ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ እና ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተለሜዎስ አንደኛ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ እና ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ በርተለሜዎስ አንደኛ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፥ “የቅዱስ እንድርያስ ቸርነት የመከራ ጊዜ ምርኩዛችን ነው” አሉ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የክርስቲያኖች አድነት ባልደረባ የሆነው የቅዱስ እንድርያስ ዓመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቤርተለሜዎስ አንደኛ መልዕክት ልከዋል። ቅዱስነታቸው ለፓርቲያርክ ቤርተለሜዎስ አንደኛ በላኩት መልዕክታቸው፣ የቅዱስ እንድርያስ ቸርነት፣ ሐዋርያዊ ቅንዓት እና ጽናት ዛሬ ለምንገኝበት አስቸጋሪ ዘመን የብርታት ምንጭ ሆኖ መገኘቱን አስረድተዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም ለእግዚአብሔር ምስጋናን ማቅረብ በእምነት እንድንበረታ፣ በከባድ የችግር ጊዜ ለዘለዓለማዊ ሕይወት በበቃው በሰማዕቱ ቅዱስ እንድርያስ ተስፋን እንድናደርግ ያግዘናል ብለዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 20/2020 ዓ. ም. በሮም ከተማ በተካሄደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ከሌሎች የሐይማኖት መሪዎች ጋር ሆነው የቆንስጣንጥንያው ጳጳስ ብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቤርተለሜዎስ አንደኛ መገኘታቸውን በደስታ አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዓለማችንን ያጋጠማት ተግዳሮቶች

ዓለማችንን ካጋጠማት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተዳምሮ ጦርነትም በርካታ የዓለማችንን ክፍሎች ለስቃይ መዳረጉን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተከሰቱ የመጡት አመጾች ጾታን ሳይለይ የበርካታ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ መሆኑን ገልጸዋል። ሰላምን ለማምጣት ተብሎ በተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በኩል የተደረጉት ጥረቶች ጠቃሚ እና አስፈላጊ እንደነበሩ ገልጸው፣ ቢሆንም ሕዝቦች በሙሉ የጋራ ሃላፊነትን ተቀብለው የወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን ባሕርይ ካልተላበሱ በቀር ግጭት እና አመጽ ሊወገድ አይችልም ብለዋል።

የአብያተ ክርስቲያናት መልካም ምሳሌነት

አብያተ ክርስቲያናት ሌሎች ሃይማኖታዊ ባሕሎችን በመጠቀም የጋራ ውይይቶችን፣ እርስ በእርስ መከባበርን እና በተግባር የሚታይ ኅብርትን ማሳየት ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል። ቅዱስነታቸው በተጨማሪም “በሃይማኖቶች መካከል የተፈጠረውን ወንድማማችነት በግልጽ ለመመልከት በመቻሌ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው” ብለዋል።

ወደ ሙሉ አንድነት የሚወስድ መንገድ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለብጹዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ቤርተለሜዎስ አንደኛ በላኩት መልዕክታቸው፣ በክርስቲያኖች መካከል መቀራረብ እና መግባባት እንዲኖር፣ ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም በመካከላቸው የጋራ ውይይትን እንዲያደርጉ የሚል መልካም ፍላጎት በቅድሚያ የታየው በቆንስጣንጥንያው ቤተክርስቲያን በኩል መሆኑን ገልጸው፣ ይህንንም በግልጽ ማየት የምንችለው ከመቶ ዓመት በፊት የክርስቲያኖች ውሕደት ለማበረታታት የተጻፈው የቅዱስ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ መልዕክት መኖሩን አስታውሰው ይህም ዛሬ ለምናደርገው ጥረት እጅግ ጠቃሚ ሆኖ መገኘቱን አስርድተዋል። በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን እና በቆንስጣንጥንያው ቤተክርስቲያን መካከል ያለው ግንኙነት ባለፈው ክፍለ ዘመን ውስጥ እጅግ እያደገ በመምጣቱ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን ብለው በሁለቱ ዓብያተ ክርስቲያናት መካከል የሚታዩ መሰናክሎች ተወግደው ሙሉ አንድነትን በመፍጠር በጋራ መንበረ ታቦት ላይ ለመቆም ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል። ለውህደት በምናደርገው ጉዞ ውስጥ አሁንም መሰናክሎች ቢኖሩም እርስ በእርስ በመዋደድ፣ ሰነ-መለኮታዊ ውይይቶችን በማካሄድ ወደ ግብ ለመድረስ ተስፋ እንዳላቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ገልጸዋል።

በክርስቶስ ላይ የጋራ እምነትን መገንባት

ለውህደት የምናደርገው ጉዞ፣ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሁሉም ሰው ወደ እርሱ እንዲቀርብ በፈለገው በእግዚአብሔር አብ ባለን የጋራ እምነትን ነው ካሉ በኋላ ለቅድስት ቤተክርስቲያን የማዕዘን ራስ፣ የእግዚአሔር ቤተ መቅደስ በመሆን፣ ሁላችንም እንደ ጥሪያችን መሠረት አገልግሎታችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ በመልዕክታቸው ገልጸዋል።

30 November 2020, 19:12