ፈልግ

ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን በቫቲካን በተከበረበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ መስዋዕተ ቅዳሴ ሲያሳርጉ ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን በቫቲካን በተከበረበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ መስዋዕተ ቅዳሴ ሲያሳርጉ 

የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም

ዛሬ ሕዳር 06/2013 ዓ.ም አለም አቀፍ የድሆች ቀን በመላው የካቶሊክ ቤተክርስትያን ምዕመናን ዘንድ ተክብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን ይህ ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን በመላው ዓለም በሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። ከእዚህ ቀደም በርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ አነሳሽነት በተከበሩት ዓለም አቀፍ የድሆች ቀን ላይ ቅዱስነታቸው የተለያዩ መልእክቶችን ያስተላለፉ ሲሆን ቅዱስነታቸው ባለፈው አመት አለም አቀፍ የድሆች ቀን በተከበረበት ወቅት ያስተላለፉትን መልእክት በድጋሚ እንደ ሚከተለው አንቀርብላችኋለን፣ ተከታተሉን።

“የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም” (መዝ 9፡18)።

1.     “የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም” (መዝ 9፡18)። እነዚህ የመዝሙረ ዳዊት ቃላት ወቅታዊ ናቸው። እነዚህ ቃላት ድሆች በልባቸው ውስጥ ከሁሉም ነገር በላይ የሆነው እምነትን እንዳላቸው ከፍ አድርጎ በማሳየት የፍትሕ መዛባት፣ ስቃዮች እና የኑሮ አለመረጋጋት በሚያጋጥማቸው ጊዜ ያጡትን ተስፋ ወደነበሩበት መመለስ የሚችል አቅም እናዳልቸው ያሳያል።

ይህ የመዝሙረ ዳዊት ክፍል የችግረኞችን ሁኔታ እና የሚጨቁኗቸውን እብሪተኞች ሁኔታ ይገልፃል። ፍትህ እንዲሰፍን እና ክፉን ለማሸነፍ የእግዚአብሔርን ፍርድ ይመጣ ዘንድ ይማጸናል። በእዚ በመዝሙረ ዳዊት ቃል በጣም የቆዩ ጥያቄዎችን በድጋሚ ለማንሳት እንገደዳለን። አምላክ ይህን ልዩነት እንዴት ይታገሣል? ድሆችን በመከራቸው መጥቶ ሳያግዛቸው ችግረኞች እንዲዋረዱ እንዴት ያደርጋል? በተለይም ድሆች እየተሰቃዩ ባለበት ሁኔታ ላይ ጨቋኞች እንዲበለፅጉ ለምን ፈቀደ?

ይህ የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ ክፍል የተጻፈው የተደላደለ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት በነበረበት ወቅት እን እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ ማኅበራዊ ልዩነት በነበረበት ወቅት የተጻፈ ነው። እምብዛም የማይታየው ፍትሃዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ድሆችን እንዲፈጠሩ ያደረገ ሲሆን እነዚህም እጅግ በጣም ደካማ በሆኑ ሰዎች ከሚገኙት ሀብቶች ጋር ሲነፃፀር ሲታይ ጥቂት የሚባሉ ሰዎች የሚያገኙት ሐብት ይበልጥ የተጋነነ ነው። የመዝሙረ ዳዊ ጸሐፊም ሁኔታውን በመመልከት ስዕላዊ በሆነ መልኩ ስለሁኔታው እውነትነት ተጨባጭ በሆነ መልኩ ያቀረባል።

