ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፍሮሲኖኔ ሐዋርያዊ ግብኝት ባደረጉበት ዕለት፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በፍሮሲኖኔ ሐዋርያዊ ግብኝት ባደረጉበት ዕለት፣ 

ር. ሊ. ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ክርስቲያን ደስታ ሊሰማው ይገባል አሉ።

“እግዚአብሔር እና ደስታ” የሚል መጽሐፍ ደራሲ፣ ኪያራ አሚራንቴ ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ባቀረቡት ጥያቄ፣ መላዋ ቤተክርስቲያንን የመምራት ሃላፊነት እና ከፍተኛ የሥራ ጫና እያለብዎት ደስተኛ የሆኑበት ምስጢር ምን ይሆን በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ቅዱስነታቸው ሲመልሱ “ደስታ ለክርስቲና ሕይወታችን ብርሃን የሚሆነን፣ ሰላምንም የሚሰጥ የእግዚአብሔር ስጦታ በመሆኑ አንድ ክርስቲያን ደስተኛ ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የቫቲካን ዜና፤

“ጌታ ሆይ ጤናን ስጠኝ፣ እንድንከባከባትም በሕይወቴ ደስታን ጨምርልኝ የሚለው የቅዱስ ቶማሶ ሞሮ ጸሎት ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጣቸው መሆኑ ሲነገር፣ ቅዱስነታችው ከደራሲ ኪያራ አሚራንቴ ጋር ባደረጉት ውይይት “ደስታ እና ቀልድ እግዚአብሔር ከሚሰጠን ከጸጋ ስጦታዎች ጋር ቅርበት ያላቸው ሰብዓዊ አመለካከቶች ናቸው በማለት አስረድተዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የ“አዲስ አድማስ” ማኅበር መስራች ከሆኑት ከኪያራ አሚራንቴ ጋር የማኅበሩን 25 ዓመት መታሰቢያ በዓል ለማክበር “ቺታ ዴላ” በሚባል የማኅበሩ ዋና ማዕከል ተገናኝተው በተወያዩበት ጊዜ እንደገለጹት ደስታን ለማግኘት ምንም የተለየ ምስጢር የለውም ብለው፣ አክለውም ደስታ ቀልድ እና ፈገግታ እንዲሰማኝ፣ ለአርባ ዓመታት ያህል ለእውነተኛ ክርስቲያናዊ ደስታ ድጋፍ የሚሆነውን የቅዱስ ቶማሶ ሞሮ ጸሎት ሲያዘወትሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ከመጀመሪያው አንስቶ የነበረ ስጦታ ነው፣

ቅድሱነታቸው ከዚህም ጋር በማያያዝ “ደስ ይበላችሁ፣ ሐሴትንም አድርጉ” በሚለው ሐዋርያዊ ቃለ ምዕዳናቸው፣ በአራተኛው ምዕራፍ ላይ ከተገለጹት ርዕሠ ጉዳዮች መካከል የሚገኝ መሆኑንም አስታውሰዋል። ደስታ እና ሰላም የማይነጣጠሉ የእግዚአብሔር ስጦታዎች መሆናቸውን የገለጹት ቅዱስነታቸው የመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንን ለመምራት እስከ ተመረጡበት ጊዜ እና ከአ]ዚያ በኋለም ውስጣዊ ሰላም የሚሰማቸው መሆኑን አስረድተዋል። ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የደስታን ትርጉም ሲያብራሩ፣ ደስታ ማለት በቀልድ ወይም በተመሳሳይ ስሜት ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን፣ ደስታ፣ የቀልድ እን የውስጥ ሰላም ውህደት ነው ብለው፣ ይህም “ምንም እንኳን ለዚህ የተገባሁ ባልሆንም፣ ኃይል እንዲሆነኝ ከእግዚአብሔር የተሰጠኝ የጸጋ ስጦታ ነው” በማለት አስረድተዋል።

