ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የሮቦት ቴክኖሎጂ የሰው ልጅ ሰብዓዊ ክብርን ማዕከል ያደረገ አንዲሆን እንጸልይ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ለኅዳር ወር 2013 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ ሮቦቲክስ እና በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI) ዙሪያ ላይ ለመሻሻል የሚደረጉ ጥረቶች “የሰውን እና የፍጥረትን ክብር ለማክበር” ያተኮረ መሆኑ እንደ ሚገባቸው አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። አሁን ባለውና በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ፊት በመራመድ ላይ በሚገኘው የአለማችን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሮቦቲክስ እና በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI) የሚባሉትን የቴክኖሎጂ ዓይነቶች በከፍተኛ ደረጃ መደበኛውን የሰው ልጅ ሥራ እና ተግባር በመተካት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን በመደበኛነት የሰውን ልጅ የማሰብ ችሎታ የሚጠይቁ ሥራዎችን ማከናወን የሚችሉ የኮምፒተር ሥርዓቶች ንድፈ-ሀሳብ እና እድገት እንደ የእይታ ግንዛቤ ፣ የንግግር እውቅና ፣ ውሳኔ አሰጣጥ እና የተለያዩ የዓለማችን ቋንቋዎች በመተርጎም የሰዎ ልጆችን ዕለታዊ ሕይወት የተቀላጠፈ እንዲሆን በማደረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን ምንም እንኳን እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች አዎንታዊ ገጽታ ቢኖራቸውም እንኳን የሰው ልጆችን እና የተፈጥሮን ክብር በማይነካ መልኩ የቴክኖሎጂ እድገቱ መከናውን እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በወራዊው የጸሎት ሐሳባቸው ትኩረት በመስጠት ምዕመናን ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለኅዳር ወር 2013 ዓ.ም ያቅረቡት የጸሎት ሐሳብ እንደ ገለጹት ሮቦቲክስ እና በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI) የሰው ልጆች የፈጠራ ውጤቶች ምሳጋና ይግባውና እነዚህ እድገቶች የሰው ልጅ ሕይወት እንዲለውጥ እያስቻሉ መሆኑን መመልከቱ በራሱ አዎንታዊ የሆነ ገጽታ እንዳለው ገልጸው እነዚህ ነገሮች ትኩረታችንን እንደ ሳቡትም አክለው ተናግረዋል። ስለሆነም ይህ እድገት ሁሌም “ለሰው ልጆች አገልግሎት” በመስጠት ፣ የሰውን ልጅ ክብር በማክበር እና ፍጥረትን በመንከባከብ ላይ በሰፊው ይውል ዘንድ እንድንጸልይ ምዕመኑን ጋብዘዋል።

እውነተኛ እድገት

በተለያዩ የእውቀት መስኮች በብዙ አተገባበርዎች እንደሚታየው ሮቦት እና በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI) እጅግ የላቀ እድገት እንዲከሰት ማድረጉን የገለጹት ቅዱስነታቸው ዛሬ በዓለም ላይ 37% የሚሆኑ ድርጅቶች በተወሰነ መንገድ ሮቦት እና በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI) ተግባራዊ አድርገዋል ብለዋል፣ ይህም ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ የ 270% ጭማሪ እንዳሳየ ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በዚህ ወር ውስጥ ሊደረግ ስለሚገባው የጸሎት ሐሳብ በገለጹበት የቪዲዮ መልእክታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት በሮቦት እና በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI) ቴክኖሎጂ “መሻሻል የጋራ ጥቅምን ከማስከበር አኳያ የሚከናውን ከሆነ የተሻለ ዓለምን ሊያመጣ ይችላል” ብለዋል። ከዚህ አንፃር በህብረተሰቡ ውስጥ በአሁኑ ወቅት የሚታዩት ልዩነቶች እንዲሰፉ  የማያደርጉ የቴክኖሎጂ እድገት እንዲመጣ ተስፋ እንደ ሚያደርጉ የገለጹት ቅዱስነታቸው በማሕበረተሰቡ መካከል ያለው ልዩነት እንዲሰፋ የሚያደርግ ማነኛውም ቴክኖሎጂ “እውነተኛ እድገት” ያሳገኝም ብለዋል። እንዲህ ዓይነቱ እድገት የሰውን ልጅ ክብር እና ለፍጥረት እንክብካቤን ማደረግን ከግምት ውስጥ አያስገባም በመሆኑም ሊሻሻል ይገባዋል ብለዋል።

ጥቅሞች

ሮቦቲክስ እና የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI) የመሻሻል ዕድሎችን ለመለየት የተማሪዎችን የመማር አቅም መገምገምን የመሳሰሉ በሰው ልጆች ላይ እየታዩ ያሉ ብዙ ችግሮችን መፍታት ይችላል። የተሻሉ የግንኙነት መሣሪያዎችን በማዘጋጀት (ለምሳሌ ጽሑፍን ወደ ንግግር ወይም ንግግርን ወደ ጽሑፍ መለወጥ የመሳሰሉ ተግባሮች) የማየት ወይም የመስማት ችግር ላለባቸው ሰዎች ሊረዳ ይችላል። ሮቦቲክስ እና የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI)  በተጨማሪም የታካሚዎችን በተለይም በሩቅ አካባቢዎች የሚኖሩትን ምርመራ እና ህክምና ለማሻሻል የጤና መረጃዎችን መሰብሰብ ፣ ማቀነባበር እና ስርጭትን ሊያፋጥን ይችላል።

