ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከመቃብር ውስጥ እንኳን ሳይቀር ኢየሱስ ሕይወትን ያመጣል አሉ!

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በሚያዝያ 03/2012 ዓ.ም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት፣ ለመቅደላዊት ማርታም እና እንዲሁም ለሌላኛዋ ማርያም የተገለጸበት የትንሳኤ በዓል በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በሚያዚያ 11/2012 ዓ.ም ምሽት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ እና ጥቂት ምዕመናን በተገኙበት ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም እየተከሰተ በሚገኘው የኮሮና ቫየርስ ወረርሽኝ የተነሳ በወቅቱ በርካታ ምዕመን ይህንን ጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበትን የትንሳኤ በዓል በየቤታቸው ሁነው በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን መስመሮች አማካይነት ለመከታተል መገደዳቸው ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በወቅቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ከሙታን የተነሳው ጌታ አዲስ ተስፋ የመሰነቅ መብት ሰጥቶናል፣ ከመቃብር ውስጥ እንኳን ሳይቀር ኢየሱስ ሕይወትን ያመጣል  ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በሚያዚያ 03/2012 ዓ.ም በትንሳኤ በዓል ዋዜማ ላይ ያደረጉትን ስብከት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

“ሰንበት ካለፈ በኋል” (ማቴ 28፡ 1) ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ሄዱ ፡፡ በፋሲካ ምሽት በተከናወነው ስረዓተ አምልኮ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል የሚጀምረው በዚህ መንገድ ነው። ከስቅለተ ዓርብ ሀሌሉያ እስከምንልበት የፋሲካ ቀን ድረስ ያለውን ምንባብ በጉጉት ስንጠባበቅ ቸል የማንልበት የትንሳኤ ትሪጉም የሚሰጠን ቀን ነው። በዚህ ዓመት ግን ከመቼውም ጊዜ በላይ በቀዳም ሱር (ቅዳሜ እለት) ለየት ያለ ታላቅ ፀጥታ አይተን አልፈናል።  በዚያን ቀን በነበሩ ሴቶች አቋም ውስጥ እራሳችንን አስገብተን መገመት እንችላለን ፡፡ እንደ እኛ እነሱም በዓይኖቻቸው ፊት የነበረውን የመከራ ድራማ በዓይኖቻቸው አይተው ነበር፣ ድንገት የተከሰተ ድንገተኛ ነገር አጋጥሞ ነበር። እነሱ ሞትን አይተው ነበር፣ በእዚህ የተነሳ በልባቸው ውስጥ የሐዘን ሸክም ነበረ። ህመሙ ከፍርሃት ጋር ተደባልቆ ነበር፣ እንደ ጌታ ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ሊገጠመን ይችላል የሚል ስጋት ውስጥ ገብተው ፈርተው ነበር። እንግዲያው ስለ መጪው ጊዜ እና መጪውን ጊዜ እንዴት መልሰው እንደገና መገንባት ስለሚያስፍልግ በእዚህ ሁሉ የተነሳ ፈርተው ነበር። አሳዛኝ ትውስታ፣ ተስፋሳቸው በአጭሩ የተቀጨበት ወቅት ነበር። ልክ እንደኛ ለእነርሱም በጣም ጨለማው ሰዓት ነበር ፡፡

ሆኖም በዚህ ሁኔታ ውስጥ ገብተው እና ፈርተው በእዚህ ምክንያት ሴቶቹ ሽባ ሆነው መቀመጥ አልፈለጉም። ለሐዘንና ለመከራ አልተሸነፉም፣ ራሳቸን በራሳቸው በጭካኔ ቆልፈው አልተቀመጡም ወይም ከእውነታው ለመሸሽ አልፈለጉም። የኢየሱስን በድን ለመቀባት የሚያስችላቸውን ቅመማ ቅመሞችን በቤታቸው እያዘጋጁ ነበር፣ ይህ ደግሞ ቀልል ያለ ነገር ግን ያልተለመደ አንድ ድንቅ የሆነ ነገር እያደረጉ ነበር። ለኢየሱስ የነበራቸውን ፍቅር አላቋረጡም፣ በሐዘን ምክንያት በጨለመው ልባቸው ውስጥ የምህረት ነበልባል አበራ። እመቤታችን በእለተ ቅዳሜ ለእርሷ ለእሱ የተወሰነውን ቀን በጸሎት እና በተስፋ አሳለፈች። በጌታ በመታመን ለሀዘን መልስ ሰጠች። እነዚያ ያልታወቁ ሴቶች በዚያ ሰንበት ምሽት ጨለማ ውስጥ “ለሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ንጋት ” ላይ ታሪክን የሚቀየር ቀን ዝግጅት እያዘጋጁ ነበር። ኢየሱስ በመሬት ውስጥ እንደተቀበረ ዘር በዓለም አዲስ ሕይወት ለማምጣት ሊያብብ ነው፣ እናም እነዚህ ሴቶች በጸሎት እና በፍቅር ይህ የተስፋ አበባ እንዲያብብ ይረዱ ነበር። በእነዚህ አስጨናቂ ቀናት ውስጥ ምን ያህል ሰዎች ናቸው  ልክ እንደ እነዚያ ሴቶች የተስፋን ዘር እየዘሩ የሚገኙት! ቀለል ባለ መልኩ እንክብካቤ በማደረግ፣ ፍቅር በማሳየት እና ጸሎት በማደረግ ሊተገበር ይችላል።

