ፈልግ

ቅን የሆነው ቅዱስ ዮሴፍ በእግዚኣብሔር እንዴት መታመን እንዳለብን ያስተምረናል! ቅን የሆነው ቅዱስ ዮሴፍ በእግዚኣብሔር እንዴት መታመን እንዳለብን ያስተምረናል! 

ቅን የሆነው ቅዱስ ዮሴፍ በእግዚአብሔር እንዴት መታመን እንዳለብን ያስተምረናል!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማኅበረስብ ክፍሎች ዘንድ ግንቦት 01/2020 ዓ.ም በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ “የማሪያም ወር” በመባል የሚታወቅ ወር ሲሆን አሁንም የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የማኅበረስብ ክፍሎች ዘንድ የግንቦት ወር የመጀመሪያ ቀን የሰራተኞች ቀን የሚከበርበት እለት ነው። ይህ ቀን በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ “ቅን እና የታታሪ” ሰራተኛ አብነት የሆነው የቅዱስ ዩሴፍ አመታዊ በዓል የሚከበርበት ወቅት ነው። በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ቅዱስ ዮሴፍን የሚመለከቱ በርካታ መረጃዎች ባይኖሩም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ኢየሱስ "የአናጢው የዮሴፍ ልጅ" ተብሎ ይጠራል። በእዚህ ረገድ ቅዱስ ዮሴፍ ሥራ ክቡር መሆኑን፣ ሥራ የሰው ልጆች ሕልውና እና ግዴታ ጭምር እንደ ሆነ ያሳየን ቅዱስ ሲሆን የሰው ልጅ የሌሎች ፍጥረታት የበላይ በመሆኑ የተነሳ ይህንን የበላይነቱን ለማኅበረሰባዊ አገልግሎት በማዋል፣ የሰው ልጅ ከፈጣሪው የተቀበለውን ፍጥረታትን በሙሉ በመንከባከብ ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ እና የእግዚኣብሔር የደህንነት እቅድ ተካፋይ ሊሆን እንደ ሚገባው ያሳየን ቅዱስ ነው ቅዱስ ዮሴፍ።

የኢየሱስን ጥበብ በተመለከተ የናዝሬት ሰዎች “ይህ ሰው ይህን ጥበብና እነዚህን ታምራት የማድረግ ኀይል ከየት አገኘ? ይህ የአናጢው ልጅ አይደለምን? የእናቱስ ስም ማርያም አይደለምን?፣ ታዲያ ይህ ሰው ይህን ሁሉ ከወዴት አገኘው?” ስለዚህም ሳይቀበሉት ቀሩ (የማቴዎስ ወንጌል 13:54-57) በማለት የሰጡት ምላሽ የሰው ልጆች ለተለያየ ዓይነት የሥራ ዘርፍ ያላቸውን አመለካከት ያሳያል። ኢየሱስ የአናጢው የዩሴፍ ልጅ በመሆኑ የተነሳ (በእዚያን ወቅት የነበሩ አንጽዎች ያልተማሩ ሰዎች ስለነብሩ) በእዚህም የተነሳ “ይህ የአናጺው ልጅ ኢየሱስ እንዴት እና ከየት ይህንን የመናገር ጥበብ” ከየት አገኘው? በማለት ሲጠይቁ እንሰማለን።

እርግጥ ነው ኢየሱስ የነበረው ጥበብ መለኮታዊ የሆነ ጥበብ ነው፣ ኢየሱስ ብዙን ጊዜ በቅዱስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተናገረው የእግዚኣብሔር ጥበብ የሚገለጸ ራሳቸውን ዝቅ ለሚያደርጉ ሰዎች እንደ ሆነ ይናገራል፣ በእዚህም መሰረት ኢየሱስ አሁንም በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ራሳቸውን ጠበበኛ አድርገው ለሚቆጥሩ ፈሪሳዊያን “የሚናግሩትን በተግባር የማያሳዩ ናቸው” በማለት ብዙን ጊዜ ይተቻቸው እንደ ነበረ ይታወቃል።

“የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ እንዲህ ነው፤ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳይገናኙ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ። በዚህ ሐሳብ ሳለ፣ የጌታ መልአክ በሕልም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፤ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፤ እጮኛህን ማርያምን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ፤ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና። ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና” 

ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤ “እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር” ማለት ነው። ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቃ፤ ከዚያም የጌታ መልአክ እንዳዘዘው ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት። ይሁን እንጂ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ የተወለደውንም ሕፃን፣ “ኢየሱስ” ብሎ ጠራው (ማቴ 1፡18-24 ).።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

ቅዱስ ዮሴፍ የነበረውን እቅድ እና ተሞክሮ በመመርመር ክርስቲያኖች ሁሉ በእርሱ ጥበባዊ አመለካከት ተሞለተው ሕይወታቸውን  እንዲያመሩ ያስፈላጋል። እርሱ ከአጥማቂው ዮሐንስ እና ከማርያም ጋር በስብከተ ገና ሰሞን ስረዓተ አምልኮ ውስጥ እንዲካተት ከተደረጉ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው፣ ሦስቱም” ትክክለኛ የነበሩ ሰዎች ናቸው። የማይሰብክ ሰው አይናገርም፣ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ፍቃድ ለመፈጸም ይሞክራል። በቅዱስ ወንጌል መንገድ በመጓዝ እና በብጽዕና ይህም “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው ፣ መንግሥተ ሰማያት የእነሱ ናትና” (ማቴ 5፡ 3) የተባለውን በተግባር ይፈጽማል። ዮሴፍ በጣም ድሃ የነበረ ሰው ነበር፣ ምክንያቱም እሱ መሠረታዊ ፍላጎቶችን ብቻ በሟሟላት ይኖር የነበረ ሰው ነው፣ ይህ ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ላይ መታመን እንደ ሚገባቸው ጠንቀቀው የሚያውቁ እና መተማመናቸውን በእርሱ ላይ ብቻ ያደረጉ ሰዎች የሚያሳዩት ድህነት ነው።