ይህ ወቅት እብሪተኞችና ፈርሃ እግዚኣብሔር የሌላቸው ሰዎች ድሆችን ለመውረር እና ያላቸውን ጥቂት የሆነ ንብረት እንኳ ሳይቀር ለመንጠቅ እና ወደ ባርነት ቀንበር ውስጥ ሊከቱዋቸው ኣንደ ሚፈልጉ እናያለን። ዛሬ ያለው ሁኔታ ከዚህ እንብዛም የተለየ አይደለም። የኢኮኖሚ ቀውሱ አብዛኛዎቹ ሰዎች ተመጣጣኝ ባለሆነ ሁኔታ ብዙ ሀብት ከማከማቸት አላገዳቸውም፣ በተቃራኒው ደግሞ በከተሞቻችን አውራ ጎዳናዎች ላይ በርካታ ሰዎች በየዕለቱ መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ፍለጋ ዚባዝኑ እና ብዙዎቹ ድሆች ደግሞ ለጉልበት ብዝበዝ እና ለውርደት ተዳርገዋል። በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ውስጥ “ሀብታም ነኝ፤ ባለጠጋ ነኝ አንዳችም አያስፈልገኝም’ ትላለህ፤ ነገር ግን ጐስቋላ፣ ምስኪን፣ ድኻ፣ ዕውርና፣ የተራቈትህ መሆንህን አታውቅም” (ራእይ 3፡9) ይለናል። ዘመናት ያልፋሉ፣ ነገር ግን ከታሪክ ምንም እንድላተማርን በማስመሰል በሐብታም እና በድሃ መካከል ያለው ልዩነት እንዲሁ እየሰፋ በቋሚነት ቀጥሉዋል። በእዚህ አግባብ ስንመለከተው የመዝሙረ ዳዊት ቃላት በእዚያን ባለፈው ጊዜ የነበሩ ቃላት ብቻ ሳይሆኑ አሁን እኛ ባለንበት ዘመን እየተከሰተ የሚገኝ እውነታ ነው፣ በእዚህም የተነሳ በእዝጊኣብሔር ፍርድ ፊት ጉዳዩ ይቀርባል።

2.     ዛሬም ቢሆን በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወንዶችን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና ሕጻናት በአዲስ መልክ በተዘረጉ በርካታ ዓይነት የባርነት ቀንበር ውስጥ እንደ ሚገኙ አምነን መቀበል መቻል ይኖርብናል።

እናት አገራቸውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰደዱ የተገደዱ ቤተሰቦቻችን፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ሕጻናትን ወይም ደግሞ ጭካኔ በተሞላው መንፈስ ጉልበታቸውን ለመበዝበዝ ከወላጆቻቸው የተነጠቁ  ሕጻናትን፣ ሙያዊ ክህሎቶቻቸውን በተግባር ለማዋል የሚፈልጉ ነገር ግን የአጭር ጊዜ ትርፍ በሚፈልገው የኢኮኖሚ መዋቅር የተነሳ ይህንን ሙያቸውን እውን ለማደረግ ያልቻሉ ወጣቶችን፣ የተለያዩ የሃይል ድርጊቶች ሰለባ ወይም ተጎጂዎች የሆኑ፣ አስገዳጅ በሆነ መልኩ ከዝሙት አዳሪነት እስከ የአደንዛዢ እጽ አዘዋዋሪነት በጣም አስከፊ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ዛሬም ቢሆን በእየለቱ እንመለከታለን። በተደጋጋሚ ጊዜ ለፖለቲካዊ ንግድ ጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙትን፣ ብዙን ጊዜ ለጥቂት ሰዎች የገል ጥቅም ማስገኛ እየዋሉ የሚገኙትን እነዚህ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን ሁኔታ አጋርነት እና እኩልነት የተነፈጉ ስንቶቹ ናቸው? ኑሮዋቸው የተዛባ እና በየከተማዋችን ጎዳናዎች ላይ ፈሰው የሚገኙ ቤት አልባ የሆኑ ሰዎች ስንት ናቸው?

የቆሻሻ መጣያ ማጠራቀሚያ ውስጥ የተትረፈረፈ ኑሮ ያላቸው ሰዎች የጣሉትን ለኖሮዋቸው የሚጠቅማቸውን ወይም የሚለበስ ነገር ፈልጋ በእየለቱ የሚኳትኑ ድሆች ስንት ናቸው! በእዚህ አኳኋን እነሱ እራሳቸው የሰዎች የቆሻሻ መጣያ እቃዎች አካል ይሆናሉ፣ በዚህ ቅሌት ውስጥ የሚሳተፉ ሰዎች ጥቂት የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማቸው ድሆችን እንደ ጉድፍ ይመለከታሉ። ብዙውን ጊዜ ድሆች በማኅበረሰቡ ላይ የተመሰረቱ ጥገኛ ህዋሳት ተደርገው የሚቆጠሩ ሲሆን ለድህነታቸው ይቅርታ አይደረግላቸውም። ፍርድ ሁል ጊዜም ቢሆን የሚሰጠው በእነርሱ ዙሪያ ነው። እነሱ ድሆች እንዲፈሩ ወይም ተስፋ እንዲቆርጡ አይፈቀድላቸውም; እነሱ ድሆች ስለሆኑ ብቻ እንደ ማፈሪያ ወይም እንደ ጥቅም የለሽ ነገር ተደርገው ይቆጠራሉ።