ጎህ ሲቀድ ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ሄዱ ፡፡ እዚያም መልአኩ “አትፍሩ! እርሱ እዚህ የለም ፤ ተነስቷልና ”(ማቴ 28፡ 5-6) በማለት ይነግራቸዋል፡፡ በመቃብር ፊት ቁመው የነበረ ቢሆንም እንኳን የሕይወትን ቃል ይሰማሉ… ከዚያም ለሁሉም ተስፋ ሰጪ የሆነው ኢየሱስ አገኛቸውና “አትፍሩ” (ማቴ 28፡10) በማለት ይናግራቸዋል።  አትፍሩ ወደ ፍራቻ ውስጥ አትግቡ። ይህ የተስፋ መልእክት ነው፡፡ እሱ ለእኛ ዛሬ ይገለጻል።  ዛሬ! እግዚአብሔር ዛሬ ማታ ለእኛ በድጋሚ የሚናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።

ዛሬ ምሽት ከእኛ ፈጽሞ ሊወሰድ የማይችል መሠረታዊ የሆነ መብት አግኝተናል፡ - ተስፋ የማድረግ መብት። ከእግዚአብሄር የሚመጣ አዲስ እና ህያው ተስፋ ነው ፡፡ እሱ እንዲሁ ብሩህ የሆነ አመለካከት ብቻ አይደለም፣ እሱ ጀርባችንን እንዲሁ በለበጣ የሚዳስስ ወይም ባዶ የማበረታቻ ቃል አይደለም። በራሳችን ልናገኘው የማንችለው ከሰማይ የመጣ ስጦታ ነው። በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ እኛ የሰውን ዘር ውበት ላይ ተመርኩዘን እና የማበረታቻ ቃላት ከልባችን እንዲወጡ በመፍቀድ “ሁሉም ደህና ይሆናል” በማለት ደጋግመን በመናገር ላይ እነገኛለን። ነገር ግን ቀናት እያለፉ ሲሄዱ እና ፍርሃት እየጨመረ ሲሄድ ፣ ደፋር የነበረው ተስፋችን እንኳን ሊበተን ይችላል ፡፡ የኢየሱስ ተስፋ የተለየ ነው። ከመቃብር እንኳ ሳይቀር ሕይወትን ስለሚያስገኝ ፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር መልካም ለማድረግ የሚችል ጥንካሬ እንዳለው የሚረዳን እምነት በልባችን ውስጥ የዘራል።

መቃብር ማንም ከገባበት በኋላ ተመልሶ ለመውጣት የማይችልበት ስፍራ ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ተገለጠልን፣ እርሱ ከሙታን የተነሳ ሞት ባለበት ስፍራ አዲስ ሕይወት ለመጀመር ይችል ዘንድ ለእኛ ተነስቷል፣ በድንጋይ ታሽገው በተቀመጡ የመቃብር ስፍራዎች ውስጥ አዲስ ታሪክ ይጀምራል። ማሕተም የተደረገበትን የመቃብሩ መግቢያ የተዘጋበትን ድንጋይ ያንከባለለው እሱ በልባችን ውስጥ ያሉትን ድንጋዮችም ሊያስወግደው ይችላል። ስለዚህ በተስፋ መቁረጥ መንፈስ ውስጥ ገብተን አንሽነፍ፣ ከተስፋችን ፊት ለፊት ድንጋይ አናስቀምጥ። ተስፋ እናደርጋለን ምክንያቱም እግዚአብሔር ታማኝ ነው፡፡ እሱ አልተወንም። እርሱ ሕመማችንን፣ ጭንቀታችንን እና ሞታችንን ለመጋራት  ወደ ሁኔታችን ውስጥ ገባ ፡፡ የእሱ ብርሃን የመቃብር ጨለማን ገለጠ ፣ ዛሬ ያ ብርሃን ወደ በሕይወታችን በጣም ጨለማ ወደ ሆነ ማዕዘኖች እንዲገባ ይፈልጋል ፡፡ ውድ  ወንድሞቼ እና እሕቶቼ! በልብህ ውስጥ ያለው ተስፋ ቢቀብርም እንኳን ተስፋ አትቁረጥ፣ እግዚአብሔር ታላቅ ነው። ጨለማ እና ሞት የመጨረሻ ቃል የላቸውም። በእግዚአብሔር ዘንድ ምንም የጠፋ የለምና በርቱ!