በማቴዎስ ወንጌል (1፡18-24) ላይ እንደ ተጠቀሰው የተከሰተው ነገር በሰው ልጅ አመለካከት ሲታይ የሚያሳፍር እና የሚጋጭ ሁኔታን ያቀርባል። ዮሴፍ እና ማርያም ታማኝ እጮኛሞች ነበሩ። እነሱ ገና አብረው መኖር አልጀመሩም ነበር፣ ነገር ግን እርሷ በእግዚኣብሔር ድንቅ ሥራ የተጸነስ አንድ ልጅ በመጠባበቅ ላይ ነበረች። ዮሴፍ በዚህ ፊት ለፊቱ በተጋረጠበት አስገራሚ ሁኔታ ተፈጥሮአዊ በሆነ መልኩ ተጨንቆ ነበር፣ የተፈጠረውን ነገር ስሜታዊ በሆነ መልኩ እና መቀጣጫ በሆነ መልኩ ለክስተቱ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሰብዓዊ መብትን ከግምት ባስገባ መልኩ እና ተወዳጅ እጮኛው የነበረችውን ማርያምን ባካተተ መልኩ መፍትሄ ይፈልጋል። ቅዱስ ወንጌል “እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ” (ማቴ 1፡19) በማለት ይናገራል። በእውነቱ ቅዱስ ዮሴፍ በተከሰተው ሁኔታ የተነሳ ማርያምን ወደ ፍርድ ቤት አቅርቧት ቢሆን ኖሮ በእርሷ ላይ ከባድ ችግሮች እና መዘዞች እንደ ሚከተሉ፣ አልፎ ተርፎም እስከ ሞት ድረስ የሚያደርሳት ተጋላጭነት እንደ ሚያጋጥማት በደንብ ይገነዘባል። እርሱ እጮኛ አድርጎ በመረጣት በማርያም ላይ ሙሉ እምነት ነበረው።

ሆኖም ይህ በእዚህ እንዳለ አሁን የተፈጠረው ነገር በቃላት ሊገለጽ በማይቻል መልኩ (ማርያም እና ዮሴፍ) የነበራቸውን ግንኙነት በተለይም ዮሴፍ እንዲጠራጠር ያደርገዋል።  ስለሆነም በሁኔታው የተነሳ ዮሴፍ ታላቅ ስቃይ ውስጥ የገባ ሲሆን በማርያም ላይ ከፍተኛ የሆነ አደጋ በማያስከትል መልኩ ከእርሷ ለመራቅ ወሰነ። ነገር ግን የእግዚአብሔር መልአክ እርሱ ማለትም ዮሴፍ ለራሱ ያቀረበው የመፍትሄ ሐሳብ የእግዚኣብሔር ፍቃድ እንዳልሆነ ጣልቃ በመግባት ይነግረዋል። በተቃራኒው ጌታ ለእርሱ የኅብረት ፣ የፍቅር፣ በአዲስ መልክ ደስታ እና አዲስ አንድነት መፍጠር የሚያስችል መንገድ ይከፍታለታል “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፤ እጮኛህን ማርያምን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ፤ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና” (ማቴ 1፡21) በማለት ይነግረዋል።

በዚህን ጊዜ ዮሴፍ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔርን አመነ፣ ለመላእክቱ ቃል በመታዘዝ ማርያምን ወሰዳት። በእርግጥ ይህ ዮሴፍ በእግዚአብሄር ላይ የነበረው የማይናወጥ እመነት ለሰው ልጅ አስተሳሰብ  አስቸጋሪ እና ለመረዳት አዳጋች የሆነውን ሁኔታ እንድንገነዘብ እድሉኑን ሰጥቶታል። በማርያም ማህፀን ውስጥ ተጸንሶ የሚገኘው ሕጻን ልጅ የእርሱ ልጅ አለመሆኑን በእምነት አማካይነት የተረዳ ሲሆን ነገር ግን ልጁ የእግዚኣብሔር ልጅ መሆኑን አውቆ እርሱ ማለትም ዮሴፍ ምድራዊ አባቱ በመሆን ሙሉ በሙሉ ለሕጻኑ እንክብካቤ ማድረግ እንደ ሚገባው ተረዳ። ይህ ቅን እና የዋህ የሆነ ሰው ያሳየን መልካም አብነት እይታችንን ከፍ እንድናደርግ እና አሻግረን እንድንመለክት ያሳስበናል። ራሳችንን አዲስ ለተከፈተው አድማስ ለክርስቶስ እና ለቃሉ ክፍት በማደረግ ከትናንሽ ይሁን ከትላልቅ ስሌቶች በጣም ሩቅ የሆነውን የእግዚአብሔርን አስገራሚ አመክንዮ መረዳት የምንችልበትን ጸጋ ልንጠይቅ የገባል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ንጹህ የሆነው እጮኛው ቅዱስ ዮሴፍ፣ ኢየሱስን ለማዳመጥ፣ እንዲሁም በራሳችን እቅዶስች እና በምርጫዎቻችን ውስጥ ሳይቀር እርሱን ተሳታፊ ይሆናን እንድትረዳን አማላጅነቷን ልንማጸን ይገባል።

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በታኅሳስ 12/2012 ዓ.ም ካዳረጉት አስተምህሮ የተወሰደ።

የቫቲካን ዜና

01 May 2020, 19:24