ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወረርሽኝ ለተጎዱ ሰዎች ያላቸውን መንፈሳዊ ቅርበት ገለጹ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንቦት 30/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት  የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከደረሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳማንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በጣሊያን እና እንዲሁም በመላው ዓለም እየተከሰተ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሰው ልጅ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደ ገባ የገለጹ ሲሆን በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እየደረሰባቸው የሚገኙ አገራት ጎን በጸሎት ከእነርሱ ጋር እንደ ሆኑ ገልጸዋል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በተጨማሪም ይህ አሁን የምንገኝበት የሰኔው ወር በወር ደረጃ የኢየሱስ ቅዱስ ልብ የሚታወስበት ወር መሆኑን በመልእክታቸው ያስታወሱት ቅዱስነታቸው መሐሪ የሆነው የኢየሱስ ቅዱስ ልብ ምሕረቱን እና ፀጋውን እንዲሰጠን ልንማጸነው ይገባል ብለዋል።     

የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ማብሰሩን የሚገልጸውን ጸሎት ከደገሙ በኃላ ለምዕመኑ ባስተላለለፉት መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ዛሬ ምዕመናን በዚህ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መገኘታቸው የሚያሳየው ይህ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በጣሊያን እያደረሰ የነበረው ጥፋት መቀነሱን እንደ ሚያሳይ የገለጹ ሲሆን በዚህ ሳንዘናጋ ጥንቃቄ ማድረጋችንን መቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በዕለቱ ለተገኙ ምዕመናን ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ገና ሙሉ በሙሉ ድል ስላልተጎናጸፍን ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ እንደ ሆነ አክለው የገለጹ ሲሆን በሽታው በአዲስ መልክ እንዳያገረሽ የበኩላችንን ጥንቃቄ ማድረግ እንደ ሚገባ ገልጸዋል።

በአንዳንድ ሀገሮች ቫይረሱ “የብዙ ሰዎችን ነፍስ መቅጠፉን ቀጥሏል፣ ባለፈው ሳምንት አርብ ቀን ብቻ በአንድ ሀገር ውስጥ በየደቂቃው አንድ ሰው ነፍሱን በወረርሽኙ ምክንያት አቷል፣ ይህም በጣም አሰቃቂ የሆነ ጉዳይ ነው” ብለዋል።

የኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ልብ

በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደ ገለጹት ይህ አሁን የጀመርነው የሰኔ ወር በልዩ ሁኔታ ለክርስቶስ ቅዱስ ልብ የተቀደሰ መሆኑን አስታውሰው “ታላላቅ መንፈሳዊ አስተማሪዎችን እና በማነኛውም የእግዚአብሔር ሕዝብ መካከል አንድነትን የሚፈጥር እምነት ነው” ብለዋል።

“የኢየሱስ ሰብዓዊ እና መለኮታዊ ልብ ሁል ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ምህረት ፣ ይቅር ባይ እና ርህራሄ የምንመጣበት ምንጭ ነው። በእያንዳንዱ የቅዱስ ወንጌል መልእክት ላይ በማተኮር የእያንዳንዱ መልእክት ማዕከል፣ የእያንዳንዱ የኢየሱስ ቃል ትኩረት የእርሱን እና የአባቱን ፍቅር ለመረዳት እንችላለን” ብለዋል።

እኛም ይህንን መተግበር እንችላለን በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ቅዱስ ቁርባንን በማምለክ ለቅዱሳን ምስጢራት ሁሉ ክብር መስጠት እንችላለን፣ ከዛም ልባችን በትንሽ በትንሹ ወደ ፍቅር፣ ታጋሽነት ፣ የበለጠ ለጋስ ፣ የበለጠ ርህሩህ እንዲሆን ማደረግ እንችላለን” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

07 June 2020, 11:14