ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የጴንጤቆስጤ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባከበሩበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የጴንጤቆስጤ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባከበሩበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እኛ የተፈጠርነው የእግዚአብሔርን ህልሞች እውን ለማድረግ ነው አሉ!

የላቲን ስርዓተ አምልኮ ሊጡርጊያ በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የዓመቱ የመጨረሻ የሊጡርጊያ ሳምን እሁድ በሕዳር 13/2013 ዓ.ም ተክብሮ ማለፉ የሚታወቅ ሲሆን በዚሁ የዓመቱ የመጨረሻ የሊጡርጊያ ሳምንት ላይ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ ንጉሥ በዓል ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በተደረገ መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እኛ የተፈጠርነው የእግዚአብሔርን ህልሞች እውን ለማድረግ ነው ማለታቸው ተገልጿል።በእለቱ ቅዱስነታቸው ያደረጉትን ስብከት የጀመሩት ወጣቶች የተፈጠሩት የእግዚአብሔርን ሕልሞች እውን ለማደረግ መሆኑን የገለጹ ሲሆን ወጣቶች በተቻላቸው አቀም ይህንን የእግዚአብሔርን ሕልም እውን ለማደረግ የበኩላቸውን አስተዋጾ ማድረግ እንደ ሚጠበቅባቸው አክለው ገልጸዋል።

ወጣቶች በቤተክርስቲያን አማካይነት የእግዚአብሔር ህልሞች በዓለም ውስጥ እውን እንዲሆኑ በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ ያቀረቡት ቅዱስነታቸው አጋጣሚውን ተጠቅመው ወጣቶች በቤተክርስቲያን ውስጥ ያላቸውን ሚና በተገቢው መልኩ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በዓመቱ የስርዓተ አምልኮ ሳምንት ማብቂያ ላይ የሚከበረው ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ዓመታዊ በዓል የፍጥረታት ሕይወት እንዲሁ በጋጣሚ የተገኘ ነገር እንዳልሆነ፣ ነገር ግን ወደ አንድ መጨረሻ ግብ የሚያመራ፡ የታሪኮች እና የፍጥረታት ሁሉ ጌታ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ የመጨረሻ ግልጸት እንደ ሚያመራ የሚያሳይ ነው። የታሪኩ መደምደሚያ ዘለዓለማዊ መንግሥቱ ይሆናል ማለት ነው። በዮሐንስ ወንጌል 18፡33-37 ስለ ክርስቶስ መንግሥት፣ ስለ ኢየሱስ መንግሥት፣ ኢየሱስ በጌተሰማኒ ከታሰረ በኋላ ስለደረሰበት ውርደት ሁኔታ በመጥቀስ ያሳለፈውን ታሪክ ያመለክታል፣ "ታስሯል፣ ተሰድቧል፣ ተከሷል በኢየሩሳሌም ባለሥልጣናት ፊት ቀርቧል"። ከዚያም በኋላ ፖለቲካዊ ለሆነ ሥልጣን እና የአይሁድ ንጉሥ ለመሆን እንደ ሚፈልግ ተደርጎ በሮም አቃቤ ሕግ ፊት እንዲቆም ተደርጓል። ጲላጦስ ጥያቄውን በማቅረብ አስገራሚ የሆነ ምርመራ ማድረግ በጀመረበት ወቅት እርሱ ንጉሥ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ሁለት ጊዜ ይጠይቀዋል (ዮሐ 18፡33,37)።

ኢየሱስም በቅድሚያ “የእኔ ምንግሥት ከዚህ ዓለም አይደለችም” በማለት ይመልሳል። ከዚያን በኋላ ደግሞ “አንተ እንዳልከው ነኝ” በማለት ያረጋግጣል። ይህም ኢየሱስ በመላው ሕይወቱ ፖለቲካዊ ለሆነ ስልጣን ምንም ዓይነት ፍላጎት እንዳልነበረው ያሳያል።