በርቱ።  ይህ በቅዱሳን በወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ ብዙውን ጊዜ የተናገረው ቃል ነው ፡፡ የተቸገረውን ሰው ለማበረታታት ሌሎች የሚናገሩት አንድ ጊዜ ብቻ ሊሆን ይችላል “በርታ፣ ተነስ ፣ ኢየሱስ እየጠራህ ነው! ” (ማርቆስ 10፡ 49) ፡፡ ከችግራችን የሚያነሳን እርሱ ከሙታን የተነሳው ብቻ ነው። በጉዞዎ ላይ ድክመት ወይም ውድቀት የሚሰማህ ከሆንክ፣ የምትፈራ ከሆንክ፣ የእግዚአብሔርን እርዳታ ጠይቅ እርሱም እጁን ይዘረጋልሃል። እጅህን ይዞ “አይዞህ!” በርታ ብሎ ያነሳሃል። “ብርታት ለራሳችን መስጠት የሚንችለው ነገር አይደለም”። እውነት ነው  ለራስህ መስጠት የምትችለው ነገር አይደለም፣ ነገር ግን እንደ ስጦታ ልትቀበለው ትችላለህ፡፡ ማድረግ ያለብን ነገር ቢኖር ልባችንን በጸሎት በመክፈት እና የኢየሱስ ብርሃን ወደ ውስጥ እንዲገባ ለማድረግ በልባችን መግቢያ ላይ የተቀመጠውን ያን ድንጋይ ማንሳት ነው።  እሱን መጠየቅ ያለብን ነገር ቢኖር “ኢየሱስ ሆይ ፣ በፍርሃቶቼ መካከል ወደ እኔ ና እና ብርታት ስጠኝ! ማለት ይጠበቅብናል። ጌታ ሆይ ከአንተ ጋር እንፈተናለን እንጂ አንናውጥም። ምንም ዓይነት ሐዘን ቢደርስብንም በተስፋችን ጠንክረን እንቀጥላለን፣ ምክንያቱም ከአንተ ጋር የምንሸከመው መስቀል  ወደ ትንሣኤ ይመራናልና፣ ምክንያቱም በሕይወታችን ጨለማ ውስጥ አንተ አብረህን ነበርክና። እርግጠኛ ባልሆንበት ስፋራ ውስጥ እርግጠኛ እንድንሆን ታደረገናለህ፣ እናም ለእኛ ከፍተኛ የሆነ ፍቅር ስላለህ አያሳስበንም።

ይህ የፋሲካ መልእክት ፣ የተስፋ መልእክት ነው ፡፡ መልእክቱ በሁለተኛ ክፍል ላይ ኢየሱስ “ሄዳችሁ ለወንድሞቼ ወደ ገሊላ እንዲሄዱ ንገሯቸው” (ማቴ 28፡10) በማለት በተናገረው ቃል ይቀጥላል። መልአኩ “እሱ ከፊታችሁ ቀድሞ ወደ ገሊላ ይሄዳል” (ማቴ 28፡ 7) በማለት ይናገራል። ጌታ ከፊታችን ይሄዳል። በህይወታችን እና በሞት ፊት ከፊታችን ሆኖ እንደ ሚሄድ ማወቁ የሚያበረታታ ነው፣ ለእሱ እና ለደቀመዛሙርቱ የዕለት ተዕለት ኑሮን ፣ የቤተሰብን እና ስራን ሀሳብ ወደ አስተባበሩበት ወደ ፊት ወደ ገሊላ ይሄዳል። በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ኢየሱስ ተስፋን ሊያመጣልን ይፈልጋል። ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን ለመጀመሪያ ጊዜ መርጦ የጠራቸው በገሊላ ከሚገኝበት ስፍራ በመሆኑ የተነሳ ቦታው የመታሰቢያ ስፍራ በመሆኑ የተነሳ አስፈላጊ ነው። ወደ ገሊላ መመለስ ማለት እኛ በእግዚአብሔር እንደተወደድን እና እንደተጠራን ማስታወስ ማለት ነው። በፍቅር ተነሳስተን በነፃ በተሰጠን ጥሪ ምክንያት የተወለድን እና እንደገና በድጋሚ የተወለድን መሆናችንን በማስታወስ ጉዞውን መቀጠል አለብን። በተለይም በችግር እና በችግር ጊዜ እንደገና እንደ አዲስ ሆነን የምንወጣበት ነጥብ ነው ፡፡

