ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ቤተክርስቲያን ለተልዕኮ ዝግጁ የሆነች ልትሆን ይገባታል” አሉ!

ር.ሊ.ጳ ፍርንቸስኮስ ዘወትር እሁድ እለት በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለሚሰበሰቡ ምዕመናን በእለቱ ቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ሚያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በመላው ዓለም በተከሰተው እና የብዙ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለወራት ያህል ተዘግቶ በነበረው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከፈተበት ወቅት በስፍራው ለተገኙ ምዕመናን ቅዱስነታቸው አስተንትኖ ማደረጋቸው ተገልጿል። ቅዱስነታቸው በዕለቱ ያደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በግንቦት 23/2020 ዓ.ም በተከበረው የበዓለ ሃምሳ ወይም የጴንጤቆስጤ በዓል ዙሪያ ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን “ቤተክርስቲያን በእርቅ መንፈስ የተሞላችን እና ለተልዕኮ ዝግጁ የሆነች ልትሆን ይገባታል” ማለታቸው ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን አስተንትኖ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

አሁን የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተከፍቷል፣ ወደ ቀድሞ ስፍራችን መመለስ ችለናል። ይህም አስደሳች ነገር ነው!

በመጀመሪያው የክርስቲያን ማህበረሰብ ላይ መንፈስ ቅዱስ መውረዱን ለማስታወስ ዛሬ የጴንጤቆስጤ (የበዓለ ሃምሳ ቀንን) እናከብራለን። የዛሬው ቅዱስ ወንጌል (ዮሐንስ 20፡ 19-23) ወደ ፋሲካ በዓል ምሽት ይመልሰናል፣ ደቀመዛሙርቱ በተሸሸጉበት በላይኛው ክፍል ውስጥ ከሙታን የተነሳው ጌታ ኢየሱስ የተገለጠበትን ሁኔታ ያሳየናል። እነርሱም እጅግ በጣም ፈርተው ነበር። እርሱም በመካከላቸው ቆሞ “ሰላም ለእናንተ ይሁን” (ዮሐንስ 20፡ 19) አላቸው። እነዚህ ከሙታን የተንሳው ጌታ “ሰላም ለአንተ ይሁን” በማለት የተነገሩት  የመጀመሪያዎቹ ቃላት ሰላምታ ከመስጠት ባሻገር ትርጉም ያላቸው ቃላት ናቸው፤ እውነቱን ለመናገር እርሱን ብቻውን ጥለውት ሂደው የነበሩ ለደቀመዛሙርቱ ይቅርታ ማደረጉን ያሳያል። እነዚህ ቃላት የእርቅ እና የይቅርታ ቃላት ናቸው። እኛም ለሌሎች ሰላምታን በምናቀርብበት ጊዜ ይቅር ባዮች እንሆናለን፣ እኛም ብንሆን ለሰራነው ስሕተት ይቅርታ የምንጠይቀበት ሁኔታን ይፈጥራል። ኢየሱስ በፍርሃት ውስጥ ለነበሩ ለነዚህ ደቀመዛሙርቱ ያዩትን ለማመን ማለትም ባዶ መቃብር በመመልከታቸው የተነሳ ለማመን ለከበዳቸው ደቀመዛሙርቱ፣ የመቅደላዊት ማርያም እና የሌሎች ሴቶች ምስክርነት በቸልተኝነት መንፈስ ለተመለከቱ ደቀመዛሙርቱ ሰላምታን ያቀርብላቸዋል። ኢየሱስ ይቅር ይላል ፣ ሁልጊዜም ይቅር ይላል፣ ለወዳጆቹ ሰላም ይሰጣል። መዘንጋት የለብንም- ይቅርታ መጠየቅ የምንታክተው እኛ ነን እንጂ ኢየሱስ መቼም ቢሆን ይቅርታ ማደረግ ታክቶ አያውቅም።

