ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “በእምነት የምደረግ ጩኸት የእግዚአብሔርን ልብ ይነካል” አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደምያደርጉ የሚታወቅ ሲሆን በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በሚያዝያ 27/2012 ዓ.ም  በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ከሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ ያደረጉት ሳምንታዊ አስተምህሮ በተለያዩ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች መተላለፉ ተገልጹዋል። በወቅቱ ቅዱስነታቸው ያደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በማርቆስ ወንጌል (ማርቆስ 10፡ 46-52) ላይ በተጠቀሰውና ኢየሱስ ዐይነ ስውሩን በርጤሜዎስን መፈወሱን በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚሁ በጸሎት ዙሪያ ላይ በአዲስ መልክ በጀመሩት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ “በእምነት የምደረግ ጩኸት የእግዚአብሔርን ልብ ይነካል” ማለታቸው ተገልጿል።

የቫቲካን ዜና

በእለቱ የተነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል

ኢየሱስ ዐይነ ስውሩን በርጤሜዎስን ፈወሰ

ከዚህ በኋላ ወደ ኢያሪኮ መጡ። ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ከብዙ ሕዝብ ጋር ከኢያሪኮ ሲወጡ ዐይነ ስውሩ የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ በመንገድ ዳር ተቀምጦ ይለምን ነበር። እርሱም የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን በሰማ ጊዜ፣ “የዳዊት ልጅ፣ ኢየሱስ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ ይጮኽ ጀመር። ብዙዎችም ዝም እንዲል ገሠጹት፤ እርሱ ግን፣ “የዳዊት ልጅ ሆይ፤ ማረኝ!” እያለ የባሰ ጮኸ። ኢየሱስም ቆም ብሎ፣ “ጥሩት” አላቸው።

እነርሱም ዐይነ ስውሩን፣ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል!” አሉት። እርሱም ልብሱን ጥሎ ብድግ በማለት፣ ተነሥቶ ወደ ኢየሱስ መጣ። ኢየሱስም፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” አለው። ዐይነ ስውሩም፣ “መምህር ሆይ፤ እንዳይ እፈልጋለሁ” አለው። ኢየሱስም፣ “ሂድ፣ እምነትህ አድኖሃል” አለው፤ ወዲያውም ዐይኑ በራለት፤ በመንገድም ኢየሱስን ተከትሎት ሄደ። (ማርቆስ 10፡ 46-52)

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያደረጉትን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንድምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ በጸሎት ጭብጥ ላይ አዲስ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንጀምራለን። ጸሎት የእምነት እስትንፋስ ነው ፣ ይህም የጸሎት ትክክለኛው መገለጫ ነው። እምነት ካለው እና  በእግዚአብሔር ከሚታመኑ ሰዎች ልብ የሚወጣን ጩኸት ይመስላል።

እስቲ በዛሬው ዕለት በተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን የበርጤሜዎስ ታሪክ ባህሪይ እናስብ (ማርቆስ 10፡ 46-52 ይመልከቱ) ፡፡ ዓይነ ስውር የነበረ እና በኢያሪኮ ከተማ ዳርቻ ባለው ጎዳና ላይ ምጽዋዕት የሚለምን ሰው ነበር። እሱ ስም-አልባ ገጸ-ባህሪይ አይደለም፣ ስም አለው “የጤሜዎስ ልጅ” ‘በርጤሌሜዎስ’ የሚባል ስም ነበረው። አንድ ቀን ኢየሱስ በእዚያ ሲያልፍ ሰማ። በእርግጥ ኢያሪኮ ነጋዴዎች እና ነጋዲ የነበሩ ሰዎች የሚተላለፉባት ከተማ ነበረች። ከእዚያ በርጤሜዎስ ዕዱሉን ያገኛል ይጮኸል፣ እሱ ኢየሱስን ለማግኘት የተቻለውን ሁሉ አድርጎ ነበር።