ይባስ ብሎ ደግሞ እጅግ የከፋ የድህነት ዋሻ ጫፍ አይታያቸውም። እነርሱን ድሆችን ከተቀረው ማኅበረሰብ የተገለሉ ለማደረግ በማሰብ የስነ-ሕንጻ ሙያዎችን በመጠቀም ለድሆች ካለው ጥላቻ የተነሳ ድሆን የሚያገል የግንባታ ሥራ የሚሰራበት ወቅት ላይ ደርሰናል። ድሆች ከከተማችን ከአንዱ ጫፍ ተነስተው ወደ ሌላው ጫፍ ድረስ በመሄድ ሥራ፣ ቤት እና ፍቅር በመፈለግ በመኳተን ላይ ይገኛሉ። በእዚህ ሂደት ውስጥ ለእነርሱ ያላቸው ትልቁ ሐብት የጸሐይ ብርሃን ብቻ ሲሆን ይህንን እንኳን በሚገባ ማግኘት እንዳይችሉ ጥቃት እና በደል ይደርስባቸዋል። ወቅታዊ የሆኑ ፍራፍሬዎችን ለመሰብሰብ ንዳድ በሆነ ብርቱ ፀሐይ ሥር ሆነው ለበርካታ ሰዓታት በጣም ዝቅተኛ በሆነ ክፍያ ይህንን ከባድ ሥራ እንዲሰሩ ይገደዳሉ። ሥራቸው ለአደጋ የተጋለጠ እና በተጨማሪም ኢሰብአዊ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ የገደዳሉ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር እንደ ልባቸው እንዳይገናኙ ይከለከላሉ። የሥራ አጥነት ካሳ፣ ጥቅማጥቅሞች አይከፈላቸውም ወይም ሲታመሙ የሕክምና ዋስታና እንኳን አይሰጣቸውም።

ዘማሪው ዳዊት ድሆችን የሚዘርፉ ሀብታሞችን አሰቃቂ እውነታዎችን “ በስውር ያደባሉ . . .ረዳት የሌለውን ለመያዝ ይሸምቃሉ፤ ድኻውንም አፈፍ አድርጎ በወጥመዱ ይጐትታሉ” (መዝ. 10፡9) በማለት ሰለሁኔታው አስከፊነት ይገልፃል። በእዚህ አደን ምክንያት ድሆች ተጠምደዋል፣ ተይዘዋል፣ ለባርነት ተዳርገዋል። በዚህም ምክንያት ብዙዎቹ ተስፋ ቆርጠዋል፣ ከመጠን በላይ በሆነ ጭንቀት ውስጥ ገብተዋል። በአጭሩ በፊት ለፊታችን የምናያቸው ድሆች ስለእነርሱ መጥፎ ነገር የሚነገር እና ለተጋነን መከራ የተዳረጉ ናቸው። ሁሉም ድሆች በተጽእኖዎች ሥር የወድቃሉ ድምጻቸው በህብረተሰብ ውስጥ እንዲሰማ እንኳን አይደረግም።

