ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “እግዚ/ርን ማየት እንችል ዘንድ ልባችንን ከሚያስቱ ነገሮች ነጻ ማድረግ ይገባል" አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ለሚገኙ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተንተርሰው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በመጋቢት 23/2012 ዓ.ም ያደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ተለመደው እና ዘወትር ረቡዕ እለት እንደ ሚያደርጉት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ አለመከናወኑ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት በጣሊያን እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በስፋት በመስተዋል ላይ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ይህ ቫይረስ እንዳይዛመት ሰዎች በተቻላቸው መጠን በአንድ ቦታ መሰብሰብ የለባቸውም የሚለውን የጤና ባለሙያዎች ምክር ከግምት በማስገባት እርሳቸው በሚኖሩበት የቅድስት ማርታ ቤት ከሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ በቪዲዮ ያስተላለፉት ሳምንታዊ አስተምህሮ እንደነበረ ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በመጋቢት 23/2012 ዓ.ም ያደረጉት የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በማቴዎስ ወንጌል 5፡ 1-11 ላይ በተጠቀሰው ኢየሱስ በተራራ ላይ ባደርገው ስብከት ላይ መሰርቱን ካደረገው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ በሚገኘው ወደ ብጽዕና መንገድ የሰው ልጆችን ማድረስ በሚችለው ኢየሱስ ባስተማረው “ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው” በሚለው ጭብጥ ዙሪያ ላይ ባደርጉት አስተምህሮ “እግዚአብሔርን ማየት እንችል ዘንድ ልባችንን ከሚያስቱ ነገሮች ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 23/2012 ዓ.ም ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞች እና እህቶች እንደምን አረፈዳችሁ!

ዛሬ (መጋቢት 23/2012 ዓ.ም) የእግዚአብሔር ራዕይ እንዲገለጽልን ሊያደረግ የሚችለውን ቅድመ ሁኔታ የልብ ንፅህናን የተመለከተውን በተራራ ላይ በተደረገው ስብከት ውስጥ በስድስተኛናት የተገለጸውን የብጽዕና መንገድ እንመለከታለን።  መዝሙረ ዳዊት እንዲህ ይላል: - “አንተ ፊቴን እሹት፣ ባልህ ጊዜ አቤቱ ፊትህን እሻለሁ፣ ልቤ አንተን አለ። ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ አትተውኝ። አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ” (መዝ. 27፣8-9)።

ይህ ቋንቋ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ግንኙነት ለመፍጠር ያለንን ጥማት ያሳያል፣ እንዲያው ሳይታሰብ የሚደረግ የይስሙላ ግንኙነት አይደለም፣ እንዲያው በደመና ውስጥ የሚመሰረት ግንኙነት አይደለም፣ በፍጹም እንዲህ አይደለም! ነገር ግን በመጽሐፈ ኢዮብ ውስጥ እንደ ተገለጸው እውነተኛ ግልጽ ነው። መጽሐፈ ኢዮብ እንዲህ ይላል-“መስማትንስ በጆሮ በመስማት ሰምቼ ነበር፤ አሁን ግን ዓይኔ አየችህ” (ኢዮብ 42.5) እንደሚለውም ነው።  እናም እኔ እንደማስበው ብዙን ጊዜ በሕይወት ሂደት ውስጥ እኛ ከእግዚአብሔር ጋር የምንመሰረተው ዓይነት ግንኙነት ነው። በቅድሚያ እግዚአብሔርን የምናውቀው ስለእርሱ ከሰማን በኋላ ነው፣ ነገር ግን ይህንን በመስማት ያገኘነውን እውቀት በሕይወት ተሞክሮዎቻችን እናጠናክረዋለን፣ ቀስ በቀስ ወደ ፊት በምንሄድበት ወቅት በደንብ እያወቅነው እንመጣለን፣ ከእዚያም በኋላ ለእርሱ ታማኝ መሆን እንጀምራለን፣ ከእዚያም በመንፈስ እየበሰልን እንሄዳለን።