ኢየሱስ በአምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሳ ብቻ 5ሺ የሚሆኑ ሰዎችን ከመገበ በኃላ በዚህ ተዓምር እጅግ በጣም ተደንቀው የነበሩ ሰዎች የሮማ መንግሥት ገርስሶ የእስራኤል መንግሥት እንዲገነባ ፈልገው እርሱን ልያነግሱት ፈልገው እንደ ነበረ እናስታውሳለን። ነገር ግን ለኢየሱስ መንግሥት ማለት ርዕዮተ ዓለም፣ ብጥብጥ እና መሳሪያ የታጠቀ ኃይል ማለት አይደለም። 5ሺ ሰዎችን በአምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሳ ከመገበ በኋላ ሕዝቡ ልያነግሡት በፈለጉ ወቅት እነርሱን ትቶ ወደ ተራራ የወጣው በዚሁ ምክንያት ነው (ዮሐ 6፡5-15) ። አሁን ለጲላጦስ መልስ ሲሰጥ ደቀ መዛሙርቱ እሱን ለመከላከል አልተዋጉም ነበር። “መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤ መንግሥቴስ ከዚህ ዓለም ብትሆን፥ ወደ አይሁድ እንዳልሰጥ ሎሌዎቼ ይዋጉልኝ ነበር፤ አሁን ግን መንግሥቴ ከዚህ አይደለችም” (ዮሐ. 18፡36) በማለት የመለሰውም በዚሁ ምክንያት ነው። ኢየሱስ ከፖለቲካው ኃይል በላይ እጅግ የላቀ የሆነ፣ በሰው ልጆች አማካይነት ሥልጣን ላይ ያልተቀመጠ መሆኑን ግልፅ ማድረግ ይፈልጋል። እርሱ ወደ ምድር የመጣው ኃይል ተጠቅሞ ዓለምን ለመግዛት ሳይሆን በፍቅር ስለእውነት ለመመስከር ነው። ይህም የቅዱስ ወንጌል ዋና መልእክት የሆነው “እግዚኣብሔር ፍቅር ነው” የሚለው መለኮታዊ እውነት ሲሆን እርሱ በዓለም ውስጥ የእርሱን የፍቅር፣ የፍትህ እና የሰለም መንግሥት ለመመስረት ነው የመጣው። እናም ይህ ኢየሱስ የነገሠበት እና እስከ መጨረሻው ዘመን የሚዘልቅ ነው። ከታሪክ እንደ ምንማረው በጦር መሳሪያ እና በምድራዊ ስልጣን ላይ  መሰርቱን በማድረግ የተገነባ መንግሥት በመጀመሪያ በቀላሉ ይበታተናሉ ቀጥሎም ብዙ ሳይቆይ ተዳክመው የፈራርሳሉ። ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት በፍቅር ላይ የተመሰረተ እና በልባችን ውስጥ ሥር መሰረት ያለው ነው፡ የእግዚኣብሔር መንግሥት በልባችን ውስጥ ሥሩን ይዘረጋል-ይህንን የሚቀበል ሰው ደግሞ ሰላምን ያገኛል፣ ነጻነትን ይጎናጸፋል ምልኣት ያለው ሕይወት ይኖራል። ሁላችንም ሰላምን እንፈልጋለን፣ ሁላችንም ነጻነት እንፈልጋለን፣ ሁላችንም ምልኣት ያለው ሕይወት እንፈልጋለን። ታዲያ ይህንን እንዴት ማግኘት እንችላለን? የእግዚአብሔር ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንግሥት፣ የኢየሱስ ፍቅር በልባችሁ ውስጥ ሥር እንዲሰድ ብታደርጉ ሰላም ታገኛላችሁ፣ ነጻነት ይኖራችኋል እንዲሁም ደስተኛ የሆነ ሕይወት ትኖራላችሁ።

