ፈልግ

ብጹዕ ካርዲናል ሉዊስ አንቶኒዮ ታግለ፤ ብጹዕ ካርዲናል ሉዊስ አንቶኒዮ ታግለ፤ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ለሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ተጨማሪ አባላትን መረጡ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ረቡዕ ሐምሌ 1/2012 ዓ. ም. በቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤት ተጨማሪ አባላትን መሰየማቸው ተገለጸ። በቅድስት መንበር ለሕዝቦች የወንጌል አገልግሎት ማስፋፊያ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ሉዊስ አንቶኒዮ ታግለ እና በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት፣ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች መምሪያ ምክትል ዋና ጸሐፊ የሆኑትን ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒይን በጳጳሳዊ ምክር ቤት የሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት አስተባባሪ አድርገው መምረጣቸው ታውቋል።

የቫቲካን ዜና፤

በጳጳሳዊ ምክር ቤት የሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት የሚከታተል ጽሕፈት ቤት የሁለተኛውን የቫቲካን ጉባኤ ፈለግ በመከተል፣ በተለይም “Nostra aetate” ወይም “በእኛ ዘመን” በተሰኘው የጉባኤው ሐዋርያዊ ሰነድ በመመራት፣ በሐይማኖት ተቋማት መካከል የሚካሄደውን የጋራ ውይይት የሚከታተል ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት መሆኑ ይታወቃል።

አዲስ ተመራጮች እነዚህ ናቸው፤

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ በቅድስት መንበር ለሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት ጳጳሳዊ ምክር ቤት ከመረጧቸው መካከል፣ ብጹዕ ካርዲናል ዴዎዶኔ ዛፓላይንጋ፣ የባንጊ ሊቀ ጳጳስ፤ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሉዊስ ማሪ ሊንግ የላኦስ ሐዋርያዊ አስተዳዳሪ፤ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኢግናጢዮስ ሱሃሪዮ በኢንዶኔዢያ የጃካርታ ሊቀ ጳጳስ እና ሊቀ ጳጳሳ ዣን ክሎድ ሆልሪች የሉክስንቤርግ ጳጳሳዊ ምክር ቤት አባል መሆናቸው ታውቋል። ከእነዚህም በተጨማሪ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ካቶሊካዊ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤዎች የተመረጡ ብጹዓን ጳጳሳት መኖራቸው ታውቋል። ሊቀ ጳጳሳት ብጹዕ አቡነ ሎሬንስ ሁክላክ ከዩክሬን፣ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፌሊክስ አንቶኒ ማቻዶ ከሕንድ ቦምቤይ፣ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጆርጅ ፍሬንዶ ከአልባኒያ ቲራና፣ ሊቀ ጳጳሳ ብጹዕ አቡነ ማርክ ቲን ዊን ከሚያንማር፣ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ዣን ማርክ አቬሊን ከፈረንሳይ፣ ብጹዕ አቡነ ፖል ዮሺኖ ኦሱካ ከጃፓን ኪዮቶ፣ ብጹዕ አቡነ ቶማስ ቹንግ አን ዙ ከታይዋን፣ ብጹዕ አቡነ ራፊ ማንያሊ ከሕንድ አላሃባድ፣ ብጹዕ አቡነ አምብሮጆ ስፕሪያፊኮ ከጣሊያን ፍሮሲኖኔ-ቨሮሊ-ፌረንቲኖ፣ ብጹዕ አቡነ ሚካኤል ዮሴፍ ማኬና ከአውስትራሊያ፣ ብጹዕ አቡነ ዊሊያም ሐና ሾማሊ ከቅድስት አገር ኢየሩሳሌም፣ ብጹዕ አቡነ ዴኒስ ቺዲ ኢሲዮዞ ከአልጄሪያ፣ ብጹዕ አቡነ ፓትሪክ ዮሴፍ ሚክኒ ከእንግሊዝ ኖትንግሃም፣ ብጹዕ አቡነ ጄምስ ማሳ ከሰሜን አሜሪካ፣ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ፖል ዴስፋርጌስ ከአልጄር እና ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ዲን ዱክ ዳዎ ከቬትናም መሆናቸው ታውቋል።

ብጹዕ ካርዲናል ሚገል አንገል ኣዩሶ ከጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከግንቦት 25/2019 ዓ. ም. ጀምሮ በጳጳሳዊ ምክር ቤት የሐይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት አስተባባሪ ጽሕፈት ቤት ፕሬዚደንት ሆነው በማገልገል ላይ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

09 July 2020, 17:45