገጽታዎች መከበርን ለማስታወስ የሚረዳ ሐዋርያዊ መልእክት እንደ ሆነ አከለው ገጸዋል።

የግንኙነት ባሕልን ይውደዱ

የቅድስት መንበር ፍላጎት እና ተግባር በዓለም ላይ ካለው ቁርጠኝነት አንጻር ሲታይ በግለሰቦች ፣ በሕዝቦች ሕይወት እና በአጋራት ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማለትም ሥነ-ሰብአዊ ፣ ሥነ-ምግባራዊ እና ሃይማኖታዊ ገጽታዎች ትኩረትን በመሳብ “ለዓለም አቀፍ የጋራ ጥቅም አገልግሎት” ትኩረት ሰጥታ እንደ ምትንቀሳቀስ የገለጹ ሲሆን እነዚህ በቫቲካን የተለያዩ አገራትን በመወከል የመጡ አምባሳደሮች ይህንን ተግባር እንደ ሚያስፈጽሙ ያላቸውን ምኞት አክለው ገለጸዋል።

በቫቲካን ወይም በቅድስት መንበር የተለያዩ አገራትን በመወከለ የመጣችሁ አምባሳደሮች በዲፕሎማሲ እንቅስቃሴያችሁ “ተገናኝቶ የመወያየት ባህል” እንደ ምታበረታቱ ተስፋ አደርጋለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው፣ ስለሆነም ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ እሳቤዎችን እውን ለማድረግ እንቅፋት የሆኑትን ልዩነቶችን እና ክፍፍሎችን ማስወገድ አስፈላጊ ነው ብለዋል። በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የቀረቡ ዓላማዎች፣ በእውነቱ እያንዳንዳችን የበለጠ ፍትሐዊ ፣ ወንድማዊ እና አንድነት ያለው ዓለም ለመገንባት በየቀኑ እንድንሠራ ይጋብዘናል ያሉት ቅዱስነታቸው ስፍሃዊ እና የወንድማማችነት ባሕል ይሰፍን ዘንድ የበለጠ መትጋት ይኖርብናል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

04 December 2020, 13:39