ይህንን በጣም ቅርብ የሆነ ግንኙነት ለመመስረት እና እግዚአብሔርን በዓይኖቻችን አይተን ለማወቅ እንችል ዘንድ እዚህ ነጥብ ላይ እንዴት መድረስ እንችላለን? አንድ ሰው ይህንን ለመረዳት ከፈለገ ወደ ኤማሁስ ሲሄዱ የነበሩ ደቀ-መዛሙርት ታሪ በምሳሌነት መውሰድ ይችላል።  ጌታ ኢየሱስ ከአጠገባቸው ነበር “ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር” (ሉቃ 24 16)። የጉዞዋቸው ማብቂያ ከመድረሱ በፊት እና እንጀራውን ከመቁረሱ በፊት ዓይኖቻቸው ከመከፈታቸው በፊት “እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ” (ሉቃ 24፡25) በማለት ይገስጻቸዋል። ይህ ኢየሱስ የተናገረው የመጀመሪያው ተግሳጽ ነው። ዓይነ ስውር የሆነ አመጣጣቸው መነሻ ይኸው ነው። ልብ ሞኝ እና ዘገምተኛ በሚሆንበት ወቅት ነገሮች ግልጽ ሁነው አይታዩም። ነገሮች እንደ ደመና ሆነው ነው የሚታዩን። በእዚህ የተራራው ላይ ስብከት ውስጥ አንድ ጥበብ አለ፣ በሚገባ ማሰላሰል እንችል ዘንድ ወደ ውስጣችን በጥልቀት መግባትና ለእግዚአብሔር ቦታ ማመቻቸት አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ቅዱስ አጎስጢኖስ እንደሚለው "እኔ ለራሴ ቅርብ ከመሆኔ የበለጠ እግዚአብሔር ለእኔ የበለጠ ቅርብ ነው" ይል ነበር። እግዚአብሔርን ለማየት መነጽራችንን መቀየር ወይም የመመልከቻ ቦታን መለወጥ ወይም መንገዱን የሚያስተምሩ የሥነ-መለኮት መምህራንን መለወጥ አያስፈልግም -ልባችንን ከሚያስቱ ነገሮች ነፃ ማውጣት አለብን! ይህ ብቸኛው መንገድ ነው።

በጣም ወሳኝ የሆነ ጠላታችን ብዙውን ጊዜ በልባችን ውስጥ ተደብቆ እንደ ሚኖር ስንገነዘብ ወሳኝ የሆነ ደረጃ ላይ ደርሰናል ማለት ነው። በጣም የተከበረው ውጊያ ኃጢአታችን ከሚያስከትለው ውስጣዊ ማታለያዎች ጋር የሚደረግ ጦርነት ነው። ምክንያቱም ኃጢአቶች ውስጣዊ እይታን ይለውጣሉ፣ ነገሮችን የምንገመግምበትን ሁኔታ ይለውጣሉ፣ እውነት ያልሆኑትን ነገሮች ያሳያሉ ፣ ወይም ቢያንስ እውነት ያልሆኑ ነገሮችን እውነት አድርገው ያቀርባሉ።

ስለሆነም “የልብ ንጽሕና” ምን ማለት እንደሆነ መረዳቱ አስፈላጊ ነው። ይህንን ለማድረግ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ተገለጸው ልብ ስሜትን ብቻ እንደማያካትት መዘንጋት የለበትም፣ ነገር ግን ልብ ለሰው ልጅ በጣም ቅርብ የሆነ ቦታ፣ አንድ ሰው ራሱን የሚገኝበት ውስጣዊ ስፍራ ነው። ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተሳሰብ ነው።

በእዚሁ የማቴዎስ ወንጌል ውስጥ “በአንተ ውስጥ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ ጨለማው እንዴት ታላቅ ይሆናል!” ይላል (6.23)። ይህ “ብርሃን” የልብ እይታ፣ ምልከታ፣ የእይታ ውህደት ነው ፣ እውነታውን እንድናነብ የሚረዳን እና የሚያስሽል ነጥብ ነው።(ሐዋሪያዊ ምዕዳን Evangelii gaudium ቁ. 143)።

ነገር ግን "ንጹህ" ልብ ማለት ምን ማለት ነው? ልቡ ንጹሕ የሆነ በእግዚአብሔር ፊት የሚኖር ነው፣ ከእርሱ ጋር ላለው ግንኙነት ተገቢ የሆነ ልብ ያለው ሰው ማለት ነው። በዚህ መንገድ ብቻ “የተዋሃደ”፣ ቀጥተኛ፣ ቅረበት ያለው ሕይወት፣ መሰረታዊ የሆነ እና የተሳቀቀ ሳይሆን ቀለል ያለ ልብ ያለው ሰው ማለት ነው።

ስለሆነም ንፁህ የሆነ ልብ ነፃ የወጣ እና ብዙ ነገሮችን መካድ የሚጠይቅ ሂደት ነው። ንጹህ የሆነ ልብ እንዲያው በቀላሉ የሚወለድ አይደለም፣ ውስጥን የማጽዳት ሂደት ይፈልጋል፣ በውስጡ ያለውን ክፉ ነገር መካድ እና ማንጻት ያስፈልጋል፣ ይህም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ተጠቀሰው “የልባችሁን ሸለፈት ግረዙት” (ዘዳግም 10፡16፣ ሕዝ 44.9 ፣ ኤር 4 ፣ 4) የሚለውን መተግበር ያስፈልጋል።

