ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ቤተ መጽሐፍት ውስጥ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ጸሎት የሕወታችን አቅጣጫ መሪ መሳሪያ ነው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘውትር ረቡዕ እለት በቫቲካን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በዛሬው እለት ማለትም በጥቅምት 258/2013 ዓ.ም ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከዚህ ቀደም በብሉይ ኪዳን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ጀምረውት ከነበረው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን የሕወታችን አቅጣጫ መሪ መሳሪያ ነው ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደሚከተለው አሰናድተነዋል፣ ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ኢየሱስ ምዳርዊ ሕይወቱን በይፋ መኖር በጀመረበት ወቅት ሁል ጊዜም የጸሎትን ኃይል ይጠቀም ነበር። እየሱስ ወደ ገለልተኛ ስፋራዎች በመሄድ በእነዚያ ስፍራዎች እንደ ነበረ ቅዱሳን ወንጌላዊያን ይገልጻሉ። እነዚህ በጣም ወሳኝ የሆኑና አስተዋይ ምልከታዎች ናቸው ፣ እነዚያን የጸሎት ሁኔታዎች በዓይነ ሕሊናችን ለመመልከት ያስችሉናል። እነሱ በግልጽ የሚያሳዩት ለድሆች እና ለታመሙ ሰዎች ኢየሱስ የበለጠ ቦታ በሚሰጥበት ጊዜያት እንኳን ኢየሱስ ከአብ ጋር ያለውን የጠበቀ ውይይት በጭራሽ እንደማይረሳ ነው። የሰዎችን ችግሮች ለመፍታት በሚሰራበት ወቅት ወደ ቅድስት ስላሴ፣ ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ወደ አለው ሕብረት መመለሱ አስፈላጊ መሆኑን እርሱ ይስማማበታል። 

ስለዚህ በኢየሱስ ሕይወት ውስጥ ከሰው ዓይኖች የተደበቀ ምስጢር አለ ፣ ይህም አንድ የተደበቀ ኃይል ወይም አካል እንዳለ ያሳያል። የኢየሱስ ጸሎት ሚስጥራዊ እውነታ ነው ፣ እኛ ትንሽ ውስጣዊ ግንዛቤ አለን ፣ ግን መላውን ተልእኮውን በትክክለኛው አተያይ ለመተርጎም ያስችለናል። በእነዚያ በብቸኝነት ሰዓታት ውስጥ - ጎህ ከመቅደዱ በፊት ወይም ማታ - ኢየሱስ ከአብ ጋር ባለው ቅርርብ ማለትም እያንዳንዱ ነፍስ በሚጠማው ፍቅር ውስጥ እራሱን ያስገባል። ይፋዊ የሆነ አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ባሉት የመጀመሪያዎቹ ቀናት ውስጥ የሚታየው ይህ ነው።

ለምሳሌ አንድ ሰንበት ፣ የቅፍርናሆም ከተማ ወደ አንድ “የሜዳ ላይ ሆስፒታልነት” ተለውጦ ነበር፣ ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ የታመሙትን ሁሉ ወደ ኢየሱስ አመጡ እርሱም ፈወሳቸው ፡፡ ሆኖም ጎህ ከመቅደዱ በፊት  ኢየሱስ ተሰወረ፣ ወደ አንድ ብቸኛ ስፍራ ፈቀቅ ብሎ ጸለየ ፡፡ ስሞን ጴጥሮስ እና ሌሎቹ ይፈልጉት ነበር፣ ሲያገኙትም “ሰዉ ሁሉ ይፈልግሃል” አሉት። ኢየሱስ እንዴት መለሰ? “እርሱም፣ “ከዚህ ተነሥተን በአቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች እንሂድ፤ እዚያም ልስበክ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና” አላቸው (ማርቆስ 1፡35)። ኢየሱስ ሁልጊዜ ከእዚያ ባሻገር ይሄዳል፣ ከአብ ጋር በጸሎት ይገናኛል፣ ወደ ሌሎች መንደሮች ፣ ሌሎች አድማሶች ሄዶ ለሌሎች ሰዎች ለመስበክ ሁል ጊዜ ትንሽ ወደ ፊት ይጓዛል።

