ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሶሪያ ሰላም እንዲፈጠር እና ለሕዝቡ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሰኔ 21/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ላይ ተንትርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት “ የእግዚአብሔር መልአክ” ማርያምን ያበሰረበትን የብስራተ ግብርኤል ጸሎት ከደረሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ስማንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በመጪው ማክሰኞ በሰኔ 23/2012 ዓ.ም “የሶሪያንና በክልሉ የሚገኙ አገራትን የወደፊት እጣ ፈንታ ወሳኝ የሆኑ እርማጃዎችን ለመደገፍ የሚረዳ አራተኛው የአውሮፓ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስብሰባ እንደ ሚከሄድ ገልጸዋል። የሶሪያ ህዝብ እና የአጎራባች አገራት ህዝቦችን በተለይም ሊባኖስ በኮርና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ምክንያት ከባድ ችግር ውስጥ ለሚገኙት አገራት ይህ ስብሰባ ተጨባጭ የሆነ መፍትሄ ያስገኝ ዘንድ እንጸልይ ብለዋል። ሕጻናት ልጆች የሚበላ ነገር ማግኘት እየተሳናቸው ነው፣ መሪዎች ሰላም የመፍጠር ችሎታቸው ይዳብር ዘንድ እንጽልይ ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቅዱስነታቸው ሳምንታዊ መልእክታቸው በቀጠሉበት ወቅት ለየመን ሕዝቦች ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በየመን በከባድ ሰብዓዊ ችግር በመሰቃየት ላይ ለሚገኙ ሕጻናት እንጸልይላቸው ብለዋል። እንዲሁም በምዕራባዊ ዩክሬን በደረሰው የጎርፍ መጥለቅለቅ ችግር ለተጎዱ ሰዎች የጌታን መጽናኛ እና ወንድማዊ ፍቅሬን ለመግለጽ እወዳለሁ ብለዋል። ቅዱስነታቸው በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ሰላምታን አቅርበው፣ ቡራኬን ከሰጡ በኋላ እነደ ተለመደው እና ዘወትር እንደ ሚያደርጉት “እባካችሁን ለእኔ መጸለይ እንዳትዘነጉ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

28 June 2020, 17:45