ፈልግ

“የዘመናችን ሕዝብም እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለስደት ተጋልጧል”።

ቤተክርስቲያን በችግር ውስጥ ለሚገኙት ሰዎች በምትሰጠው ልዩ ትኩረት እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከ1914 ዓ. ም. ጀምሮ በየዓመቱ ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን ስታከብር ቆይታለች። ዕለቱ ላለፉት 106 ዓመታት፣ በመስከረም ወር መጨረሻ ሳምንት ላይ ሲከበር የቆየ ሲሆን የዘንድሮ እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር መስከረም 29/2020 ዓ. ም. ተከብሮ ይውላል።  ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመስከረም ወር ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን እንዲሆን  በማለት “እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለስደት ተጋልጠዋል” የሚለውን መሪ ቃል በማቅረብ በአሁኑ ወቅት የሚከሰተውን የአገር ውስጥ መፈናቀል ለማስታወስ ፈልገዋል። "በውስጣችን ያለው ፍርሃት ለያይቶን፣ በጋራ እንዳንወያይ አድርጎናል" በማለት የቪዲዮ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የቫቲካን ዜና፤

ወደ ግብጽ የተደረገውን ስደት ስናስታውስ፤

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በመስከረም ወር ለሚከበረው ዓለም አቀፍ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ቀን ያስተላለፉትን መልዕክት ባጠቃለሉበት ወቅት የሚከተለውን ጸሎት አቅርበዋል፥

"እግዚአብሔር አባት ሆይ፣ ሕጻኑን ኢየሱስን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያም ከአደጋ እንዲከላከል በማለት ለቅዱስ ዮሴፍ በአደራ ሰጥተሃል። እኛም ዘወትር የእርሱ ጥበቃ እና እገዛ እንዳይለየን እንለምናለን። ከኃይለኞች የሚሰነዘር ጥቃት ለማምለጥ መከራን የቀመሰው ቅዱስ ዮሴፍ፣ በጦርነት እና በድህነት ምክንያት ችግር እና መከራ የሚደርስባቸውን ፣ አገራቸውን እና ቤት ንብረታቸውን ጥለው የሚሰደዱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ከአደጋ ጠብቆ ወደ ሰላማዊ ሥፍራ እንዲያደርሳቸው እንለምናለን . . . "።    

23 June 2020, 19:56