ስለዚህ ይህ ሰው ከፍ ያለ ጩኸት የሚያሰማ ሰው ሆኖ ወደ ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ይገባል። እሱ ዐይነ ስውር ሰው የነበረ በመሆኑ የተነሳ ማየት አይችልም፣ ኢየሱስ ቅርብ ይሁን ወይም ሩቅ ማየት ስለማይችል ለመለየት አልቻለም። ነገር ግን መጠኑ እየጨመረ እና ወደ እርሱ እየቀረበ ከመጣው ሕዝብ ኢየሱስ በእዚያ እያለፈ እንደ ሆነ ተረድቷል። ነገር ግን እርሱ ሙሉ በሙሉ ብቻውን ነበረ፣ እናም ማንም ሰው ለእርሱ ግድ አልነበረውም። ታዲያ በርጤሌሜዎስ ምን አደረገ? ጮኸ። በእሱ ውስጥ የነበረውን ብቸኛ የሆነ መሣሪያ ማለትም ድምጹን ይጠቀማል። “የዳዊት ልጅ ኢየሱስ ሆይ ማረኝ!” (ማርቆስ 10፡47) በማለት ይጮኸል ፡፡

የእርሱ ተደጋጋሚ ጩኸቶች ብዙዎቹን ያበሳጫል፣ ብዙዎቹም ይገስጹታል፣ ዝም እንዲል የነግሩታል።  በርጤሌሜዎስ ግን ዝም አላለም፣ በተቃራኒው የባሰ ድምፁን ከፍ አድርጎ ጮኸ “የዳዊት ልጅ ፣ኢየሱስ ሆይ ፣ ማረኝ!” (ማርቆስ 10፡ 47) እያለ መጮኹን ቀጠለ። ይህ “የዳዊት ልጅ” የሚለው አገላለጽ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው ፡፡ ይህ ማለት “መሲህ” ማለት ነው ፣ ይህ ደግሞ በሰው ሁሉ ዘንድ የተናቀ ከነበረው ሰው አፍ የወጣ የእምነት ምስክርነት ነው።  

ኢየሱስም የእሱን ጩኸት ሰማ ፡፡ የበርጤሌሜዎስ ጸሎት የኢየሱስን ልቡ፣ የእግዚአብሔርን ልብ ይነካል፣ ከእዚያን በኋላ ወደ ደህንነት የሚወስደው በር ለእርሱ ይከፈትለታል። ኢየሱስም ቆም ብሎ፣ “ጥሩት” አላቸው። እነርሱም ዐይነ ስውሩን፣ “አይዞህ፤ ተነሥ፤ ይጠራሃል!” አሉት። እርሱም ልብሱን ጥሎ ብድግ በማለት፣ ተነሥቶ ወደ ኢየሱስ መጣ፣ ከእዚህ በፊት ዝም እንዲል ነግረውት የነበሩት ሰዎች አሁን ወደ ጌታ ያመጡታል። ኢየሱስ አነጋገረው ፣ ፍላጎቱን እንዲገልጽለት ጠየቀው - ይህ አስፈላጊ ነው - ያ ጩኸት ወደ ጥያቄ ይለወጣል ኢየሱስም “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” በማለት ጠየቀው ዐይነ ስውሩም፣ “መምህር ሆይ፤ እንዳይ እፈልጋለሁ”  (ማርቆስ 10፡51) በማለት ይመልሳል።

ኢየሱስ “ሂድ እምነትህ አድኖሃል” (ማርቆስ 10፡ 52) አለው።  ይህ ምስኪን ፣ ድሃ ፣ ችላ የተባለ ሰው በነበረው ጠንካራ እምነት የተነሳ የእግዚአብሄርን ምህረት እና ኃይል ለመሳብ ችሏል። እምነት ሁለት እጆችን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ፣ የደኅንነት ስጦታ ይሰጠን ዘንድ ለመማጸን የሚጮህ ድምጽ ነው። የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ “ትህትና የፀሎት መሠረት ነው” (ቁጥር 2559) በማለት ይገልጻል። ጸሎት ከምድር ይመጣል፣ ከትህትናም ይወለዳል፣ እርሱም ከመጥፎ ሁኔታችን ፣ ለእግዚአብሔር ካለን የማያቋርጥ ጥማታችን ውስጥ ይወጣል (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁጥር 2560-2561) ።

