ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኙው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኙው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ 

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ይህ ወቅት የግዴለሽነት፣ የራስ ወዳድነት፣ መለያየት ወቅት ሊሆን አይገባም” አሉ

የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር በሚከተሉ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሚያዚያ 04/2012 ዓ.ም በመላው ዓለም በሚገኙ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ ተከብሮ ማለፉ ይታወሳል። ይህ በዓለ በአሁኑ ወቅት በዓለም ደረጃ እይተከሰተ ባለው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከእዚህ ቀደም ይህ በዓል ብዙ ምዕመናን በተገኙበት መልኩ ሊከበር እንዳልቻለ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን ምዕመናን በያሉበት ስፍራ በየቤታቸው ሁነው በማሕበራዊ የመገናኛ መስመሮች አማካይነት ለመከታተል ተገደዋል። ይህ በዓል በሚያዚያ 04/2012 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን የተነሳበት እለት መታሰቢያ ቅዳሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ መሪነት በጣም ጥቂት ምዕመናን በተገኙበት መካሄዱ ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ቅዱስነታቸው መስዋዕተ ቅዳሴያቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እንደ ተለመደ እና ዘወትር በታላላቅ መንፈሳዊ በዓላት በተለይም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት የገና በዓል ቀን እና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በተነሳበት የትንሳኤ ቀን ልማዳዊ በሆነ መልኩ አንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  የተሰኘ መልእክት በዓላቱን አስመልክተው መልእክት እንደ ሚያስተላልፉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በሚያዚያ 04/2012 ዓ.ም  እለት ረፋዱ ላይ በላቲን ቋንቋ Urbi et Orbi በአማሪኛው ለከተማው (ሮም) እና ለዓለም  የተሰኘው ምልእክት ባስተላለፉበት ወቅት “ይህ ወቅት የግዴለሽነት፣ የራስ ወዳድነት፣ መለያየት ወቅት ሊሆን አይገባም”  ብለዋል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በወቅቱ ያስተላለፉትን መልእክት ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው እናቀርብላችኋለን ተከታተሉን።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መልካም ፋሲካ!

ዛሬ የቤተክርስቲያኗ “ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል!” በማለት ያወጀችሁ አዋጅ በዓለም ዙሪያ ያስተጋባል።  “በእውነት ተነስቷል!” ፡፡

ልክ እንደ አዲስ ነበልባል ይህ የምሥራች ቃል ዛሬ ሌሊት አስተጋብቱዋል። ቀድሞዉን የነበረው የዓለም ብርሃን ኃይለኛ ፈተና የገጠመው እና አሁን መላውን ቤተሰባችንን በከፍተኛ ደረጃ ፈተና ውስጥ የከተተው ውረርሽኝ ምክንያት ዓለም እየተዳከመች ትገኛለች፡፡ በዚህ ምሽት “ተስፋችን የሆነው ክርስቶስ ከሙታን ተነስቱዋል” የሚለው የቤተክርስቲያኗ ድምፅ አስተጋብቱዋል።

ይህ የተለየ “ተላላፊ” የሆነ ከልብ ወደ ልብ የሚተላለፈ መልእክት ነው - የሰው ልብ ሁሉ ይህንን የምሥራች ይጠባበቃልና። እርሱም “ተስፋዬ ክርስቶስ ተነስቷል” የሚል ተላላፊ የሆነ የተስፋ ቃል ነው። ይህ ችግሮች እንዲጠፉ የሚያደርግ አስማታዊ ቀመር አይደለም። የለም እንዲህ አይደለም። የክርስቶስ ትንሣኤ ያ አይደለም። ከዚያ ይልቅ በክፉ ሥር ፍቅር የተጎናጸፈውን ድል የሚያሳይ ነው፣ መከራን እና ሞትን “ዘሎ የሚያልፍ” አይደለም፣ ነገር ግን በእነሱ ውስጥ አልፎ በጥልቁ ውስጥ መንገዱን በመክፈት ክፉን ወደ መልካም የሚቀይር ድል ነው፣ ይህ የእግዚአብሔር ሁለንተናዊ ኃይል የሚገለጽበት ነው።