ዛሬ ኢየሱስ እርሱ የሕይወታችን ንጉሥ ይሆን ዘንድ እንድንፈቅድለት ይጠይቀናል። በቃሉ፣ በመላካም አብነቱ፣ በመስቀል ላይ ተሰውቶ እኛን ከሞት ያዳነን ይህ ንጉሳችን የደጉን ሳምራዊ መንገድ እንድንከተል በማመልከት በጥርጣሬ ለተሞላው ሕይወታችን አዲስ የሕይወት ሕልውና ብርሃን በመስጠት ከፍርሃት ነጻ ሆንን እና በእየእለቱ ከሚገጥሙን ፈተናዎች ተላቀን እንድንኖር ይረዳናል። ነገር ግን እኛ የኢየሱስ መንግሥት ከዚህ ዓለም እንዳልሆነ ማስታወስ ይኖርብናል። አንዳንድ ጊዜ በስህተቶቻችንን እና በኃጢአቶቻችንን እንድንፈትሽ ጊዜ በመስጠት፣ የዓለምን እና የዓለም ምንግሥታት አምክንዮ  እንዳንከተል በማድረግ ህይወታችን አዲስ ትርጉም እንዲኖራት ያደርጋል።

ኢየሱስን የሕይወታችን ንጉሥ አድርገን እድንቀበል እና የእርሱ መንግሥት እንዲሰፋ ለማድረግ እውነት ለሆነው ለእርሱ ፍቅር ምስክርነት በመስጠት መኖር እንችል ዘንድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትረዳን አማላጅነቷን መማጸን ይኖርብናል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ያሰሙት ስብከት መሰረቱን ያደርገው በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል 25፡ 31-46 ላይ በተጠቀሰው “የሰው ልጅ ከመላአክቱ ሁሉ ጋር በክብሩ ሲመጣ፣ በክብሩ ዙፋን ላይ ይቀመጣል፤ ሕዝቦች ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እርሱም፣ እረኛ በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ፣ ሕዝቡን አንዱን ከሌላው ይለያል፤ በጎቹን በቀኙ፣ ፍየሎቹን ግን በግራው ያቆማቸዋል። በዚያን ጊዜ ንጉሡ በቀኙ እና በግራ በኩል ባሉት ሰዎች ላይ እንደ ሚፈርድባቸው” በሚገልጸው የመጨረሻው ቀን ፍርድ በሚያመልክተው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ ያጠነጠነ ስብከት እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የኢየሱስን የመጨረሻ ፍርድ አስመልክቶ በመነናገር ነበር ስብከታቸውን የጀመሩት።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ኢየሱስ ለእኛ ያለውን ፍቅር በመስቀል ላይ ከመግለጹ በፊት የመጨረሻ ምኞቱን ይናገራል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ንጉሡም “እውነት እላችኋለሁ፣ ለተጠማ ወይም ለተራበ፣ እንግድናን ለተቀበል፣ ለታረዘ፣ ለተቸገረ፣ ለታመመ ወይም በእስር ቤት ውስጥ የሚገኘውን ከእነዚህ አነስተኛ ከሆኑት ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት፣ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው’ በማለት እንደ መለሰላቸው ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን የምናደርገው ማነኛውም መልካም ነገር ለኢየሱስ እንደ ምናድርግ ይቆጠራል ብለዋል።

የእግዚአብሔርን ሕልሞች እውን ማድረግ

እነዚህን ስራዎች በተግባር ላይ እንዴት ማዋል እንደ ምንችል ሁላችንም እራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፣ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በመቀጠል “እኔ እዚህ ነኝ” በሚለው የኢየሱስ ቃላት ላይ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፣ መልካም ተግባራትን በምናከናውንበት ወቅቶች ሁሉ ኢየሱስ በእዚያ ይገኛል ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በተለይ ለወጣቶች ሲናገሩ “ታላላቅ ሕልሞችን ተስፋ ሳንቆርጡ እውን ማደረግ እንደ ሚጠበቅባቸው” የገለጹ ሲሆን  እኛ የተፈጠርነው “የእግዚአብሔርን ህልሞች በዚህ ዓለም እውን ለማድረግ ነው” በማለት ወጣቶችን አሳስቧቸዋል።