በዙሪያው ያሉትን ደቀመዛሙርት ይቅር በማለት እና በመሰብሰብ ፣ ኢየሱስ አንድ ቤተክርስቲያን፣ የራሱ የሆነች ቤተክርስቲያን ይመሰርታል፣ ይህም በእርቅ መንፈስ የተሞላ እና ለተልዕኮ ዝግጁ የሆነ ማህበረሰብ ነው። እንደገና ከእርሱ ጋር በእርቅ መንፈስ የተሳሰረ እና ለተልዕኮ ዝግጁ የሆነ ማሕበረሰብ ነው።  አንድ ማህበረሰብ በእርቅ መንፈስ ካልታጀበ ለተልእኮው ዝግጁ አይደለም፤ በራሱ ውስጥ ለመወያየት ዝግጁ ነው ፣ ለውስጣዊ [ውይይቶች] ዝግጁ ነው እንጂ ለተልእኮው ዝግጁ አይደለም። ከሙታን ከተነሳው ጌታ ጋር መገናኘታቸው ዝቅተኛ የነበረውን የሐዋርያቱን ስሜት ከፍ በማደረግ ደፋር ምስክሮች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በመሠረቱ  ወዲያውኑ “አብ እኔን እንደ ላከኝ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” (ዮሐንስ 20፡ 21) በማለት ይናገራል። እነዚህ ቃላት ሐዋርያት ለኢየሱስ አደራ የሰጠውን አንድ ዓይነት ተልእኮ ለማሳደግ የተላኩ መሆናቸውን ግልፅ ያደርጉታል። “እኔ እልካችኋለሁ” የሚሉት ቃላት የዚያን ጊዜ መልካም ወቅት ነበር በማለት ብቻ ራሳችንን በራሳችን ቆለፈን መቀመጥ ማለት አይደለም፣ ባለፉት መልካም ነገሮች መቆጨት ማለትም አይደለም። የትንሳኤ ደስታ ታላቅ ነው ፣ ነገር ግን እሱ ራሱ መቀመጥ የለበትም ፣ እሱ መስጠት ነው የሚገባው። በፋሲካ ወቅት በነበሩት እለተ ሰንበት ይህንን የመሳሰሉ ተመሳሳይ የሆኑ ትዕይንቶችን አዳምጠናል።  ከኤማሁስ ደቀመዛምቶች ጋር የተደረገ ግንኙነት፣ ከዚያም በኋላ ደግሞ መልካሙ እረኛ፣ የኢየሱስን የስንብት ንግግሮች እና መንፈስ ቅዱስ እልክላችኋለሁ ብሎ ቃል የገባልንን የቅዱስ ወንጌል ክፍል አዳምጠናል፣ ይህ ሁሉ የተደረገው የደቀመዛሙርቱን እምነት ለማጠንከር ነው፣ ከተልእኮው አንፃር ስንመለከት የእኛንም እምነት ለማጠንከር የተደረገ ነው።

ተልእኮውን ለማነቃቃትም ፣ ኢየሱስ ለሐዋርያቱ መንፈሱን ቅዱስ እንደ ሰጣቸው ቅዱስ ወንጌል እንዲ በማለት ይናገራል፤ “እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ” (ዮሐንስ 20፡22) እንዳላቸው ይናገራል። መንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን የሚያቃጥል እና ሰዎች እንድንሆን የሚያደርገን እሳት ነው፣ ደቀመዛሙርቱ በዓለም ውስጥ እንዲቀጣጠል  ሊለኩሱት የሚችሉት የፍቅር እሳት ነው፣ ይህም ዝቅተኞችን፣ ድሆችን ፣ የተገለሉትን የሚደግፍ የርህራሄ ፍቅር ነው። በምስጢረ ጥምቀት እና በምስጢረ መሮን አማካይነት መንፈስ ቅዱስን እና የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የሆኑትን ጥበብ፣ እውቀት፣ እምነት፣ ብልህነት፣ ምክር ፣ ብርታት ፣ እግዚአብሔርን መፍራት የመሳሰሉ ስጦታዎችን ተቀብለናል። ይህ የመጨረሻው ስጦታ - እግዚአብሔርን መፍራት የሚለው ከዚህ በፊት ደቀመዛሙርቱን ሽባ ያደረገው ፍርሃት ተቃራኒ የሆነ ነገር ነው ፣ ለጌታ ያለን ፍቅር የርሱ ምሕረት እና መልካምነት እርግጥ መሆኑን  መገንዘብ ይኖርብናል። ምህረቱ እና ቸርነቱ ፣ የእርሱን እና የእርሱን ድጋፍ ሳያቋርጥ በእሱ በተጠቀሰው አቅጣጫ ለመንቀሳቀስ የሚያስችል መተማመን ነው።

የጴንጤቆስጤ በዓል መንፈስ ቅዱስ ሕይወት ሰጪ መሆኑና በእኛ ውስጥ እንደሚኖር መገንዘብ እንችል ዘንድ ግንዛቤያችንን ያድሳል። እኛ በምቾት ተከበን ከምንኖርበት ስፍራ ውጥተን በብርታት እርሱን መመስከር እንችል ዘንድ ያደርገናል። አሁን ሀሳባችንን ወደ ማርያም እናድርግ፣ እጅግ ቅድስት የሆነችው እርሷ መንፈስ ቅዱስ በወረደበት ወቅት እዚያ ከሐዋርያቱ ጋር ነበረች፣ በመሆኑም ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ታግዛ ሚሲዮናዊ ሕይወቷን በብርታ ትቀጥል ዘንድ እርሷ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንድትረዳን አማላጀነቷን በመማጸን ወደ እርሷ መጸለይ ይኖርብናል።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
31 May 2020, 14:50