ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ የተስፋ ወኪሎች ያደርገናል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ 10ኛ ዓመታዊ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ ፌስቲቫል ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልእክት ማሕደረ ትውስታን ፣ ምስጢረ ጥምቀትን እና ተስፋን ማግኘት አስፈላጊነት ላይ ጎላ አድርገው ገልፀዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እ.ኤ.አ. ከሕዳር 26 – 29 ዓ.ም ድረስ በጣሊያን ቬሮና ተብሎ በሚታወቀው ክፍለ አገር ውስጥ እየተካሄደ ለሚገኘው አስረኛው የቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ ዓመታዊ ፌስቲቫል ሐሙስ ሕዳር 18/2013 ዓ.ም ለተሳታፊዎች የቪዲዮ መልእክት አስተላልፈዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በፌስቲቫሉ ላይ በአካልና እንዲሁም በኢንተርኔት አማካይነት በተለያዩ የማሕበራዊ የመገናኛ መረቦች አማካይነት ፌስቲቫሉን እየተከታተሉ ለሚገኙት ሁሉ የእንኳን ደህና መጣችሁ ሰላምታቸውን ባቀረቡበት መልእክታቸው ላይ ቅዱስነታቸው አክለው እንደ ገለጹት የፌስቲቫሉ አዘጋጆች “በስሜታቸውና በድርጊታቸው የሚለያዩ ፣ ግን የጋራ ጥቅምን ለመገንባት በሚሰበሰቡ ሰዎች” መካከል መገናኘት እንዲኖር የሚያደርግ ፌስቲቫል በማዘጋጀታቸው ቅዱስነታቸው መደሰታቸውን አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህ ዓመት ክብረ በዓል ልዩ ሁኔታ ላይ ትኩረት በማድረግ ቀጣዩን የጤና ቀውስ በማጉላት "ከባድ የግል እና ማህበራዊ ቁስሎችን" ባስከተለው በእዚህ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽ ላይ ትኩረታቸውን አድርገዋል።

በተጨማሪም በካቲት 2020 ዓ.ም ላይ ከእዚህ ዓለም በሞት የተለዩ የቀደሙትን ዘጠኝ ፌስቲቫሎችን ያዘጋጁ እና አነቃቂ የነበሩ አባ አድሪያኖ ቪንቴንዚን በመልእክታቸው አስታውሰዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የአባ ቪንቼንዚን አገልግሎት በማስታወስ “ፍሬዎቻቸው በሌሎች የሚሰበሰቡባቸው” ሂደቶችን የማስጀመር ልዩ ባህርያቸውን በማድነቅ በተዘራው መልካም ምስጢር ኃይል ውስጥ ዘወትር ሲታወሱ እንደ ሚኖሩ ገልጸዋል።

መታሰቢያ እና መጽዓይ ጊዜ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የዘንድሮው ፌስቲቫል መሪ ሐሳብ “የወደፊቱ መታሰቢያ” የተሰኘው እንደ ሆነ የገለጹ ሲሆን “የወደፊቱን ለመጎብኘት” የሚያስችል መንገድ እንዲፈጠር እያንዳንዱን ሰው ወደ የፈጠራ አስተሳሰብ እንዲመጣ ጋብዘዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አክለው እንደ ገለጹት ለክርስቲያኖች “መጪው ጊዜ ስም አለው ይህ ስም ደግሞ ተስፋ ነው” ብለዋል።

ተስፋ እና የልብ በጎነት

“ተስፋ” ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳብራሩት “በጨለማ ራሱን የማይዘጋ የልብ በጎነት” ነው በማለት የተናገሩ ሲሆን ተስፋ ቀደም ሲል በነበሩ ነገሮች ውስጥ ተዘፍቆ አይቀርም፣ የአሁኑን ጊዜ ብቻ አይኖርም ፣ ነገር ግን “ነገን እንዴት ማየት” እንደሚቻል ተስፋ በሚገባ ያውቃል ብለዋል። “ነገ ለክርስቲያኖች የተዋጀ ሕይወት ሆነ - ከቅድስት ሥላሴ ፍቅር ጋር የመገናኘት ስጦታ ደስታ ነው” ብለዋል።

ከዚህ አንፃር ቤተክርስቲያን መሆን ማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትቱ እንደ ገለጹት “እውነተኛ መንፈሳዊ በሽታ” ብለው የገለጹትን በትዝታ ውስጥ የመኖር ፈተና በማስወገድ ስነ-መለኮታዊ-ተኮር አመለካከት መኖር ማለት ነው ብለዋል።

ያለፈው ጊዜ ትዝታ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተጨማሪ ማብራሪያ ሲሰጡ እንዳረጋገጡት የክርስቲያን ተለዋዋጭ እንቅስቃሴ ያለፈውን ጊዜ በናፍቆት ለመያዝ ብቻ ሳይሆን “የበጎ አድራጎት ሕይወት” በመኖር የአብን ዘላለማዊ ትዝታ ለመዳረስ መስራት ይኖርበታል ብለዋል። ምናባዊ አስተሳሰብን በስፋት ይጠቀም የነበረው እንደ ራሺያዊው ኢቫኖቪች ኢቫኖቭ ገለፃ ይህ የሆነበት ምክንያት በእውነት እውን የሚሆነው ነገር ቢኖር እግዚአብሔር የሚያስታውሰው ነገር ብቻ ስለሆነ ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስረድተዋል ፡፡