እምነት ጩኸት ነው፣ ከእምነት ያልሆነ ደግሞ ያንን ጩኸት አፍኖ ይይዛል፣ “ዝምታን” ይመርጣል። እምነት ለምን እንደተፈጠረ ስንገነዘብ ከገባንበት አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ለመውጣት የሚደረግ የተቃውሞ ድምጽ ነው። እምነት-የለሽ ከሆንን ግን የደረሰብንን አሳዛኝ ሁኔታ ተቀብለን እንድንኖር እንገደዳለን። እምነት የመዳን ተስፋ ነው ፣ እምነት ከሌለን ግን የደረሰብንን ክፉ ነገር ተቀብለን መኖር እንጀምራለን።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ በበርጤሌሜዎስ ጩኸት ዙሪያ ላይ ዛሬ የጀመርነው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በእዚሁ መልኩ የጀመርንበት ምክንያት እንደ እርሱ ዓይነት ጩኸት ማሰማት የሚፈልጉ ሰዎች ይኖራሉ ብዬ በማሰቤ የተነሳ ነው።  በርጤሌሜዎስ ብርቱ የነበረ ሰው ነው። በዙሪያው የነበሩ ሰዎች ጩኸት ምንም ፋይዳ እንደሌለው፣ መልስ የማያስገኝ ከንቱ የሆነ ጩኸት እንደ ሆነ፣ ሰውን ከመረበሽ የዘለለ ፋይዳ የማያስገኝ ጩኸት እንደ ሆነ አጥብቀው ቢነግሩትም፣ እርሱ ግን ዝም አላለም። በመጨረሻም እርሱ የፈለገውን አገኘ።

ከተለያዩ የሰው ልጆች አስተሳሰቦች እጅግ ተቃራኒ የሆነ፣ በሰው ልብ ውስጥ የሚጮህ ድምጽ አለ። እዚህ ምድር ላይ ሳለን ጉዞአችንን ትርጉም ባለው መልኩ እንድናደርግ የሚገፋፋን፣ ያለማንም ትዕዛዝ በተከታታይ ከልባችን የሚወጣ ድምጽ አለ፣ በተለይም በጨለማ ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ: - “ኢየሱስ ሆይ ማረኝ! ኢየሱስ ሆይ ለሁላችንም ምህረትን አድርግ! ” በማለት የሚጮኽ ድምጽ አለ።

ግን ምናልባት እነዚህ ቃላት አጠቃላይ ፍጥረታትን የሚወክሉ ቃላት አይደሉም ወይ? ትክክለኛ የሕይወት መስመር ለማወቅ፣ የምሕረትን ምስጢር ለማግኘት ሁሉም እርሱን ይለምናል። ክርስቲያኖች ብቻ አይደሉም የሚጸልዩት፤  ሁሉም የሰው ልጆች ይጸልያሉ። ነገር ግን የጸሎቱ አድማስ ሰፊ ሊሆን ይችላል፣ ቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ እንደ ሚለው “እስከ አሁን ድረስ ፍጥረት ሁሉ በምጥ ጊዜ እንዳለው ሥቃይ በመቃተት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን” (ሮሜ 8፡22) በማለት ይናገራል። አርቲስቶች ብዙውን ጊዜ በፍጥረታት ሁሉ በተለይም ከሰው ልብ ውስጥ የሚወጣውን የዚህ ዝምታ ጩኸት አስተርጓሚዎች ይሆናሉ ፣ ምክንያቱም ሰው  ሁልጊዜ “እግዚአብሔርን ይለምናልና” ነው (የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ቁጥር 2559)።

06 May 2020, 13:49