3.     የመዝሙረ ዳዊት መጽሐፍ አቀማመጥ በፍትህ መዛባት፣ በችግረኞች እና በስቃይና መከራ ውስጥ ያሉትን ድሆች በተመለከተ በሐዘን ያናገራል። በተመሳሳይም መልኩ ልብን በሚነካ መልኩ ድሃ ማለት ምን ማለት እንደ ሆነ ትርጉሙን ይናገራል፣ እነርሱ "በእግዚአብሔር ላይ እምነታቸውን የጣሉ" በእርግጠኝነት እርሱ ፈጽሞ እንደማይተዋቸው እርግጠኛ የሆኑ ናቸው በማለት ይናገራል። በቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ድሆች በእግዚኣብሔር የሚያምኑ ናቸው በማለት ይናገራል! ዘማሪው ዳዊት ለዚህ ምክንያት መልስ ሲሰጥ እነርሱም ጌታን በሚገባ "ያውቁታል” በማለት ይናገራል። በመጽሐፍ ቅዱስ ቋንቋ እንዲህ ዓይነቱ "እውቅና" የግል ስሜትን እና የፍቅር ግንኙነትን ያካትታል።

በሚያስደንቅ እና ፈጽሞ ባልተጠበቀ ሁኔታ እግዚኣብሔር ከድሆች ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት ይገልጻል። የእሱ የመፍጠር ኃይል ከሁሉም ሰብዓዊ ፍላጎቶች በላይ የሆነና እያንዳንዱ ግለሰብ "በማስተዋል” እንደ ሚመለከት ያሳያል። ይህም በጌታ ላይ ያላቸው መታመንን ተስፋ እናድይቆርጡ እና በእየጊዜው ተስፋቸው እየለመለመ እየጨመረ እንዲሄድ ያደርጋል። ድሃዎች እግዚአብሔር ሊተዋቸው እንደማይችል ያውቃሉ፣ ስለዚህ እነሱ ሁልጊዜ በሚያስታውሳቸው አምላክ ፊት ናቸው። የእግዚያብሄር እርዳታ አሁን ካለው የስቃይ ሁኔታ ባሻገር በመሄድ ጥናካሬን እና የሰውን ልብ የመቀየር ከእዚያምም ወደ ነጻነት መንገድ የመምራት አቅም እንዳለው ይታወቃል።

4.     መጽሐፍ ቅዱስ አምላክ በድሆች ፈንታ ስለሚወስደው እርምጃ በተደጋጋሚ ይናገራል። እርሱ ጩኸታቸውን "ይሰማል" እና "ያድናቸዋልም"፣ እርሱ ይከላከልላቸዋል እንዲሁም ይጠብቃቸዋል. እርሱ "ይታደጋቸዋል"  "ያድናቸዋልም"! በእርግጥ ድሆች በስቃያቸው ውስጥ እግዚአብሔር ግድየለሽ ሆኖ ወይም ዝም ብሎ አይመለከታቸውም። እግዚአብሔር ፍትህን የሚሰጥና የማያሳፍር ነው (መዝ 40:18; 70: 6); እርሱ የሚረዳቸው መሸሸጊያቸው ነውና መዝ 10፡4)።

በሌሎች ትክሻ ላይ ተንጠላጥለው ያገኙትን ሐብት እንዳይነካ እና ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ መልኩ የጠጠበቀ ይሆን ዘንድ በማሰብ ማንኛውንም ዓይነት የግድግዳ መስመሮች መገንባት እና በሮችን ለመዝጋት በከንቱ እንደክማለን። በዚህ ዓይነት መንገድ ለዘላለም ልንጓዝ አንችልም። በነቢያት እንደተገለጸው "የእግዚአብሔር ቀን" (በአሞጽ 5:18፣ ኢሳ፡ 2-5፣ ኢዩሄል 1-3) በአገራት መካከል የተፈጠሩትን መሰናክሎች በማፈራረስ የጥቂት ሰዎች እብሪትን በብዙ ሰዎች ሕበረት ይተካዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እየገጠማቸው ያለው የማግለል ሁኔታ ለረጅም ጊዜ ሊቀጥል አይችልም። ጩኸታቸው በፍጥነት እየጨመረና መላውን ምድር ሊያዳርስ ይችላል። አባ ሚሪሞ ማዞላሪ የሚባሉ ካህን “ድሆች በፍትሕ መጓደል ላይ የማያቋርጥ ተቃውሞ አላቸው፣ ድሆች እንደ ባሩድ ዱቄት ናቸው፣ በእሳት ከተያያዙ ዓለም ይፈነዳል” ይሉ ነበር።

15 November 2020, 12:41