ደስታ በሕይወት ለመኖር ያግዛል፣

“አዲስ አድማስ” የተባለ ማኅበር መስራች የሆኑት ኪያራ ሚራንቴ ቅዱስነታቸው ተጨማሪ ሃሳብ እንዲያክሉበት በጠየቋቸው ጊዜ ቅዱስነታቸው እንደተናገሩት፣ ደስታ የሚገኘው በየዕለቱ ከምንማረው የሕይወት ልምድ መሆኑን አስረድተው፣ ይህን ለመማር ራስን ክፍት እና ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል። “ደስታን እንደ እግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ እኖርበታለሁ” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ ይህን ደስታ ሊወስድብኝ የሚፈልግ ክፉ መንፈስ ዘወትር ጥረት ቢያደርግም፣ እግዚአብሔር እጅግ አብዝቶ በነጻ ስለ ሰጠኝ እርሱ ራሱ ይጠብቀዋል ብለዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚለው ማድረግ የሚገባን ሕይወታችንን መጓዝ ያለብን መንፈስ ቅዱስ በሚያሳየን መንገድ መሆን እንዳለበት አስረድተው፣ ፍቅር፣ ደስታ እና ሰላም የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች መሁኦናቸውን አስታውሰዋል። “እግዚአብሔር ታላቅ ነው” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ መንፈስ ቅዱስ ከሁሉ የበለጠ ኃይለኛ በመሆኑ ለክርስትና ጉዟችን የሚያስፈልገንን ጉልበት ሳያቋርጥ ይሰጠናል ብለው፣ ሰላም የእግዚአብሔ ስጦታ እንደሆነ ሁሉ ደስታም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው ብለዋል።

“እኔ ስለማልችን፣ አንተ አድርግልኝ”

አካሄዴ ትክክል መሆን እና አለ መሆን ለማወቅ የሕሊና ምርመራ ማድረግ፣ የልብ ውስጥ ስሜትን መረዳት፣ በልቤ የማስታውሳቸው ሰዎች ማን እንደሆኑ ለይቶ ማወቅ፣ እነዚህ በሙሉ ክፉን እና ደጉን ለይቼ ለማወቅ ያግዙኛል ያሉት ቅዱስነታቸው፣ ከእግዚአብሔር የሚገኝ እውነተኛ ደስታ ለሕይወቴ ብርሃን በመሆን ወደ መልካም ይመራኛል ብለው፣ በተቃራኒው ከሰይጣን የሚገኝ ደስታ ብልጭልጭ እና ለጊዜው ታይቶ ወዲያው የሚጠፋ መሆኑን አስረድተዋል። በስቃይ ጊዜ ደስታ ሊኖረን ይቻላል ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ቅዱስነታቸው ሲመልሱ፣ በስቃይ ጊዜ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመቅረብ ከአቅማችን በላይ የሆነ ነገር ሲያጋጥመን ለእግዚአብሔር አደራ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል።

“ቀልዶችን የመረዳት እውቀት ስጠኝ”

 የ“አዲስ አድማስ” ማኅበር መስራች የሆኑት ኪያራ አሚራንቴ ደስታን አስመልክተው ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ያቀረቡትን ጥያቄ ባጠቃለሉበት ወቅት፣ የቅዱስ ቶማሶ ሞሮን ጸሎት ሲያስታውሱ “እግዚአብሔር ሆይ! ድካምን አስወግዳ ጥንካሬን የምትላበስ ፣ ማማረርን የምትጠላ ነፍስ እና ስለ ራስ ብቻ ከማሰብ ይልቅ ለሌሎችም የምትራራ ነፍስ እንድትሰጠኝ፣ በሕይወቴ የሚያስደስቱኝን የሰዎች ቀልድ የምረዳበት፣ ከተረዳሁ በኋላም ለሎች ማካፈል የምችልበትን ጸጋ ስጠኝ በማለት መጸለይ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል። 

20 May 2020, 16:53