ፈልግ

የኢየሱሳዊያን የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም  ለስደተኛ ሕጻናት የትምህርት አገልግሎት ሲሰጥ የኢየሱሳዊያን የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ለስደተኛ ሕጻናት የትምህርት አገልግሎት ሲሰጥ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸሰኮስ የተረሱ ሰዎችን ድምጽ ለዓለም ማሰማይ ይገባል አሉ!

የኢየሱሳዊያን የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም  በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል JRS (Jesuit refuge service) የተመሰረተበትን 40ኛ ዓመት ባከበረበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት መልእክት የተረሱ ሰዎችን ድምጽ ለዓለም ማሰማት ተገቢ እንደ ሆነ መግለጻቸው ተዘግቧል።ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው እንደ ገለጹት በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለሚሰደዱ ስደተኞች ይህ የኢየሱሳዊያን የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም  በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል JRS (Jesuit refuge service) በአሁኑ ወቅት እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት አጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን ለብቻቸው ሁነው ለሚሰቃዩ እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለተለያዩ ስደተኞች የወዳጅነት እጅን መዘርጋት በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል።

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል ለሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ለሆኑት ለአባ ሪፓሞንቲ በጻፉት መልእክት ይህ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ስር የሚተዳደረው ተቋም ለስደተኞች እና ለጥገኝነት ጠያቂዎች ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያበረከተ ለሚገኘው አገልግሎት ምሳጋና ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን የእዚህ ተቋም “ተቀብሎ የማስተናገድ ባህል” መልካም ምሳሌ ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል ተግባር መሆኑን የገለጹ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከሚሰደዱ ሰዎች ጋር በጸሎቴ እና በፍቅር ለእነርሱ ቅርብ መሆኔን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል።

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው አመታዊ ሪፖርት “የታገዱ ህይወቶች” በሚል አርዕስት ስደተኞችን በተመለከተ ባወጣው ዘገባ እንደ ገለጸው በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የስደተኞችን እለታዊ እንቅስቃሴ እና የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚያግድ ወይም የሚዘገይ፣ እንዲሁም በዕለት ተዕለት ኑሮን ምክንያት  እየተናወጡ ስለሚገኙ ሰዎች እየደረሰባቸው ስላለው አለመረጋጋትን በተመለከተ የሚናገር ዘገባ እንደ ሆነም ተገልጿል። እ.አ.አ በ 2019 ዓ.ም በማዕከሉ 20 ሺህ ስደተኞች ከተቋሙ ጋር ኝኙነት ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ጨምሮ በሮሜ ከተማ ውስጥ ብቻ 11 ሺ ስደተኞች እንደ ነበሩ ተቋሙ በዘገባው አስፍሯል። እናም ይህ በቅርቡ ይፋ የሆነው መረጃ እንደሚገልጸው አስቸኳይ የሆነ እርምጃ ካልተወሰደ  “ስደተኞችን በተመለከተ ያለው ፖለቲካ፣ የሚጣሉ ገደቦች፣ ድበር መዝጋት የመሳሰሉ ጉዳዮች ከአሁኑ አግላይ ያልሆኑ ፍትሃዊ ውሳኔዎች ካልተወሰዱ በስተቀር መገለል እና መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎችን እንደ ሚያባብሱ፣ ይህም መላውን ማህበረሰብ ይበልጥ ተጋላጭ እንደ ሚያደርገው” ሪፖርቱ በስፋት ይገልጻል።

በወንድማማች ፍቅር ስደተኞችን መቀበል

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ዳይሬክተር ለሆኑት ለአባ ካሚሎ ሪፓማኖቲ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት መልእክት ላይ ሪፖርቱ ላይ የተጠቀሰውን “ይህ ጽህፈት ቤት በተለይም በዚህ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የስደተኞችን የጥገኝነት ጥያቄ መብት ለማስከበር በዚህ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት እያደረገው የሚገኘውን በትጋት ያታገዘ ተግባር” በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ያደነቁ እና ያመሰገኑ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጥገኝነት የማግኘት መብት እንዲያገኙ ተቋም በማስቻሉ አመስግነው ጦርነትን፣ ረሃብን፣ ከባድ የሆነ ሰባዊ ቀዎስን በመሸሽ ወደ ተለያዩ አገራት የሚሰደዱትን ስደተኞች ተቀብሎ ማስተናገዱን እንዲቀጥል ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው ገለጸዋል። በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ “ስደተኞችን” በተመለከተ ከሰጠው ትርጓሜ ጋር ከሞላ ጎደለ እንደ ሚስማሙ የገለጹ ሲሆን በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ሰራተኞች ለስደተኞች ትኩረት በመስጠት በወንድማማችነት ፍቅር እንዲቀበሏቸው ቅዱስነታቸው ጥሪ ያደረጉ ሲሆን እኔ በመንፈስ ለሁሉም ሰው ቅርብ ነኝ እናም በጸሎት እና በፍቅር ከእናንተ ጋር መሆኔን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ብለዋል። በሰዎች መካከል ሰላም፣ ፍትህ እና ቅንነት በሌለበት ዓለም ውስጥ እምነት እና ተስፋ እንዲኖር ማድረግ  ተገቢ ነው በዋል። ፡፡

የአንድነት ምሳሌ

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ማቢቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደለጹት “እናተ እያከናወናችሁት የምትገኙት በጎ ተግባር በዓለም ውስጥ እውነተኛ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እና የእንግዳ መቀበል ባህል እንዲኖር ቁርጠኝነትን ሊያነቃቃ ይችላል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

13 November 2020, 11:59