ፈልግ

በሜክሲኮ የሚገኘው በወንጀለኞች የሚፈጸመውን ግዲያ የሚቃወም ሐውልት በሜክሲኮ የሚገኘው በወንጀለኞች የሚፈጸመውን ግዲያ የሚቃወም ሐውልት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ስደተኞች የማባከን ባሕል ሰለባዎች ናቸው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 17/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት  የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከደገሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳማንታዊ መልእክት በአሁኑ ወቅት በዓለማችን በከፍተኛ ሁኔታ የሚታየው የማባከን ባሕል ስደተኞችን ሰለባ አንዳደረገ ገልጸው ለዚህ ተግባራችን ደግሞ አምላክ ይጠይቀናል፣ ለዚህ እየፈጸምነው ለምንገኘው ተግባር ሂሳቡን ከአምላክ ጋር ማወራረዳችን አይቀርም ብለዋል።

በሜክሲኮ ሳን ፈርናንዶ በሚባል ስፍራ ውስጥ በስደተኞች ላይ ከፍተኛ እልቂት የተፈጸመበት በአሥረኛው ዓመት ዋዜማ ላይ ፍትህና እውነት አስካሁን አለመረጋገጣቸውን በመልእክታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በእምነታቸው ምክንያት ለስደተ የተዳረጉ ሰዎች እና የዚህ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎችን አስታውሰው በዓለም ዙሪያ በሽብርተኞች ምክንያት  በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው ሁልጊዜም እንደ ሚያሳስባቸው ገልጸው በተለይም ደግሞ በሰሜናዊ ሞዛምቢክ የተፈጠረው ሁኔታ አሳዛኝ በመሆኑ ሁኔታው በሰላማዊ መንገድ አንዲቋጭ እንጸልይ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ በተለይም የዛሬ አሥር ዓመት ገደማ ምስጢራዊ በሆነ ሁኔታ 72 ስደተኞች በጅምላ ተጨፍጭፈው መገደላቸውን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው እነዚህ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 24/2010 ዓ.ም በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ስደተኞች በማዕከላዊ ሜክሲኮ ሳን ፈርናዶ በሚባልበት ስፍራ የ72 ስደተኞች አስከሬን መገኘቱ የሚታወስ ሲሆን ከተገኙት አስክሬኖች መካከል የሆንዱራስ ፣ የሳልቫዶራስ ፣ የጓቲማላን ፣ የኢኳዶር ፣ የብራዚል ተወላጆችና ከሕንድ የመጣ አንድ ሰው እንደ ሚገኙበት በወቅቱ መዘገቡ ይታወሳል። ይህ ድርጊት የተፈጸመው የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር በሚያካሂዱ ሰዎች እንደ ነበረ በወቅቱ የተገለጸ ሲሆን እነዚህ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች የሚፈጽሙት የጭካኔ ተግባር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ እንዳሳሰባቸው ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሰተላለፉት መልእክት አክለው ገልጸዋል።

23 August 2020, 10:46