በተመሳሳይ መልኩ ሮቦቲክስ እና የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI)  በሥነ ምህዳራዊ መስክ ላይ በሰፊው ተሰማርቶ ይገኛል። በ AI አማካይነት በአየር ንብረት ለውጥ ላይ መረጃን መተንተን እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመተንበይ የሚያግዙ መዋቅሮችን መፍጠር ይቻላል። የከተማ ወጪን በመቀነስ ፣ የአውራ ጎዳናዎችን የመቋቋም አቅም በማሻሻል እና የታጋሽ ኃይል ውጤታማነትን በመጨመር ንጹህ እና ዘላቂ አገልግሎቶችን በመስጠት ከተማዎችን ለመፍጠርም ሊያገለግል ይችላል። ይህንን የቴክኖሎጂ እድገት ለጋራ ጥቅም መጠቀሙ ሰፊ አጋጣሚዎችን እንደሚከፍት የገለጹት ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ከጣሊያን የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ከኢጣሊያ ሁለገብ ኃይል ኩባንያ ኤነል ምስሎችን በመጠቀም ከእነዚህ ጥቅሞች ጥቂቶቹን በዋቢነት ገልጸዋል።

የሰው ልጅን ማገልገል

የኤንኤል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍራንቼስኮ ስታራዝ “ፈጠራን በተሻለ አቅማችን ለመጠቀም መቻል ያለብንን ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን አስቀምጠናል” ብለዋል።

በመቀጠልም ፣ “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንዳረጋገጡት ፣ የተገኙት ጥቅሞች በፍትሃዊነት እንዲሰራጭ እና ዕድሎችን እንዲከፍት እና የጤንነትን ዕድገትን መፍጠር እንዲያስችሉ መጠቀም የእኛ ተግባር ነው” በማለት የገለጹ ሲሆን “የአሁኑን እና የወደፊቱን በተመለከተ ለድርጊታችን እና ለምርጫችን አዎንታዊ አቅጣጫ ለመስጠት በዘላቂነት ላይ የተመሠረተ ራዕይን ተቀብለን ለሰዎች እና በማዕከሉ ውስጥ ለአከባቢው አክብሮት መስጠት አለብን በማለት አክለው ገልጸዋል። በዚህ መንገድ ብቻ ስንጓዝ ነው የቴክኖሎጂ ዝግመተ ለውጥ የሰው ልጅ ተባባሪ ሊሆን እና ዕድሎች ሊፈጥር የሚችለው በማለት የገለጹት ቅዱስነታቸው ይህም እስከ ጥቂት ዓመታት በፊት ድረስ እንኳን መገመት ያቃተን ጉዳይ ነበር ብለዋል።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዓለም አቀፍ የጸሎት መረብ ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወርሃዊ የጸሎት ዓላማዎች መስፋፋት ኃላፊነቱን የወሰደ ማሕበር ነው። የአውታረ መረቡ ዓለም አቀፋዊ ዳይሬክተር የሆኑት ፍሬድሪክ ፎርኖስ ለኅዳር ወር የቅዱስ አባታችን የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን የጸሎት ሐሳብ አስመልክተው በሰጡት አስተያየት እነዚህን ፈጣን የቴክኖሎጂ ለውጦች ለ “ለሁሉም” ማስተላለፍ አስፈላጊ ስለመሆኑ ይናገራሉ።

"የዚህ ወር የፀሎት ዓላማ" የሰው ልጅ በቴክኖሎጂ እድገት ያገኘው (ወደፊትም የሚያገኘው) ጥቅም ሁልጊዜም ከግምት ውስጥ መግባት አለበት የሚለውን ሀሳብ ያጠናክራል "የሳይንሳዊ እና የቴክኖሎጂ ፈጠራ እድገት ብዙዎችን ይዞ መምጣት ቢችል ምንኛ ድንቅ ነበር!" እኩልነት እና ማህበራዊ አቀፍነት ወይ አካታችነትን ከግምት ማስገባት ይኖርበታል ብለዋል።

ሮቦቲክስ እና የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI)  እና ሌሎች የቴክኖሎጂ ትግበራዎች  ቅዱስነታቸው እንደሚሉት ለስነምግባር እና ለማህበራዊ ፍትህ ትልቅ ፈተናዎችን እንደ ሚሆኑ የገለጹ ሲሆን የሊቀ ጳጳሱ የቅርብ ጊዜ አቤቱታ አስፈላጊ የሆነው ለዚህ ነው- ይህ የቴክኖሎጆ መሻሻል ሁልጊዜ ‘ሰው ልጆችን በተሻለ መልኩ ማገልግል ላይ እንዲውል’ መጸለይ ያስፈልጋል።

የኅዳር ወር 2013 ዓ.ም የጸሎት ዓላማ

ሮቦቲክስ እና የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI)  እያስገኙት የሚገኙት ከፍተኛ አውንታዊ ለውጥ አለ። ሮቦቲክስ እና የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI)   ከጋራ ጥቅም ጋር ከተዋሃደ የተሻለ ዓለም እንዲኖር ማድረግ ይችላል። በእርግጥ የቴክኖሎጂ እድገት ልዩነቶችን ከጨመረ እውነተኛ እድገት አይደለም። የወደፊቱ እድገቶች የሰውን እና የፍጥረትን ክብር በማክበር ላይ ያተኮሩ መሆን አለባቸው ፡፡

ሮቦቲክስ እና የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (Artificial intelligence AI)  ቴክኖሎጂ እድገት ሁሌም የሰው ልጆችን እንዲያገለግል እንጸልይ… “ለሰው አገልግሎት እንዲውል” እንጸልይ።

10 November 2020, 14:13