ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ህንጻ ውስጥ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ህንጻ ውስጥ  

“ውዳሴ ለአንተ ይሁን” ሳምንት ከነገ ግንቦት 10-16/2012 ዓ.ም ድረስ እንደ ሚከበር ተገለጸ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በግንቦት  09/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ህንጻ ውስጥ ከሚገኘው ቤተ መጽሐፍት ውስጥ በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ክፍል ላይ መሰረቱን ያደረገ አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ክብር በመስጠት ከሚደገሙ ጸሎቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሰውና በተለይም ክርስቶስ ከሙታን ከተነሳበት የትንሳኤ በዓል ጀምሮ እስከ በዓለ ሃምሳ ድረስ የሚደገመውን “የሰማይ ንግስት ሆይ ደስ ይበልሽ፣ እርሱ እንደ ተናገረው ከሙታን ተነስቷል” የሚለውን ጸሎት እኩለ ቀን ላይ ከደገሙ በኋላ እንደ ተለመደው ቅዱስነታቸው ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልዕክት ከነገ ግንቦት 10/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” ሳምንት መከበር እንደ ሚጀመር የገለጹ ሲሆን በእዚህ ሳምንት ለፍጥረታት በሙሉ እንክብካቤ የምናደርግበት ወቅት እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

የቫቲካን ዜና

“ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” ሳምንት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው በማለት መልዕክታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በዚህ አሁን በኮቪድ -19 ወረርሽኝ በተዋጠው የጋራ ቤታችን በሆነችው ምድራችን እንክብካቤ ማድረግ አስፈላጊነት ጎላ አድርገው ገልፀዋል።

“ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” በሚል አርዕስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የዛሬ አምስት አመት ገደማ ለንባባ ያበቁትን ሐዋርያዊ መልዕክት 5ኛ አመት የመታሰቢያ ቀን አስመልክቶ ይህ የአንድ ሳምንት የ“ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” ሳምንት እንደ ሚከበር ቀድም ሲል መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ቅዱስነታቸው በሳምንታዊ መልዕክታቸው “ወረርሽኝ በተከሰተበት በዚህ ወቅት የጋራ ቤታችንን መንከባከብ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እናውቃለን” ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን እናም እያንዳንዱን ሰው እንዲያስብበት እና እንዲንከባከቡ የሚያግዙ ገንቢ አመለካከቶችን ለመፍጠር እና ለማጎልበት በጋራ ቁርጠኝነት እንዲሠራ ጥሪ አቅርበዋል።

“ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” በሚል አርዕስት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  የዛሬ አምስት አመት ገደማ ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ መልዕክት አምስተኛ አመት ለአንድ ሳምንት ያህል በተለያዩ ምድራችንን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ተግባራትን በመፈጸም እንዲከበር ይህ አሁን መላውን ዓለም እያስጨነቀ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኛ ከመከሰቱ በፊት መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን ለእዚህ አመት የተመረጠው መሪ ቃል ደግሞ “ሁሉም ነገር የተሰላሰለ ነው” የሚል እንደ ሆነ ተገልጿል።

ይህ ሳምንት ከነገ ግንቦት 10-16/2012 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን በቫቲካን ሁለንተናዊ ሰብዓዊ እድገት በበላይነት የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጋር በመተባበር ለአንድ ሳምንት የተዘጋጀ መታሰቢያ ሲሆን ከእዚህ ቀድም የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችን በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት እየደረሰባት ያለውን ውድመት ለመከላከል ከእዚህ ቀድም የተጀመሩ በጎ ተግባራት ለማስተዋወቅ የተጀመረ የለውጥ ጉዞ ቀጣይ ክፍል ሲሆን “በጸሎት ፣ በማሰላሰል እና ለተሻለ ዓለም አብረን በመዘጋጀት በአሁኑ ወቅት ይህንን ቀውስ በጋራ በመዋጋት  የተሻለ የጋራ መኖሪያ መገንባት ይኖርብናል” በማለት ቅዱስነታቸው በመልዕክታቸው አክለው ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” ሳምንት ጋር ሕዝቡ ተባብሮ እንዲሰራ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ በየትኛውም ስፍራ የሚገኙ ክርስቲያኖች በዚህ “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” መንፈስ እንዲያንፀባርቁ እና እርምጃ እንዲወስዱ መጋበዛቸው ተገልጿል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “ውዳሴ ለአንተ ይሁን” በላቲን ቋንቋ “Laudato Sì” በሚል አርዕስት የዛሬ አምስት አመት ገደማ ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ መልዕክት “የጋራ የመኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን እንከባከብ” የሚል ጭብት የያዘ ሐዋርያዊ መልእክት ይፋ ማደረጋቸው ይታወሳል። ይህ ሐዋርያዊ መልእክት ስድስት ምዕራፎችን በውስጥ አቅፎ የያዘ ሐዋርያዊ መልእክት ሲሆን የእዚህ ሐዋርያዊ መልእክት መሪ ሐሳብ የመነጨው ደግሞ እ.አ.አ. በ11ኛው ክፍለ ዘመን በኖረው እና ለተፈጥሮ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ፍቅር ከነበረው ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲሲ ጥሎት ካለፈው አሻራ ሲሆን እርሱም ምድራችንን በተመለከተ ሲናገር “የጋራ ቤታችን፣ ሕይወታችንን የምናጋራት እህታችንና እጆቹዋን ዘርግታ የምታቅፈን ውድ እናታችን” በማለት ምድራችንን ውበት ይገልጽ የነበረ ሲሆን በተጨማሪምጌታዬ ሆይ በምትንከባከበን እና በምታስተዳድረን በቀለማት ባሸበረቁ አበቦች እና ዕጽዋት በተሞላችውና ልዩ ልዩ ፍሬዎችን በምታፈራልን እህታችን እና እናታችን ምድር አማካይነት ተወደስ” በማለት የተፈጥሮን ሥጦታዎን በመመልከት ብቻ የእዚህ ስጦታ ፈጣሪ የሆነውን አምላክን ማወደስ እንደ ሚቻል ይገልጽ ነበር። ምድራችንን መንከባከብ ማለት የአምላክ ስጦታን መንከባከብ ማለት እንደ ሆነ አበክሮ ይገልጻል።

17 May 2020, 18:02