ነገር ግን አንድ የቀረ ነገር አለ። ከገሊላ እነርሱ ከነበሩበት ስፍራ ከኢየስሩሳሌም እጅግ ርቆ የሚገኝ ቦታ ነበር። እና በጂኦግራፊያዊ ምልከታ ብቻ አይደለም። ገሊላ ከቅድስቲቷ ከተማ አንጻር ሲታይ የመጨረሻ ስፍራ ነበራት። የተለያየ ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች የሚኖሩበት ስፍራ ነበረች “የአሕዛብ ገሊላ” (ማቴ 4፡15)።  ኢየሱስ ወደዚያ የላካቸው ከዚያ እንደገና እንዲጀምሩ በመጠየቅ ነው። ይህ ምን ይነግረናል? የተስፋ መልእክት ለቅዱሳን ሥፍራዎቻችን ብቻ የተገደበ መሆን የለበትም ፣ ነገር ግን ለሁሉም መቅረብ አለበት። ሁሉም ሰው ማበረታቻ ይፈልጋል ፣ እናም እኛ “የሕይወትን ቃል” የሆነውን እርሱን ነካነው (1 ዮሐ 1፡1) ካልሰጠነው ማን ይሰጣል? የሌሎችን ሸክም የተሸከሙ እና ማበረታቻ የሚሰጡ ፣ የሚያጽናኑ ፣ የሚያምኑ ፣ በሞት ጊዜ የሚያጽናኑ ክርስቲያን መሆን እንዴት ያማረ ነው! በእያንዳንዱ እንደ ገሊላ ባሉ ስፍራዎች፣ በሁሉም ስፍራዎች ውስጥ በሚገኙ ሰብዓዊ ቤተሰቦች ውስጥ የሚገኙ ወንድማማቾች እና እህታማሞች ስለሆንን የሕይወትን ጣዕም ማምጣት እንችል ዘንድ እርሱ እንዲረዳን መጸለይ ይኖርብናል። የሞት ጩኸት ዝም እናሰኝ፣ ጦርነቶች ከእንግዲህ እንዳይኖሩ እናድርግ! ጠመንጃ ሳይሆን እንጀራ ስለሚያስፈልገን የጦር መሳሪያዎችን ምርት እና ንግድ እናቋርጥ፡፡ የንጹሃን ህይወት የሚቀጠፈው ውርጃ እና መግደል ያበቃ። በቂ የሆኑ ነገር ያላቸው ሰዎች ባዶ እጃቸውን የሆኑ ሰዎችን እጆች ​​ለመሙላት ክፍት የሆኑ የሰዎች ልብ ይኑር።

እነዚያ ሴቶች በመጨረሻ “የኢየሱስን እግር ያዙ” (ማቴ 28፡ 9) ፡፡ እኛን ለመገናኘት እስካሁን የተጓዙ እግሮች፣ ወደ መቃብር ከገቡ በኋላ አሁን ደግሞ ከመቃብር መውጣት ጀመሩ። ሴቶቹ ሞትን የተረገጠውን እግሮች ተቀብለው የተስፋን መንገድ ከፈቱ ፡፡ ዛሬ ተስፋን ፍለጋ የምጓዝ ነጋዲያን እንደ መሆናችን መጠን ተስፋችን ከሙታን በተነሳውን ክርስቶስ ላይ እናድርግ። ጀርባችንን ለሞት እንስጥ ልባችንን ለእርሱ እንክፈትለት፣ አንተ ራስህ ሕይወት ነህና።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
11 April 2020, 14:43