ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛን በጎበኙበት ወቅት፤ ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛን በጎበኙበት ወቅት፤ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ መጽናናትን ተመኝተውላቸዋል።

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ ታላቅ ወንድማቸውን በሞት የተለዩትን የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛን በጸሎታቸው አስታውሰው መጽናናትን ተመኝተውላቸዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛን በጸሎት የሚያስታውሷቸው መሆኑን በመልዕክታቸው አረጋግጠውላቸዋል።

የቫቲካን ዜና፤

ብጹዕ አቡነ ጆርጅ ራዚንገር የሕክምና ዕርዳታ ሲደረግላቸው ቆይተው፣ ተወልደው ባደጉባት የጀርመን ከተማ ራቲስቦና ውስጥ በ96 ዓመት ዕድሜአቸው ረቡዕ ሰኔ 24/2012 ዓ. ም. ማረፋቸው ታውቋል። ብጹዕ አቡነ ጆርጅ ራዚንገር ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ሕመም ጸንቶባቸው በሬግኔስቡርግ ሆስፒታል የሕክምና ዕርዳታ ሲያገኙ መቆየታቸው ይታወሳል። የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ ከሁለት ሳምንታት በፊት ከቫቲካን ወደ ጀርመን ተጉዘው ጠይቀዋቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ በላኩት የማጽናኛ መልዕክታቸው፣ የሚወዷቸውን ወንድማቸውን፣ የብጹዕ አቡነ ጆርጅ ራዚንገርን ዕረፍት ከሁሉ አስቀድመው የሰሙ መሆኑን አስታውሰው፣ በዚህ ጥልቅ ሐዘን ወቅት፣ ሕይወትን የሚሰጥ፣ ምሕረት በተሞላው ደግነቱ፣ ታማኝ የወንጌል አገልጋይ የነበሩትን አቡነ ጆርጅ ራዚንገር እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸው በማለት በጸሎት አስታውሰዋል።  

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በማከልም በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እርዳታ እና ቸርነት የተሞላበት መለኮታዊ መጽናናትን በጸሎት ለምነው፣ የተስፋ እና የሰላም ምንጭ፣ ከሞት በተነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ ባላቸው እምነት ዘወትር ኅብረት ያላቸው መሆኑን ለቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቤነዲክቶስ 16ኛ ገልጸውላቸዋል።       

03 July 2020, 08:06