ይህ ውስጣዊ መንጻት በክፉ ተጽዕኖ ስር ያለውን የልብ ክፍል እውቅና ያገናዘበ ነው - “አባት ሆይ ታውቃለህ፣ እንደዚህ ይሰማኛል፣ እንደዚህ አስባለሁ፣ እናም ይህ መጥፎ የሆነ ነገር ነው” - መጥፎውን ክፍል ለይቶ ማወቅ፣ ክፉ ነገር የተጠናወተውን ነገር በሚገባ ለይቶ ማወቅ እና በመንፈስ ቅዱስ በመመራት ቀጣይነት ባለው መልኩ ክፉ ነገሮችን ለይቶ ማወቅ እና እርምጃ መውሰድ። ከታመመ ልብ፣ ኃጢያተኛው ከሆነ ልብ፣ በአጢያት ውስጥ በመሆኑ የተነሳ ነገሮችን በጥሩ ሁኔታ ማየት ከማይችል ልብ እግዚአብሔር ከሚሰጠን የልብ ብርሃን ምልአት እና በመንፈስ ቅዱስ ርዳታ ነጻ መሆን እንችላለን። በዚህ ጉዞ ላይ እኛን የሚመራ እርሱ ራሱ ነው። አዎን በእዚህ መልኩ በሚደርገው የልብ ጉዞ አማካይነት “እግዚአብሔርን ለማየት” እንችላለን።

በዚህ ቅዱስ በሆነው ራዕይ ውስጥ በሁሉም በተራራው ላይ በተደርጉ ስብከት ውስጥ በሚገኙ ብጹዕን እንድንሆን ከሚያደርጉን መስፈርቶች ውስጥ የወደፊቱ ሁኔታ ልኬት፣ ስለሞት፣ የመጨረሻ ፍርድ፣ ስለነፍሳችን እና የሰው ልጅ የመጨረሻ ዕጣ ፈንታ የሚመለከት የስነ-መለኮት አስተምህሮ እንመለከታለን፣ ወደ ምንሄድበት መንግስተ ሰማያት ውስጥ ስለሚገኘው ደስታ እንመለከታለን። ነገር ግን ሌላ አቅጣጫም ይጠቁመና፣ እግዚአብሔርን ማየት ማለት በእኛ ላይ በሚደርሰው ነገር ላይ ያለውን መለኮታዊ ጥበቃ መረዳትን ፣ በቅዱስ ቁርባን ውስጥ መገኘቱን ፣ በወንድሞች ውስጥ መገኘቱን በተለይም በድሆች እና በመከራ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች ውስጥ መገኘቱን ማወቅ ማለት ነው (ማጣቀሻ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ ቁ. 2519 ይመልከቱ)።

በእዚህ የተራራው ላይ ስብከት ክፍል ( ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው) ከሚለው ከእዚህ ትንሽ ከፍ ብሎ ከሚገኘው ወደ ብጽዕና የሚወስዱ አስተምህሮዎች ፍሬ ውጤት ነው፣ ውስጣችን የሚገኙትን መልካም ነገሮች ጥማት ማዳመጥ ከቻልን እና በእርሱ ምሕረት እንደምንኖር ከተገነዘብን ወደ ነጻነት ሕይወት የሚወስደውን የሕይወት ዘመን በቀጣይነት በመከተል ወደ መንግሥተ ሰማይ የሚያመራውን መንገድ እንከተላለን ማለት ነው። ይህ ተግባር ደግሞ ጠንከር ያለ ሥራን የሚጠይቅ ነው፣ ለመንፈስ ቅዱስ ሥራ ራሳችንን ክፍት ካደረግን መንፈስ ቅዱስ የሚሠራው ሥራ ነው። በዚህ ምክንያት በሕይወታችን ውስጥ ከሚከናወነው ተግባር የበለጠ  እግዚአብሔር የሚያከናውነው ተግባር ከሁሉም በላይ ነው - በህይወት ፈተናዎች እና ንፅህናዎች ላይ - እግዚአብሔር ያለው ሚና ከፍተኛ ነው። ይህም የእግዚአብሔር እና የመንፈስ ቅዱስ ተግባር ነው። እኛ በፍጹም መፍራት የለብንም፣ የልባችንን በሮች በሙሉ ሊያነጻ እና ወደ ሙሉ ደስታ ሊቀይረው ለሚመጣው፣ በእዚህ ጎዳና ላይ እንድንጓዝ ለሚረዳን መንፈስ ቅዱስ የልባችንን በር እንክፈትለት።

01 April 2020, 19:56