ፈልግ

በማላዊ ሕጻናት በጉልበት ሥራ ላይ ተሰማርተው በማላዊ ሕጻናት በጉልበት ሥራ ላይ ተሰማርተው 

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ብዙ ሕጻናት ወደ ጉልበት ሥራ እዲገቡ ሊያደርግ እንደ ሚችል ተገለጸ

የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛን አስመልክቶ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያዘጋጀው ዓለም አቀፍ ቀን በሰኔ 05/2012 ዓ.ም መከበሩ ተገለጸ። በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በተከሰተው ኢኮኖሚያዊ እና የሥራ ቀውስ ሰበብ በሚልዮን የሚቆጠሩ ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናት በችግር ውስጥ የገቡትን ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት በማሰብ በጉልበት ሥራ ላይ ይሰማራሉ የሚል ስጋት እንዳለ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ 218 ሚሊዮን ያህል ሕፃናት በጉልበት ሥራ ላይ ተሰማርተው እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 152 ሚሊዮን በግዳጅ ወደ ሥራ የተሰማሩ ናቸው፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 73 ሚሊዮን የሚሆኑት ሕጻናት በአደገኛ ሁኔታዎች ውስጥ በአስገዳጅ ሥራ ላይ የተሰማሩ ናቸው፣ ከ 152 ሚሊየን በአስገዳጅ ሥራ ውስጥ ከተሰማሩ ሕጻናት መካከል 64 ሚሊዮን የሚሆኑት ሴት ልጆች ሲሆኑ 88 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ወንድ ሕጻናት ልጆች ናቸው፣ ይህም በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ከእያንዳንዱ 10 ሕጻንት ውስጥ አንዱ ሕጻን ለጉልበት ሥራ የተዳርጓል ማለት ነው።

የኮሮና ቫይረስ እና የሕጻናት የጉልበት ሥራ

የዓለም አቀፉ የሰራተኛ ድርጅት (ILO) እና የተባበሩት መንግስታት የሕፃናት ፈንድ (ዩኒሴፍ/UNICEF) በጋራ ባወጡት መግለጫ እንደ ገለጹት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ቀውስ የተነሳ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተጨማሪ ሕፃናት የጉልበት ብዝበዛ ወደ ሚያጋጥማቸው የጉልበት ሥራ ላይ እንደ ሚሰማሩ ከወዲሁ ግምት እንደ ተሰጠው ተዘግቧል።

ይህንን በተመለከተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 03/2012 ዓ.ም በቫቲካን ያደርጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ካጠናቀቁ በኋላ ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት በልጆች ላይ በሚደርሰው አስገዳጅ የጉልበት ብዝበዛ ለከፍተኛ ጉዳት እየተጋለጡ ለሚገኙ ልጆች የዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ትኩረት እንዲሰጥ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል።

ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 03/2012 ዓ.ም ቅዱስነታቸው በቫቲካን ካደረጉት ሳምንታዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በመቀጠል ባስተላለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ለጉልበት ብዝበዛ ለተዳረጉ ሕጻንትን ጉዳይ ቅዱስነታቸው ማንሳታቸው የተገለጸ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሕጻናት የጉልበት ብዝበዛ ሰላብ እንደ ሆኑ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ አርብ ሰኔ 05/2012 ዓ.ም የልጆች ጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል ዓለም አቀፍ ቀን እንደ ሚከበር ገልጸው እንደ ነበር መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የበርካታ ወንዶችና የሴቶች ልጆች የተቀናጀ ሰብዓዊ ልማት አደጋ ላይ መውደቁን ገልጸዋል።

በመቀጠልም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደገለጹት “አሁን ባለው ድንገተኛ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሁኔታ ውስጥ በበርካታ አገሮች ውስጥ ብዙ ልጆች እና ወጣቶች ቤተሰቦቻቸው በጣም ድሃ በመሆናቸው የተነሳ ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ዕድሜያቸውን የማይመጥን እና ተገቢ ወዳልሆኑ ስራዎች ውስጥ እንዲገቡ እየተገደዱ መሆኑን ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል።

አክለውም ብዙውን ጊዜ “እነዚህ የባርነት እና የእስራት ዓይነቶች አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሥቃይን የሚያስከትሉ ናቸው” ብለዋል።

ሁላችንም ለዚህ ኃላፊነት አለብን!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መልእክታቸውን ሲቀጥሉ “ተቋማት ለአካለ መጠን ያልደረሱ ወጣቶችን ለመከላከል የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪዬን አቀርባለሁ” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን እሱ በሚያሳዝን ሁኔታ ውስጥ በዚህ አስቸጋሪ በሆነ የጉልበት ብዝበዛ እንዲጋለጡ ያደረጋቸው የተዛባ እና ተለዋዋጭ ኃይል የሚያደናቅፉ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ክፍተቶች የተሞሉ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

በመጨረሻም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ልጆች የሰው ልጅ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ናቸው፤ በመሆኑም  እድገታቸውን እና ጤንነታቸውን ማረጋገጥ የሁላችንም ኃላፊነት ሊሆን ይገባል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ማጠናቀቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

10 June 2020, 11:45