ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም የስደተኞች ቀን በቫቲካን በመስዋዕተ ቅዳሴ በተከበረበት ወቅት ለስደተኞች ሰላምታ ሲያቀርቡ! ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እ.አ.አ በ2018 ዓ.ም የስደተኞች ቀን በቫቲካን በመስዋዕተ ቅዳሴ በተከበረበት ወቅት ለስደተኞች ሰላምታ ሲያቀርቡ! 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም አመሰገኑ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል ለሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ዋና ዳይሬክተር ለሆኑት ለአባ ሪፓሞንቲ በጻፉት መልእክት ይህ በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጥላ ስር የሚተዳደረው ተቋም ለስደተኞች እና ለጥገኝነት ጠያቂዎች ተቋሙ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያበረከተ ለሚገኘው አገልግሎት ምሳጋና ማቅረባቸው የተገለጸ ሲሆን የእዚህ ተቋም “ተቀብሎ የማስተናገድ ባህል” መልካም ምሳሌ ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል ተግባር መሆኑን የገለጹ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከሚሰደዱ ሰዎች ጋር በጸሎቴ እና በፍቅር ለእነርሱ ቅርብ መሆኔን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል።

የቫቲካን ዜና

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ከጥቂት ቀናት በፊት ባወጣው አመታዊ ሪፖርት “የታገዱ ህይወቶች” በሚል አርዕስት ስደተኞችን በተመለከተ ባወጣው ዘገባ እንደ ገለጸው በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የስደተኞችን እለታዊ እንቅስቃሴ እና የዕለት ተዕለት ኑሮን የሚያግድ ወይም የሚያዘገይ፣ እንዲሁም በዕለት ተዕለት ኑሮ ምክንያት  እየተናወጡ ስለሚገኙ ሰዎች እየደረሰባቸው ስላለው አለመረጋጋት በተመለከተ የሚናገር ዘገባ እንደ ሆነም ተገልጿል። እ.አ.አ በ 2019 ዓ.ም በማዕከሉ 20 ሺህ ስደተኞች ከተቋሙ ጋር ግንኙነት ማደረጋቸው የተገለጸ ሲሆን ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ጨምሮ በሮሜ ከተማ ውስጥ ብቻ 11 ሺ ስደተኞች እንደ ነበሩ ተቋሙ በዘገባው አስፍሯል። እናም ይህ በቅርቡ ይፋ የሆነው መረጃ እንደሚገልጸው አስቸኳይ የሆነ እርምጃ ካልተወሰደ  በስተቀር “ስደተኞችን በተመለከተ ያለው ፖለቲካ፣ የሚጣሉ ገደቦች፣ ድንበር መዝጋት . . . ወዘተ የመሳሰሉ ጉዳዮች ከአሁኑ አግላይ ያልሆኑ ፍትሃዊ ውሳኔዎች ካልተወሰዱ በስተቀር መገለል እና መደበኛ ያልሆኑ ሁኔታዎችን እንደ ሚያባብሱ፣ ይህም መላውን ማህበረሰብ ይበልጥ ተጋላጭ እንደ ሚያደርገው” ሪፖርቱ በስፋት ይገልጻል።

በወንድማማች ፍቅር ስደተኞችን መቀበል

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ዳይሬክተር ለሆኑት ለአባ ካሚሎ ሪፓማኖቲ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባስተላለፉት መልእክት በሪፖርቱ ላይ የተጠቀሰውን “ይህ ጽህፈት ቤት በተለይም በዚህ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የስደተኞችን የጥገኝነት ጥያቄ መብት ለማስከበር በዚህ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት እያደረገው የሚገኘውን በትጋት ያታገዘ ተግባር” በመጥቀስ ቅዱስነታቸው ያደነቁ እና ያመሰገኑ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ጥገኝነት የማግኘት መብት እንዲያገኙ ተቋም በማስቻሉ አመስግነው ጦርነትን፣ ረሃብን፣ ከባድ የሆነ ሰባዊ ቀዎስን በመሸሽ ወደ ተለያዩ አገራት የሚሰደዱትን ስደተኞች ተቀብሎ ማስተናገዱን እንዲቀጥል ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አክለው ገልጸዋል። በተጨማሪም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌ “ስደተኞችን” በተመለከተ ከሰጠው ትርጓሜ ጋር ከሞላ ጎደለ እንደ ሚስማሙ የገለጹ ሲሆን በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ሰራተኞች ለስደተኞች ትኩረት በመስጠት በወንድማማችነት ፍቅር እንዲቀበሏቸው ቅዱስነታቸው ጥሪ አድርገዋል። ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው ጨምረው እንደ ገለጹት እኔ በመንፈስ ለሁሉም ሰው ቅርብ ነኝ እናም በጸሎት እና በፍቅር ከእናንተ ጋር መሆኔን ለማረጋገጥ እወዳለሁ ብለዋል። በሰዎች መካከል ሰላም፣ ፍትህ እና ቅንነት በሌለበት ዓለም ውስጥ እምነት እና ተስፋ እንዲኖር ማድረግ  ተገቢ ነው በዋል። ፡፡

የአንድነት ምሳሌ

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “JRS” በመባል የሚታወቀው የኢየሱሳዊያን ማሕበር የስደተኞች አገልግሎት መስጫ ተቋም ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት መልእክት ማቢቂያ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እንደለጹት “እናንተ እያከናወናችሁት የምትገኙት በጎ ተግባር በዓለም ውስጥ እውነተኛ የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ እና የእንግዳ መቀበል ባህል እንዲኖር የሚያስችል መንፈስ እንዲፈጠር ሊያነቃቃ ይችላል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

29 May 2020, 20:15