ፈልግ

አርሶ አደር እና ሚሊሻ ተዋጊ ከጎንደር ኢትዮጵያ በስተሰሜን ምዕራብ በተክለድንጋይ መንደር ውስጥ አርሶ አደር እና ሚሊሻ ተዋጊ ከጎንደር ኢትዮጵያ በስተሰሜን ምዕራብ በተክለድንጋይ መንደር ውስጥ 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በኢትዮጵያ እና በሊቢያ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጥቅምት 29/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል ለተገኙ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናኑ ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ቅዱስነታቸው ለዓለም ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ወቅታዊ በሆኑ የቤተክርስቲያን እና የዓለማችን ክስተቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሳምንታዊ መልእክት እንደ ነበረ ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን የጀመሩት “ትናንት (ጥቅምት 28/2013 ዓ.ም)  በባርሴሎና ውስጥ ጆአን ሮይግ ዲግሌ በመባል የሚታወቅ አንድ ምዕመን እና ሰማዕት ብፁዕ እንደሆኑ መታወጁን” የገለጹ ሲሆን በስፔን የእርስ በእርስ ጦርነት ወቅት በአሥራ ዘጠኝ ዓመቱ ገና ወጣት ሳለ የተገደለ ወጣት እንደ ነበረ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። እርሱ በሥራው ቦታ ስኢየሱስ ምስክርነት ይሰጥ እንደ ነበረ የገለጹት ቅዱስነታቸው ሕይወቱን ለኢየሱስ ስጦታ አድርጎ አስከ መስጠት ድረስ ለእርሱ ታማኝ ሆኖ መኖሩን ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። የእሱ ምሳሌ ሁላችንንም በተለይም በወጣቶች ውስጥ የክርስቲያን ጥሪን ሙሉ በሙሉ ለመኖር ፍላጎት ያነሳል፣ የእርሱንም አርዐያ መከተል ይኖርብናል ብለዋል።

“አስቸጋሪ ሁኔታ ተባብሶ ብዙ ተጎጂዎችን የገደለ እና ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ምክንያት በቅርብ ቀናት ውስጥ በተመታው የማዕከላዊ አሜሪካ ነዋሪዎችን እንዳስብ የሚያደርገኝ ባንዲራ እዚያ አያለሁ፣ ጌታ ሟቾቹን በመንግሥቱ እንዲቀበል ፣ ቤተሰቦቻቸውን እንዲያጽናና በጣም በችግር ውስጥ ያሉትን እንዲሁም እነሱን ለመርዳት የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ ያሉትን ሁሉ ይደግፍ ዘንድ እጸልያለሁ” ብለዋል።

“ከኢትዮጵያ እየመጣ ያለውን ዜና በስጋት እየተከታተልኩ ነው። በትጥቅ ትግል የታገዘ ግጭት የማድረግ ሙከራ እንዲወገድ እየጠየኩኝ፣ ሁሉንም ወደ ፀሎት እና ወንድማዊ አክብሮት፣ ውይይት እና አለመግባባቶችን በሰላም እንዲያጠናቀቅ ማድረግ እንዲችሉ እጋብዛለሁ” ብለዋል።

በጥቅምት 29/2013 ዓ.ም በቱኒዚያ ሁሉንም ወገኖችን አሳታፊ ያደረገ በሊቢያ ዘላቂ ሰላም ማምጣት የሚችል “የፖለቲካ ውይይት መድረክ” ስብሰባዎች እንደ ሚጀመሩ በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው የዝግጅቱን አስፈላጊነት ከግምት በማስገባት በዚህ ረቂቅ ጊዜ ለሊቢያ ህዝብ ረዥም ስቃይ መፍትሄ እንደሚገኝ እና በቅርቡም ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ተከብሮ ተግባራዊ እንደሚሆን በጣም ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል። ለሊቢያ ሰላምና መረጋጋት እንዲመጣ ለፎረሙ ልዑካን እንጸልይላቸው በማለት አክለው ገልጸዋል።

ዛሬ በጣሊያን ውስጥ “ውሃ ፣ የምድር በረከት” በሚል ጭብጥ የምስጋና ቀንን እናከብራለን። ለግብርና ውሃ አስፈላጊ ነው እንዲሁም ለሕይወትም አስፈላጊ ነው! በገጠራማ ስፍራዎች ለሚገኙ በተለይም አነስተኛ ገበሬዎች በጸሎትና በፍቅር ለእናንተ ቅርብ መሆኔን እገልጻለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህ በቀውስ ውስጥ በምንገኝበት ወቅት ሥራቸው ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ነው፣ ውሃ እንደ አንድ የጋራ ጥቅም እንዲጠበቅ ከሚመክሩት የጣሊያን ጳጳሳት ጋር እቀላቀላለሁ ፣ አጠቃቀሙም ሁሉንም ተደራሽ ማድረግ አለበት ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

08 November 2020, 11:59