ከሙታን የተነሳው ጌታ ያው እርሱ በመስቀላይ የተሰቀለውን እንጂ ሌላ ሰው አይደለም። ክቡር በሆነ ሰውነቱ የማይታዩ ቁስሎችን ተሸከመ-እነዚህ ቁስሎች የተስፋ መስኮቶች ሆነዋል። የተጎሳቆለውን የሰው ልጅ ቁስል ይፈውስ ዘንድ ዓይናችንን ወደ እርሱ እንመለስ ፡፡

ዛሬ ሀሳቤ በቀጥታ በቅድሚያ የሚሄደው በኩሮና ቫይረስ ወደ ተተቁ ብዙ ሰዎች ነው፣ ለታመሙ፣ ለሞቱ እና የሚወዱትን ሰው በሞት በማጣት በሐዘን የተጎሳቆሉ ለሚገኙ፣ በአንዳንድ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ወደ ሚገኙ ሰዎች፣ በአንዳንድ ምክንያት ቤተሰቦቻቸውን መሰናበት ያልቻሉ ሰዎች ። ህይወት ሰጪ የሆነው ጌታ ወደ ምንግሥተ ሰዋይ የሄዱትን ሁሉ ወደ መንግሥቱ በደስታ ይቀበልልን፣ በሐዝን ምክንያት እስካሁን ድረስ እያዘኑ የሚገኙትን ሰዎች ያጽናናልን፣ ተጋላጭ በሆኑ ስፍራዎች የሚገኙትን ሰዎች በተለይም አረጋውያን እና ብቻቸውን ላሉት መፅናናትን እና ተስፋን ይስጥልን።  በተለይም በአረጋውያን መንከባከቢያ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩት ሰዎች ፣ ወይም በእስር ቤቶች እና በወህኒ ቤቶች ውስጥ ለሚኖሩት ሰዎች ማበረታቻ እና ድጋፍ ፈጽሞ እንዳይለያቸው እንዲረዳቸው እንጸልይ።  ለብዙዎች ይህ የትንሳኤ በዓል ይህ ወረርሽኝ እያመጣ ባለው ሀዘንና ችግር ሳቢያ እየተከሰተ ከሚገኛው አካላዊ ስቃይ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች የተከሰቱበት ብቸኛው በዓል ነው ።

ይህ በሽታ የሰውን ልጅ ቅርርብ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም እኛን ከቅዱሳን ምስጢራት  በተለይም ከቅዱስ ቁርባ እና ከምስጢረ ንስሐን በማግኘት ይመጣ ከነበረው የማበረታቻ እና የመጽናኛ እድል እንዳናገኝ የከለከለ አጋጣሚ ነው። በብዙ አገሮች ውስጥ እነዚህን ቅዱስና የሆኑ ምስጢራትን መቀበል አልቻሉም፣ ነገር ግን ጌታ ብቻችንን አልተወንም! በጸሎት ሕበረት በመፍጠር በጸሎታችን አንድ ስንሆን እጁን በላያችን ላይ እንደሚያሳርፍ እናምናለን (መዝ 138:5) “ተነስ አሁንም እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ!” በማለት ከእኛ ጋር መሆኑን በጥብቅ ያረጋግጥልናል።

ፋሲካችን ኢየሱስ ፣ ለጎረቤቶቻችን እንክብካቤ እና ፍቅር ምስክርነት እስከ መስጠት ድረስ የደረሱ፣ ለአቅመ ደካሞች እና ለፍቅር ምስክርነት ለሚሰጡት ሀኪሞች እና ነርሶች ጥንካሬ እና ተስፋን ይስጥ፣ ምክንያቱም የገዛ ጤንነታቸውን ለድርድር አቅርበዋልና።  ምስጋናችን እና ፍቅራችን ለእነሱ ፣ ለሲቪል ማህበረሰብ አስፈላጊ የሆኑ አገልግሎቶችን ዋስትና ለመስጠት በትጋት ለሚሰሩ ሁሉ ፣ እንዲሁም በብዙ አገሮች ውስጥ የሰዎችን ችግር እና ስቃይ ለማስታገስ በመስራት ላይ ለሚገኙ የሕግ አስከባሪዎች እና የጦር ሰራዊ አባላት እነርሱን እጅግ አድርጌ ላመስገን እወዳለሁ።

