ፈልግ

በሊባኖስ ዋና ከተማ በቤሩት የደረሰው የፍንዳታ አደጋ በሊባኖስ ዋና ከተማ በቤሩት የደረሰው የፍንዳታ አደጋ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለሊባኖስ ጸሎት ማድረግ ያስፈልጋል አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሐምሌ 29/2012 ዓ.ም ዘወትር ረቡዕ እለት የሚያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ ባስተላለፉት መልእክ ትላንት ማታ በሊባኖስ ዋና ከተማ በቤሩት የአገሪቷን እና የዓለም ሕዝቦችን ሳይቀር ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የከተተ እና የብዙ ሰዎችን ሕይወት በቀጠፈው ከፍተኛ ፍንዳታ ማዘናቸውን ገልጸዋል። በዚህ አደጋ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን በሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ መቁሰላቸው ተገልጿል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከሁሉም ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት ጋር ስለጉዳዩ እንደ ሚነጋገሩ ገልጸው ለተጎጂዎች እና ለቤተሰቦቻቸው መጸለይ እንደ ሚቀጥሉ ገልጸዋል።

በዚህ አሳዛኝ ጊዜ ​​የሁሉም ሰው ቁርጠኝነት ያስፈልጋል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተጎጂዎችን እና ቤተሰቦቻቸውን በማስታወስ ጸሎት ያደርጉ ሲሆን ሊባኖስ ይህን ቀውስ ለማሸነፍ ትችል ዘንድ እንዲረዷት ለሁሉም ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት ጥሪ አቅርበዋል።

ትናንት በቤሩት በሚገኘው በአንድ ወደብ አቅራቢያ ከፍተኛ ፍንዳታዎች መከሰታቸው የሚታወስ ሲሆን በአደጋው ከመቶ በላይ የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ከ4000 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል፣ በከተማይቷ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱም ተገልጿል።  ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ማጠቃለያ ላይ ለተጎጂዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው መጸልያቸውን እንደ ሚቀጥሉ አረጋግጠው በሁሉም ማህበራዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ተቋማት የችግሩ ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ለመርዳት ቁርጠኛ ተነሳሽነት እንዲያሳዩ የጠየቁ ሲሆን  ይህንን አሳዛኝ እና አስቸጋሪ ወቅት ለመቋቋም እና ለመሻገር የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ የራሱን ሚና ይጫወት ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

05 August 2020, 12:09