ፈልግ

2019.09.30 San Girolamo -o Gerolamo- Sacerdote e dottore della Chiesa 2019.09.30 San Girolamo -o Gerolamo- Sacerdote e dottore della Chiesa 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ የጻፉት መልዕክት የቅዱስ ጀሮምን የመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር ያረጋግጣል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረቡዕ መስከረም 20/2013 ዓ. ም ያቀረቡትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ ዕለቱ የቤተክርስቲያን ሊቅ እና የመጽሐፍ ቅዱስ አፍቃሪ የሆነው፣ የቅዱስ ጀሮም መታሰቢያ ዕለት መሆኑን አስታውሰዋል። በዚህም መሰረት ቅዱስ ጀሮም ያረፈበት አንድ ሺህ ስድስት መቶኛ ዓመት የሚያስታውስ ቅዱስ ሐዋርያዊ መልዕክት በፊርማ በማረጋገጥ ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ቅዱስነታቸው ከዚህ ጋር በማያያዝ ባሰሙት ንግግር፣ መጽሐፍ ቅዱስን የሕይወቱ ማዕከል ያደረገው፣ የዚህ ታላቅ የቤተክርስቲያን ሊቅ እና አባት አርአያነት፣ በእኛም ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ፍቅር እንዲያድግ በማድረግ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር የግል ግንኙነት እንድናደርግ ዲኖርገን በማለት ንግግራቸውን አጠቃልለዋል።    

ቅዱስነታቸው በማስከተልም ከጣሊያን የተለያዩ ከተሞች መጥተው በስፍራው የተገኙ ምዕመናንን በማስታወስ ባሰሙት ንግግር፣ እግዚአብሔር ለልባቸው ምኞት መልካሙን እንዲሰጥ፣ ለቅርብ ወዳጆቻቸውም በሙሉ በሕይወታቸው መልካም እንዲያበዛላቸው ተመኝተውላቸዋል። ቀጥለውም አረጋዊያንን ወጣቶችን፣ ሕሙማንን እና ጋብቻቸውን በቅርቡ የፈጸሙትን አስታውሰዋቸዋል። እያንዳንዱ ሰው በሚገኝበት የኑሮ ደረጃ፣ በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ እና በሚያጋጥመው ስቃይ ቸርነትን እንዲለማመድ፣ በእውነት ላይ የቆመ ቤተሰብን እንዲመሰርት ተመኝተዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የዕለቱን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ሲያጠቃልሉ በሥፍራው ለተገኙት ምዕመናን በሙሉ ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ሰጥተዋቸል። 

30 September 2020, 21:01