ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ለነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ መልእክት ይፋ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ለነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ያቀረቡት የጸሎት ሐሳብ በባሕር ላይ በመርከብ በመጓዝ የተለያየ ዓይነት አገልግሎት ለሚሰጡ መርከበኞች የቀረበ ጸሎት እንደ ሆነ የተገለጸ ሲሆን በተለይም በመርከብ በመቅዘፍ የተለያየ ዓይነት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ፣ በንግድ መርከቦች፣ በመርከብ በመጓዝ በዓሳ ማጥመድ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች እና የባህር ኃይል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መልኩ ሥራ ለሚያከናውኑ ሰዎች በሙሉ ጸሎት የሚደረግበት ወር እንዲሆን ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት ይፋ አድርገዋል። ቅዱስነታቸው በቪዲዮ ባስተላለፉት መልእክት የሚከተለውን ብለዋል…

የመርከበኞች ወይም የዓሳ አጥማጆች እና የቤተሰቦቻቸው ሕይወት በጣም ከባድ ነው።አንዳንድ ጊዜ አስገዳጅ በሆነ የጉልበት ሥራ ሰለባዎች ይሆናሉ ወይም ከአገራቸው ርቀው በሚገኙ ወደቦች ውስጥ ይሰራሉ። የዓሳ ማጥመድ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሚታየው ውድድር እና የአከባቢ ብክለት ችግር ሥራቸውን የበለጠ ውስብስብ ያደርግባቸዋል። በባሕር ላይ የሚሰሩ መርከበኞች ባይኖሩ ኖሮ ብዙ የዓለም ክፍሎች ይራባሉ። በባህር ላይ ሁነው ሥራቸውን ለሚያከናውኑ ለሚኖሩ መርከበኞች ሁሉ እንጸልይ ፣ ለመርከበኞች፣ ለዓሳ አጥማጆች እና ለቤተሰቦቻቸው እንጸልይ።

06 August 2020, 09:34