ፈልግ

በሀሪከዮን አውሎ ነፋስ የተጠቃው የሁዱራስ መንደር በሀሪከዮን አውሎ ነፋስ የተጠቃው የሁዱራስ መንደር  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በአደገኛ አውሎ ነፋስ ለተመታው ለመካከለኛው አሜሪካ ሕዝቦች ጸለዩ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕዳር 20/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለው ጸሎት ከተደገመ በኋላ ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በቅርቡ በተከሰተው ጠንካራ አውሎ ነፋሶች ለተመታዉ ለመካከለኛው አሜሪካ ህዝብ ያለኝን ቅርበት ለመግለጽ እፈልጋለሁ ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን በተለይም የቅዱስ እንድሪያስ፣ የሳንታ ካታሊና ደሴቶች እንዲሁም የሰሜን ኮሎምቢያ የሰሜን የፓስፊክ ዳርቻዎች በእዚህ የተፈጥሮ አደጋ በመጠቃታቸው ልናስታውሳቸው ይገባል፣ በእነዚህ አደጋዎች ምክንያት ለሚሰቃዩት ሀገሮች ሁሉ እፀልያለሁ ብለዋል።

ለሮም ከተማ እና ከተለያዩ ሀገራት ለመጡ ምዕመናን ለእናንተ ሞቅ ያለ ሰላምታዬን አቀርብላችኋለሁ በማለት በሳምንታዊ መልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በቅርቡ የካርዲናልነት ማዕረግ ለተቀበሉ 13 ካርዲናሎች እንጸልይላቸው ብለዋል።

ለሁላችሁም የተባረከ እለተ ሰንበት እና መልካም የስብከተ ገና ወቅት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ በማለት በመልክእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ወረርሽኙ በእኛ ላይ ከሚያስከትለው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳን መልካም የሚባሉትን ነገሮች ለማውጣት እንሞክር፣ የበለጠ ጨዋነት ፣ አስተዋይ እና ለሌሎች ሰዎች  ችግሮች ተገቢውን ቦታ በመስጠት በቤተሰብ ውስጥ ችግር ላለባቸው ሰዎች በመጸለይ ይህንን የስብከተ ገና ወቅት በመንፈሳዊነት ልንጓዘው ይገባል፣ ይህንንም ለመተግበር የበለጠ ጨዋነት፣ ብልህነት እና ለሌልች ሰዎች ፍላጎቶች ትኩረት መስጠት የተሰኙት እነዚህ ሶስት ነገሮች በጣም ይረዱናል ካሉ በኋላ እንደ ተለመደው “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ሳምንታዊውን መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

29 November 2020, 12:01