ስለሆነም በተፈጥሮ የሰው ልጅ ጥልቅ ልኬቶች አንዱ የሆነውን ከፍቅር እና ከልምድ ጋር የተቆራኘ ማህደረ ትውስታ ሊኖረን ይገባል እንጂ በማህበራዊ፣ በፖለቲካዊ እና በምሁራዊ ዘርፎች “ፈጠራን የሚያግድ እና ግትር እና ሀሳባዊ ሰዎች እንድንሆን የሚያደርገን” ትውስታ ማስወገድ እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ምስጢረ ጥምቀት፣ ሕይወት እና ትውስታ

ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ሁላችንም በጥምቀት ሕይወት ተፈጠርን ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አረጋግጠዋል። እኛ “ከእግዚአብሄር ጋር ፣ ከሌሎች እና ከፍጥረት ሁሉ ጋር ህብረት ያለውን ሕይወት በስጦታ ተቀብለናል፣ ሕይወታችን እርሱ ራሱ የክርስቶስ ሕይወት ነው” ፣ እናም የእርሱን ሕይወት በእኛ ሕይወት ውስጥ እስካልገለጥን ድረስ በዓለም ውስጥ እንደ እውነተኛ አማኝ ሁነን መኖር አንችልም” ብለዋል።

ስለዚህ ወደ ቅድስት ሥላሴ ፍቅር ሕይወት ውስጥ ስንገባ የእግዚአብሔር መታሰቢያ የሆነውን  የማስታወስ ችሎታን እናገኛለን፣ ፍቅር የሆነው በአብ ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ ውስጥ ፍቅር ስለሚገኝ መልካም የሆኑ ነገሮችን የማስታወስ ችሎታችን ከፍ ይላል ብለዋል። በዚህ መንገድ መላ ሕይወታችን በሥርዓተ አምልኮ መንገድ ላይ የሚጓዝ ይሆናል፣ የክርስቶስ ፋሲካ ዘላለማዊ መታሰቢያ” የሆነውን ሕይወት ለመኖር እንችላለን ብለዋል።

እንደ አማኞች መኖር

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የወደፊቱን መታሰቢያ በሕይወት መኖር ቤተክርስቲያኗ “በምድር ላይ የእግዚአብሔር መንግሥት መጀመሪያ እና ዘር” እንድትሆን እራሳችንን መወሰን ነው ብለዋል። ይህ ማለት አማኞች በኅብረተሰብ ውስጥ ሰርገው መኖር ይኖርባቸዋል ማለት ነው፣ በተመሳሳይ መልኩም “በምስጢረ ጥምቀት የተቀበለውን የእግዚአብሔርን ሕይወት ማሳየት ፣ ከአብ ፣ ከወልድ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አብረን የምንሆንበትን የወደፊቱን ሕይወት እንኳን አሁን በማስታወስ መኖር ማለት ነው” በማለት ተናግረዋል ፡፡ በዚህ መንገድ ፣ የወንጌልን አዋጅ ወደ ተራ የህብረተሰብ አድማስ፣ ኢኮኖሚያዊ ንድፈ ሀሳቦች ወይም የፖለቲካ ቡድኖች አመለካከት ለማውረድ የሚደርገውን ተምኔታዊ ወይም ፍጹም የሆነ አስተሳሰብ ፈተና ማሸነፍ እንችላለን ብለዋል።

የሰዎችን ልብ ለመማረክ እና ዓይኖቻቸውን ወደ ኢየሱስ ወንጌል ለመምራት በውስጣችን ባለው የእግዚአብሔር ሕይወት ጥንካሬ እና የፈጠራ ችሎታ ከዓለም ጋር መሳተፍ ያስፈልገናል በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚህ መንገድ አዲስ ፣ ሁሉን አቀፍ ኢኮኖሚ እና ፍቅርን የሚጨምር የፖለቲካ ቅርፅን የሚያራምድ አዳዲስ ዘሮችን ለመዝራት ማገዝ እንችላለን ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማጠቃለያ መልእክታቸው አክለው እንደ ገለጹት በቤተክርስቲያኗ ማህበራዊ አስተምህሮ ፌስቲቫል ላይ ለተሳተፉ ሰዎች በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት አክለው እንደ ገለጹት የቤተክርስቲያኗ ማሕበራዊ አስተምህሮ ርዕሰ ጉዳዩን በማወቅ አባ አድሪያኖ ቪንቼንዚ በሕይወት በነበሩበት ወቅት እርሳቸው በሚፈልጓቸው ጎዳና ላይ እንዲቀጥሉ ለተሳታፊዎች ያሳሰቡ ሲሆን በዚህ መንገድ ብቻ ነው ግድግዳዎችን በማፍረስ ድልድዮችን መገንባት የምንችለው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ያስተላለፉትን መልእክት አጠናቀዋል።

27 November 2020, 11:50