ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለወጣቶች-ክርስቶስ እንደሚኖርና እንደሚነግስ በሕይወታችሁ መስክሩ አሉ!

የላቲን ስርዓተ አምልኮ ሊጡርጊያ በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የዓመቱ የመጨረሻ የሊጡርጊያ ሳምን እሁድ በሕዳር 13/2013 ዓ.ም ተክብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ የዓመቱ የመጨረሻ የሊጡርጊያ ሳምንት ላይ ክርስቶስ የዓለም ሁሉ ንጉሥ በዓል ተክብሮ ማለፉ ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ይህ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በተደረገ መስዋዕተ ቅዳሴ ተከብሮ ማለፉን ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ከመስዋዕተ ቅዳሴው በመቀጠል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የሀገር ጎብኝዎች በተገኙበት በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት “የእግዚኣብሔር መልኣክ ማሪያምን አበሰራት” የሚለው ጸሎት ከተደገመ በኋላ ቅድስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በመጭው የአውሮፓዊያኑ 2021 ዓ.ም መግቢያ ላይ በአገረ ስብከት ደረጃ የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እንደ ምክበር የገለጹ ሲሆን ወጣቶች ክርስቶስ እንደሚኖርና እንደሚነግስ በሕይወታችሁ መስክሩ ማለታቸው ተገልጿል።

ቅዱስነታቸው የክርስቶስ የዓለም ንጉሥ ዓመታዊ በዓል በቫቲካን ከተከበረ በኋላ ባስተላለፉት መልእክት  በአገረ ስብከት ደረጃ በሆሳህና በዓል ላይ ይከበር የነበረው የዓለም  የወጣቶች ቀን ክርስቶስ የዓለም ንጉሥ በዓል በሚከበርበት ቀን ላይ እንዲከበር መወሰናቸውን ገልጸዋል።

ክርስቶስ በማዕከሉ

ቅዱስ አባታችን ለውጡን ሲያሳውቁ የዓለም አቀፍ የወጣቶች በዓል “የእዚህ በዓል አነሳሽ እና ደጋፊ የነበሩት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አፅንዖት እንደሰጡት የበዓሉ ማዕከል የሰው ልጅ ቤዛ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ ምስጢር ሆኖ ይቀጥላል” ብለዋል።

ሀገረ ስብከቶች በየሁለት ወይም ሦስት ዓመቱ ርእስ ሊቀ ጳጳሱ በመረጡት ቦታ ከሚከናወነው በዋናው አህጉራዊ የዓለም የወጣቶች ቀን መካከል በሚገኙ ጊዜያት ውስጥ በአገረ ስብከት ደረጃ የሚከበር የዓለም የወጣቶች ቀን መሆኑም ይታወቃል። “እነሆኝ  የጌታ ባሪያ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ ” (ሉቃ 1፡38) በሚል መሪ ቃል 34ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም በፓናማ በተለያዩ ደማቅ ዝግጅቶች ተከብሮ ማለፉ የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በስፍራው ተገኝተው ባደረጉት ንግግር “እውነተኛ ፍቅር ልዩነትን አያስወግድም፣ ነገር ግን አንድነትን ያጠናክራል” ማለታቸው ይታወሳል። እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ እ.አ.አ በ2020 ዓ.ም 35ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን “ማርያም በፍጥነት ተነስታ ሄደች” (ሉቃ 1፡39) በሚል መሪ ቃል በፖርቱጋል ዋና ከተማ በሊዝቦን እንዲከበር ቀን ተቆርጦለት የነበረ ሲሆን ነገር ግን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ወደ 2023 ዓ.ም መዛወሩ ተገልጿል።

ክርስቶስ ንጉሥ መሆኑን ጮክ ብላችሁ ግለጹ።

ቀደም ባሉ ጊዜያት ውስጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ይህንን የዓለም የወጣቶች ቀን በማስመልከት ባስተላለፉት መልእክት “አንተ ወጣት ተነሥ እልሃለሁ!” (ሉቃስ 7፡14) እና እ.አ.አ. በ2021 ዓ.ም “አሁንም ተነሣና በእግርህ ቁም፤ ስለ እኔ ስላየኸውና ምስክር እንድትሆን ልሾምህ ተገልጬልሃለሁ”(ሐዋ. 26፡16) በሚሉት ጥቅሶች ላይ እንድታስተነትኑ እፈልጋለሁ ማለታቸው ይታወሳል።

እንደምትመለከቱት “ተነስ” ወይም “ቁም” የሚለው ግስ በሦስቱም ጭብጦች ውስጥ ይታያል። እነዚህ ቃላት ደግሞ ስለ ትንሣኤ፣ ስለ አዲስ ሕይወት መነቃቃት ይናገራሉ። እ.አ.አ. በ2018 ዓ.ም የተካሄደው ሲኖዶስ ካበቃ በኋላ ከወጣቶች ጋር ተገናኝቼ ከተነጋገርኩኝ በኋላ በወጣው የመጨረሻው ሰነድ ላይ ቤተክርስቲያን በህይወታችሁ ጎዳና ላይ ብርሃን የሚፈነጥቅ መብራት እንደ ሆነ የሚያመለክቱ እነዚህ ቃላት በሰፊው የተንጸባረቁበት በላቲን ቋንቋ “Christus Vivit” በአማርኛው “ክርስቶስ ሕያው ነው!” በሚል አርእስት የተጻፈ እንድ ቃለ ምዕዳን ይፋ መሆኑ ይታወቃል።  መላው ቤተክርስቲያን ወደ ሌዝቦን የምታደርገው ጉዞ እነዚህን ሁለት ሰነዶች ለመተግበር እና ለወጣቶች ሐዋርያዊ የሆነ እንክብካቤ መስጠት ላይ የተሰማሩትን ሰዎች ተልእኮ ለመምራት ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚያደርግ ተስፋ አለኝ ማለታቸው ይታወሳል።

22 November 2020, 11:51