ጸሎት የኢየሱስን አካሄድ የሚመራው አቅጣጫ ተቋሚ መሳሪያ ነበር ፡፡ የእርሱ ውጤታማ ተግባር፣ መግባባትን ከግምት በማስገባት “ሁሉም ሰው ይፈልግሃል” ብሎ መናገራቸው የሚያማልል ቃል ሳይሆን ነገር ግን የተልእኮው ደረጃዎች ያዘዘውን ቁም ነገር ያሳያል። ኢየሱስ የመረጠው መንገድ ምቹ የነበረ መንገድ ሲሆን ነገር ግን ኢየሱስ በብቸኝነት ባደረገው ጸሎቱ የሰማውን እና የተቀበለውን የአባቱን መነሳሳት የታዘዘበት ነው።

ይህንን በተመለከተ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ “ኢየሱስ ሲጸልይ እርሱ እንዴት መጸለይ እንደ ሚገባን አስቀድሞ ያስተምሮናል” (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁጥር 2607) በማለት ይገልጻል። ስለዚህ ከኢየሱስ ምሳሌ እኛ የክርስቲያን ጸሎት አንዳንድ ባህሪያትን ማግኘት እንችላለን።

በመጀመሪያ እና በዋነኝነት እርሱ ለጸሎት ቅድሚያ ይሰጣል፣ የእለቱ የመጀመሪያ ምኞት ጸሎት ነው ፣ ዓለም ከመነቃቱ በፊት ጎህ ሳይቀድ የሚያደርገው ነገር ነው። ያለበለዚያ ነፍስ እስትንፋስ የሌላት ትሆናለች ። ያለጸሎት የተጀመረ አንድ ቀን በአደጋዎች እና አስጨናቂ በሆኑ ነገሮች የተሞላች ትሆናለች፣ ወይም አሰልቺ በሆኑ ተመክሮዎች የተሞላች ትሆናለች፣ በእኛ ላይ የሚደርሰው ሁሉ ወደ መጥፎ ጽናት እና ጭፍን ወደ ሆነ ዕጣ ፈንታ ሊለወጥ ይችላል። ይልቁን ኢየሱስ እውነተኛ መታዘዝን ያስተምራል፣ ይህም ማዳመጥ ነው። ጸሎት በዋነኝነት እግዚአብሔርን ማዳመጥ እና መገናኘት ነው ፡፡ ስለሆነም የዕለት ተዕለት የኑሮ ችግሮች እንቅፋት አይሆኑም፣ ነገር ግን ከፊት ለፊታችን ያሉትን ነገሮች ለማዳመጥ እና ከእግዚአብሄር ራሱ ጋር ለመገናኘት እንችል ዘንድ መንገዱን ይከፍትልናል። ስለዚህ የሕይወት ፈተናዎች ወደ መልካም እድል እና ወደ የበጎ አድራጎት ተግባራት እንዲያድጉ ወደ ዕድሎች ይቀየራሉ። የዕለት ተዕለት ጉዞዋችን አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ጨምሮ “የጥሪ” ዕይታን ያገኛል። በዚህ ምክንያት ጸሎት በሕይወት ውስጥ  አስቸጋሪ የሆኑትን ነገሮች ወደ ጥሩ የመለወጥ ኃይል አለው ፤ ጸሎት አእምሮን የመክፈት እና ልብን ወደ ታላቅ አድማስ የማስፋት ኃይል አለው። 

በሁለተኛ ደረጃ ፀሎት በፅናት ሊተገበር የሚችል ጥበብ ነው ፡፡ ኢየሱስ ራሱ እንዲህ ይለናል-አንኳኩ ፣ አንኳኩ ፣ አንኳኩ ይለናል። እኛ አልፎ አልፎ ከአፍታ ስሜታዊነት በመነሳት የሚደረጉ ጸሎቶችን የማድረግ ችሎታ አለን፣ ነገር ግን ኢየሱስ ሌላ የጸሎት ዓይነት ያስተምረናል-በሕይወት ደንብ ውስጥ ሥነ-ስረዓት ያለውን፣ የሕወታችንን አቅጣጫ የሚወስነውን ዓይነት ጸሎት ያስተምረናል። የማያቋርጥ ጸሎት በደረጃ ለውጥን ያስገኛል ፣ በመከራ ጊዜያት ጠንካራ ያደርገናል ፣ በሚወደን እና ሁልጊዜ በሚጠብቀን በእርሱ እንድንደገፍ ጸጋን ይሰጠናል።

