ፈልግ

2020.10.03 Assisi Papa Firma Enciclica 2020.10.03 Assisi Papa Firma Enciclica 

የር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ለመላው ዓለም የቀረበ መልዕክት መሆኑ ተገለጸ።

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ቅዳሜ መስከረም 23/2013 ዓ. ም በጣሊያን ውስጥ አሲዚ ከተማ ተገኝተው “ሁላችንም ወንድማማቾች ነን” በሚል ርዕሥ ይፋ ባደረጉት የአዲስ ቃለ ምዕዳን ማጽደቅ ሥነ-ሥርዓት ላይ ታላላቅ የፍራንችስካዊያን ማኅበር ገዳማዊያት እና ገዳማውያን መገኘታቸው ታውቋል። ዕለቱ በፍራንችስካዊያን ማኅበር ታሪክ የተመዘገበበት መሆኑን በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት፣ የኮንቨንቷል ፍራንችስካዊያን ታናናሽ ወንድሞች ጠቅላይ አለቃ፣ ክቡር አባ ካርሎስ አልበርቶ ትሮቫሬሊ ተናግረው የር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ አዲስ ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳን ለዓለም በሙሉ የቀረበ መልዕክት መሆኑ ገልጸዋል።

የቫቲካን ዜና፤

የጣሊያን ባልደረባ እና ጠባቂ በሆነው በቅዱስ ፍራንችስኮስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ዋዜማ ላይ መስከረም 23/2013 ዓ. ም የተፈጸመው ሥነ-ሥርዓት ትልቅ መንፈሳዊ ስሜት የተገለጸበት መሆኑ ታውቋል። “ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በስፍራው ተገኝተው፣ ‘ሁላችንም ወንድማማቾች ነን’ የሚለውን አዲስ ቃለ ምዕዳናቸውን በፊርማቸው በማጽደቅ ይፋ ያደረጉበት ዕለት፣ ታላላቅ የሚባሉ የቅዱስ ፍራንችስኮስ ቤተሰባዊ ማኅበራት አባላት የተካፈሉበት እና ባለፉት ቀናት ውስጥ በተደረጉት ውይይቶች ላይ ሃሳባቸውን የገለጹበት፣ ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመሆን የአገልጋይነት ሕይወት የታየበት መሆኑን የኮንቨንቷል ፍራንችስካዊያን ታናናሽ ወንድሞች ጠቅላይ አለቃ፣ ክቡር አባ ካርሎስ አልበርቶ ትሮቫሬሊ ገልጸዋል።

ክቡር አባ ካርሎስ አልበርቶ ትሮቫሬሊ አክለውም፣ ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ በስፓኒሽ ቋንቋ የጻፉትን ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸውን ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም የተባበሩትን በሙሉ ማመስገናቸውን ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው በዕለቱ የቀረበውን የመስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት ከተካፈሉት ጋር አጭር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል። ክቡር አባ ካርሎስ አልበርቶ ትሮቫሬሊ “ይህ ታላቅ ቀን በሕዝቦች መካከል ሰላም የሚወርድበትን መንገድ የሚያስተምር መሆኑን ገልጸው፣ በቅዱስ ፍራንችስኮስ አገር በሆነችው በአሲዚም ሰላም እንዲወርድ በመመኘት ንግግራቸውን አጠቃለዋል።    

04 October 2020, 15:02