ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮድ በብራዚል የአፐሬሲዳ የእመቤታችን ቅድስት ድንግ ማርያም ሐውልት ይዘው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮድ በብራዚል የአፐሬሲዳ የእመቤታችን ቅድስት ድንግ ማርያም ሐውልት ይዘው 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ብራዚልን በጸሎታቸው እንደ ሚያስታውሱ ገለጹ!

በሰኔ 04/2012 ዓ.ም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና በብራዚል የአፓሬሲዳ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሆኑት አቡነ ኦርላንዶ ብራንዲስ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እና ሞት እየተከሰተባት ለሚገኘው ለብራዚል ለየት ባለ ሁኔታ ጸሎት እንደ ሚያደርጉ ቅዱስነታቸው መናገራቸው የተገለጸ ሲሆን በዚህ አስከፊ በሆነ ወቅት ሁሉም የብራዚል ዜጎች በብራዚል አገር ከፍተኛ ክብር ለሚሰጣት ለአፔረሲዳ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጸሎት እንዲያደርጉ  ቅዱስነታቸው ምክረ ሐሳብ ማቅረባቸው ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ፍቅርን፣ መተባበር እና ጸሎት በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ልንተገብራቸው የሚገባን ጉዳዮች እንደ ሆኑ ቅዱስነታቸው የገለጹ ሲሆን የአፕሬሲዳ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ እና አማላጅነት መጠየቅ ይገባል፣ ይህ በሰኔ 04/2012 ዓ.ም  ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በብራዚል ከአፕሬሲዳ አገረሰብከት ሊቀ ጳጳስ ኮሆኑት ኦርላንዶ ብራንዲስ ጋር በስልክ ያደረጉት ውይይት ዋና ጭብጥ ነው። የኮራና ቫይረስ በብራዚል ብቻ ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ነፍስ የቀጠፈ ሲሆን ወረርሽኙ ከዚህ በላይ የሆነ አደጋ እንደ ሚያስከትል ከወዲሁ ግምት ተሰጥቶታል።

በአፐሬሲዳ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ ስር

“ለብራዚል ሕዝቦች የማደርገው ጸሎት ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በተጨማሪም በልቤ ውስጥ እንደ ማስባቸው ለሁሉም የብራዚል ሕዝቦች ይንገሩልኝ” በማለት ለሊቀ ጳጳስ ኦርላንዶ ብራንዲስ ቅዱስነታቸው በውይይቱ ወቅት መናገራቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በጸሎት ከብራዚል ሕዝቦች ጋር እንደ ሚሆኑ ያረጋገጡ ሲሆን ሁል ጊዜም ቢሆን የብራዚል ሕዝቦች በአፐሬሲዳ እመበታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ እንዲታመኑ አደራ ማለታቸው ተገልጿል።

የጋና ብፁዕን ጳጳሳት መንግስት የቤተክርስቲያን ተቋማትን ለኮርና ሕክምና እንዲጠቀም ፈቃድ ሰጡ!

የጋና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት መንግስት በመላው አገሪቱ የሚገኙትን 13 የቤተክርስቲያኗ የሕክምና መስጫ ተቋማት እና መዋቅሮች ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሕክምና እንዲጠቀምበት መፍቀዳቸው ተገለጸ።

አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

የጋና የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብፁዕን ጳጳሳት በመላው አገሪቷ የሚገኙትን የቤተክርስቲያኗ የሕክምና መስጫ ተቋማት በኮሮና ቫይረስ ለተጠቁ ዜጎች ለይቶ ማቆያ ጣቢያ አድርጎ እንዲጠቀምበት የፈቀዱት ቤተክርስቲያን ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከል መንግሥት እያደረገ የሚገኘውን ጥረት ለመደገፍ የራሷን አስተዋጾ ለማደረግ በማሰብ እንደ ሆነም ተገልጿል።

በተጨማሪም በጋና የሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቁምስናዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያ ችግር ውስጥ የወደቁትን ሰዎች ለመርዳት የበኩላቸውን ጥረት እያደረጉ እንደ ሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን ድጋፍ አጠናክረው እንደ ሚቀጥሉ ብፁዕን ጳጳሳቱ መግለጻቸው ተዘግቧል።

ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረበት እለት ድረስ በጋና 10,358 የሚሆኑት ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው የተገለጸ ሲሆን ይህ ሪፖርት አገሪቷ በአፍሪካ አህጉር በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከፍተኛ ቁጥር የሚገኙባት አራተኛው አገር እንድትሆን እንዳደረጋት ተገልጿል።

12 June 2020, 17:56