ፈልግ

በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የሕዳሴ ግድብ በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ የሚገኘው የሕዳሴ ግድብ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ አባይ አንድነትን እና ብልጽግናን ሊፈጥር እንጂ መለያየትን ሊያመጣ አይገባም አሉ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በነሐሴ 09/2012 ዓ.ም በእለቱ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ የተከበረውን የፍልሰታ አመታዊ በዓል አስመልክተው በእለቱ በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት  የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከምዕመናን ጋር በጋራ ከደገሙ በኋላ ለዓለም ያስተላለፉት ሳማንታዊ መልእክት ዛሬ በሰማያዊ ክብር ውስጥ የምትገኘውን ድንግል ማርያም በምናሰላስልበት ወቅት “የተስፋ እናት” እንደ ሆች አምነን በመቀበል ነው ብለዋል። ይህ “የተስፋ እናት” የተሰኘው ሊጣኒያ ይህ የማዕረግ ስም በቅርቡ በሎሬቶ ሊጣኒያ ውስጥ እንዲካተት እንደ ተደረገ በመግለጽ ሳምንታዊውን መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዓለም ላይ በጣም ተስፋ ለሚያስፈልጋቸው ሁኔታዎች እና ሰዎች ሁሉ አማላጅነቷን እንማጸናለን፣ ለሰላም ፣ ለፍትህ ፣ ለተከበረ ሕይወት ተስፋ እንዲኖረን እንማጸናታለን፣ ዛሬ በኃይል እርምጃ እና የአሸባሪዎች ጥቃት ሰለባ ለሆኑት የሰሜን ናይጄሪያ ህዝብ በተለይ መጸለይ እፈልጋለሁ ብለዋል።

“እኔ የአባይን ወንዝ በተመለከተ በግብፅ ፣ በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል እየተካሄደ የሚገኘውን አስቸጋሪ ድርድር ሁኔታውን በተለየ መልኩ እየተከታተልኩኝ ነው” በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህ ዘለአለማዊ የሆነ ወንዝ ሁልጊዜም ቢሆን አንድነትን የሚፈጥር የሕይወት ምንጭ እንዲሆን እንጂ መለያየትን ሊያመጣ አይገባም፣ ወንዙ ወንድማማችነትን እና ብልጽግናን እንዲያመጣ እንጂ ጠላትነትን፣ አለመግባባትን ወይም ግጭትን እንዳያስከትል በጀመሩት የውይይት መስመር ላይ እንዲቀጥሉ ለሁሉም ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጥሪ አቀርባለሁ” ብለዋል። “በግብፅ፣ በኢትዮጲያ እና በሱዳን የምትገኙ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ! ውይይት የእናነት ብቸኛው ምርጫ እንዲሆን እንመኛለን  ለምትወዷቸው ሕዝቦቻችሁ እና ለመላው ዓለም ውይይት መልካም የሆነ ምርጫ ነው” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ሰላምታ አቅርበው እና ሐዋርያዊ ቡራኬያቸውን ሰጥተው ሳምንታዊ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

15 August 2020, 15:42