የኢየሱስ ጸሎት ሌላው ዓይነተኛ ባሕርይ ደግሞ ብቸኝነት ነው። የሚጸልዩ ሰዎች ከዓለም ውጪ ሊሆኑ አይችሉም፣ ነገር ግን በረሃማ ቦታዎችን ይመርጣሉ። እዚያ በዝምታ ውስጥ በምንሆንበት ወቅት እጅግ ብዙ ድምጾች ሊሰሙ ይችሉ ይሆናል፣ ብዙ የዓለም ድምጾች ያስተጋቡ ይሆናል፣ የምንጫናቸው እውነተኛ የሆኑ ባሕሪያት ሊኖሩን ይችል ይሆናል. . .ወዘተ። በእዚያ ሁኔታ በዝምታ ውስጥ በምንሆንበት ወቅት ከሁሉም በላይ በዝምታ እግዚአብሔር ይናገራል። ድርጊቶች ትርጉም የሚሰጡበት ውስጣዊ ሕይወትን ማጎልበት እንዲችል እያንዳንዱ ሰው ለእርሱ ማለትም ለእግዚአብሔር ቦታ እንዲሰጥ እርሱ ይፈልጋል። ውስጣዊ ሕይወታችንን እንድናጎለብት እርሱ ይፈልጋል። ያለ ውስጣዊ ሕይወት አጉል ፣ ተበሳጭ እና ጭንቀታም እንሆናለን - ጭንቀት እንዴት ይጎዳናል! እኛ መጸለይ የሚገባን እና ያለብን ለዚህ ነው፣ ያለ ውስጣዊ ሕይወት ከእውነታው እንሸሻለን ፣ ከራሳችን እንሸሻለን።

በመጨረሻም የኢየሱስ ጸሎት ሁሉም ነገር ከእግዚአብሄር እንደሚመጣ እና ወደ እርሱ እንደሚመለስ የምናውቅበት ስፍራ ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኛ የሰው ልጆች እኛ የሁሉም ነገር ጌቶች እንደሆንን እናምናለን ፣ ወይም በተቃራኒው እኛ ለራሳችን ያለንን ግምት ሁሉ እናጣለን ፣ ከአንድ ወገን ወደ ሌላው እንሄዳለን ፡፡ ጸሎት ከእግዚአብሄር ፣ ከአባታችን እና ከፍጥረት ሁሉ ጋር ባለን ግንኙነት ውስጥ ትክክለኛውን ልኬት እንድናገኝ ይረዳናል ፡፡ እናም የኢየሱስ ጸሎት በወይራ አትክልት ስፍራ እንዳደርገው በዚያ ጭንቀት ውስጥ እራስን በአብ እጅ አሳልፎ መስጠት ማለት ነው “አባቴ ሆይ የሚቻልህ ከሆነ . . .  ነገር ግን የአንተ ፈቃድ ይሁን” ማለትን ያመለክታል። በአብ እጅ ራስን አሳልፎ መስጠት መልካም ነው። በተበሳጨን ቁጥር፣ ትንሽ ስንጨነቅ መንፈስ ቅዱስ ከውስጣችን ይለውጠናል እናም እርሱ በአብ እጅ እራሱንአሳልፎ መስጠቱ “አባት ሆይ ፣ ፈቃድህ ይከናወን” ዘንድ እንዳለው ራሳችንን ለኢየሱስ አሳልፈን መስጠት ይኖርብናል።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች ፣ ኢየሱስ ክርስቶስን በወንጌል ውስጥ የፀሎት አስተማሪ እንደ ሆነ እንወቅ እና እራሳችንን በእሱ ትምህርት ውስጥ እናስገባ። በዚህ ሁኔታ ደስታ እና ሰላም እንደምናገኝ አረጋግጥላችኋለሁ።

 

04 November 2020, 20:44