ፈልግ

በፊሊፒንስ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በፊሊፒንስ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሮማኒያ በእሳት፣ በፊሊፒንስ ደግሞ በጎርፍ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት አደረጉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሕዳር 06/2013 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እርሳቸው ዘወትር እሁድ በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የሚያደርጉትን የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ ለመከታተል ለተገኙ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናኑ ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ቅዱስነታቸው ለዓለም ያስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ትኩረቱን ወቅታዊ በሆኑ የዓለማችን ክስተቶች ላይ ያደረገ ሳምንታዊ መልእክት እንደ ነበረ ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሀይለኛ አውሎ ነፋስ ምክንያት በደረሰው ውድመት ለሚሰቃየው የፊሊፒንስ ህዝብ እና በሮማኒያ ዋና ከተማ ውስጥ በሚገኘው አንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ ከባድ አሰቃቂ የእሳት ቃጠሎ ማዘናቸውን በመልእክታቸው የገለጹ ሲሆን በተለይም በዚህ ሆስፒታል ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው የኮቪድ -19 ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች እንደ ነበሩ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እሁድ ዕለት በከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት በደረሰው ጥፋት እና ጎርፍ እየተሰቃዩ ለሚገኙት የፊሊፒንስ ህዝብ በጸሎት እንደ ሚያስቧቸው እና በመንፈስ ከእነርሱ ጋር መሆናቸውን ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህ ዓመት ፊሊፒንስን ከመታው እጅግ የከፋው አውሎ ነፋሱ የሟቾች ቁጥር በይፋ ወደ 67 ከፍ ብሏል ፣ ከአራት አስርት ዓመታት በላይ በከፋ የጎርፍ አደጋ በተመታው ሰሜናዊ ክልል ውስጥ ብዙ አካባቢዎች በጎርፍ ተጥለቅልቀው የገኛሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ገብርኤል ጸሎት ከምዕመናኑ ጋር በመቀባበል ከደገሙ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት “ለዚህ አደጋ በጣም ተጋላጭ ለሆኑ በጣም ድሃ ቤተሰቦች አጋርነቴን እገልጻለሁ” ሲሉ እነሱን ለመርዳት ለሚሰሩ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዚህ ዓመት በዓለም ላይ በጣም ኃይለኛ የሆነው ቫምኮ እና ሱፐር ታይፎን ጎኒን ጨምሮ በአራት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ስድስት አውሎ ነፋሶች በፊሊፒንስ ተክሰተዋል ከፍተኛ አደጋ አስከትለዋል።

ተጎጂዎችን ለመርዳት ካሪታስ ፊሊፒንስ መንግስት ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲያፈላልግ ለመንግስት ጥሪ አቅርቧል።

በሩማንያ አሳዛኝ ሁኔታ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ቅዳሜ ዕለት ሮማኒያ ውስጥ በሚገኘው አንድ ሆስፒታል ውስጥ በኮሮናቫ ይረስ የተጎዱ ሕመምተኞች በሕክምና ላይ በነበሩበት ወቅት አንድ አሳዛኝ የእሳት አደጋ መከሰቱን አውስተዋል፣ በዚህ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች ጸሎት ማድረጋቸው ተገልጿል።

በሰሜን ምስራቅ ሮማንያ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ 10 ሰዎችን ገድሎ 10 ሰዎችን አቁስሏል ፣ ሰባቱ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ የመንግሥት ባለስልጣናት አደጋውን አስመልክተው እንደ ገለጹት የእሳት ቃጠሎው በፒያራ ነአማት ከተማ በሚገኘው የሕዝብ ሆስፒታል ውስጥ ለኮቪድ -19 ታካሚዎች በተዘጋጀው ልዩ የሕክምና መስጫ ክፍል ውስጥ እንደ ተነሳ ከእዚያም በኋላ የእሳት አደጋው በወደ ሌሎች ክፍሎች መዛመቱን ገልጸዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተጠቁ ሰዎችን በሚያስተዳድረው እና ሁኔታውን በሚከታተለው ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ባወጣው መረጃ መሠረት ሩበሮማንያ ከ 350,000 በላይ ሰዎች በኮርኖአ ቫይረስ መጠቃታቸውን ይፋ ያደረገ ሲሆን ወደ ዘጠኝ ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን ሞት በማስመዘገቧ በዓለም ላይ ከፍተኛ የሞት መጠን ካላቸው 20 አገሮች አንዷ እንደ ሆነች ገልጿል።

15 November 2020, 12:51