ትልቅ ምርጫ ማድረግ

ይህንን እውን ማድረግ እንችላለን በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስብከታቸውን የቀጠሉ ሲሆን “ታላቅ የሆኑ ምርጫዎችን” በማድረግ እውን ማድረግ እንደ ሚቻል አክለው ገልጸዋል። በእለቱ ወደ ተነበበው የቅዱስ ወንጌል ቃል በመመለስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የኢየሱስ ፍርድ እኛ በምናደርገው ምርጫ ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ሚሆን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በምርጫችን ላይ መሰረቱን ያደረገ ፍርድ እንደ ሚፈርድብን ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል። ጥላቻን እና ክፉ ነገርን ከመረጥን በጭራሽ ደስተኛ ልንሆን አንችልም፣ ነገር ግን “እግዚአብሔርን ከመረጥን በየቀኑ በፍቅር ውስጥ እናድጋለን እንዲሁም ሌሎችን ለመውደድ ከመረጥን እውነተኛ ደስታ እናገኛለን” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ስብከታቸው ሲቀጥሉ አክለው እንደ ገለጹት “ምርጫዎቻችንን ከባድ ሊያደርጉ የሚችሉ እንቅፋቶች” በተመለከተ የተናገሩ ሲሆን “ፍርሃት ፣ አለመተማመን ፣ ያልተመለሱ ጥያቄዎች” እነዚህ እና እነዚህን የመሳሰሉት ሁኔታዎች በምናደርገው ምርጫ ላይ ጫና እንደ ሚፈጥሩ ቅዱስነታቸው ጨምሮ ገልጸዋል። ነገር ግን እነዚህን መሰናክሎች ሁሉ እንድናልፍ የሚረዳን ፍቅር ብቻ እንደ ሆነ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የምኖረው ለምንድነው?” ከማለት ይልቅ “ለማን ነው የምኖረው?” ወደ ሚለው ሐስተሳሰብ እንድንሻገር የሚረዳን ፍቅር ብቻ ነው ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ስብከታቸውን ሲቀጥሉ እንደ ገለጹት “ሕይወትን መምረጥ” ማለት ተጠቅሞ መጣል ወይም የብክነት እና ሁሉኑም ነገር የመፈለግ ባሕልን ማስወገድ ማለት ነው፣ ሕይወታችንን ወደ መንግስተ ሰማያት ግብ የሚመሩ፣ የእግዚአብሔርን ሕልሞች እውን ለማደረግ የሚችሉ ምርጫዎችን” ማደረግ ይኖርብናል ብለውዋል።

ለእኛ የሚያዋጣውን ነገር መምረጥ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መልካም ተግባራትን ለማከናወን እና ደስተኛ ለመሆን ለሚጥሩ አንድ የመጨረሻ ምክር አክለው ተናግረዋል። የዕለት ተዕለት ምርጫዎችን በምንወስንበት ጊዜ እራሳችንን መጠየቅ ያለብን “ምን ማደረግ እንዳለብኝ የሚሰማኝ ስሜት ሳይሆን፣ ለእኔ የሚበጀው ምንድነው?” የሚለው ሊሆን እንደ ሚገባ በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ መንፈስ ቅዱስ በልቦች ውስጥ የሚያኖረው ጥያቄ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “ይህ ውስጣዊ ማስተዋል በአስቸጋሪ ምርጫዎች ወይም በሕይወታችን ላይ ለውጥ በሚያሳድሩ ውሳኔዎች ላይም ውጤት ሊያስገኝ ይችላል” በማለት የተናገሩ ሲሆን ወደ ኢየሱስ እንመልከት እና ለእኛ የሚበጀንን እንድንመርጥ ድፍረትን እንዲሰጠን እንለምነው። በፍቅር መንገድ እርሱን ተከተሉት በዚህ መንገድ ደስታ ይገኛልና ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው የእለቱን ስብከት አጠናቀዋል።

22 November 2020, 11:49