በእነዚህ ሳምንታት ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወት በድንገት ተለውል። ብዙዎች በቤት ውስጥ በመቆየታቸው የተነሳ አስተንትኖ ለማደረግ እድሉን ያገኙበት፣ የሕይወት ዘመናቸውን ውስጥ ያለውን የህይወት ደረጃን በመተው ፣ ከሚወዱዋቸው ጋር ለመቆየት እና ከእነርሱ ጋር ለመደሰት ዕድል አግኝተዋል። ለብዙዎች ሰለ መጪው ጊዜ እርገጠኛ ባለመሆናቸው የተነሳ የሚጨንቁበት፣ በአደጋ ላይ ስለወደቁ ሥራዎቻቸው የሚጨናቁበት፣ ስለመጪው ጊዜ እርግጠኛ የማይሆኑበት ጊዜ ነው።  የፖለቲካ መሪዎች ለጋራ ጥቅም በንቃት እንዲሰሩ ፣ ሁሉም የተከበረ ሕይወት እንዲመሩ እና ሁኔታዎች በሚፈቅዱበት ጊዜ መደበኛ የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን እንዲቀጥሉ እንዲረዳቸው የፖለቲካ መሪዎችን አበረታታለሁ ፡፡

ይህ ግድየለሽነት ጊዜ አይደለም ፣ ምክንያቱም መላው ዓለም እየተሰቃየ ስለሆነ እና ወረርሽኙን ለመቋቋም አንድ መሆን ይኖርብናል። ከሞት የተነሳው ኢየሱስ ለሁሉም ድሆች ፣ ተጋላጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች፣ ለስደተኞች እና መጠሊያ ለሌላቸው ሰዎች ጽናት ይስጣቸው።  እነዚህን በከተሞች እና በሁሉም የዓለም ክፍል ውስጥ ባሉ አካባቢዎች የሚኖሩ እና በጣም ተጋላጭ የሆኑ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ቸል እንዳንል። መሠረታዊ ፍላጎቶች አለመኖራቸው (እንደዚሁም በአሁኑ ወቅት ብዙ የንግድ ተቋማት በመዘጋታቸው የተነሳ ሁኔታው በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም) እንደ መድኃኒት እና በተለይም በቂ የጤና መጠበቂያ መሳሪያዎችን በቂ በሆነ ሁኔታ መኖራቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።  እነዚህ ሁኔታዎች ለዜጎቻቸው በቂ ድጋፍ እንዲሰጡ ኃላፊነት የተጣለባቸው ሀገሮች በተጣለባቸው ማእቀብ የተነሳ ሁኔታው አስቸጋሪ ስለሚሆንባቸው የሁሉንም ሕዝቦች ከፍተኛው ፍላጎት ለማርካት በሚያስችላቸው ሁኔታ ውስጥ ስላልሆኑ ከአሁኑ ሁኔታ አንጻር ዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ሊላሉ ይገባል። የድሃ አገሮችን የዕዳ ሚዛን በከፊል እንዲቀንስ ካልሆነም እንዲሰርዙ እጠይቃለሁ።

ይህ የራስ ወዳድነት መንፈስ የምናሳይበት ጊዜ ሊሆን አይገባም፣ ምክንያቱም እያጋጠመን ያለው ተግዳሮት በሰዎች መካከል ልዩነት ሳይፈጠር በሁሉም ዘንድ እየተከሰት እይሚገኝ በመሆኑ ነው። በኮሮና ቫይረስ ከተጎዱ የዓለም ብዙ አካባቢዎች መካከል የአውሮፓ አገር ዋነኛው ይመስለኛል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ይህ ተወዳጅ አህጉር ሁኔታዎችን ለማሸነፍ በሚያስችለው መልኩ ተጨባጭ የትብብር መንፈስ ተመስጦ እንደገና መነሳት ችሏል ፡፡

ብቸኛው አማራጭ የወደፊቱ ትውልድ ሰላማዊ አብሮ የመኖር ልምድ እና የልማት ፍላጎት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉ የራስ ወዳድነት እና የግል ጥቅምን ብቻ የማስከበር ሙከራ ያለፈውን ጊዜ ለመመለስ የሚደረግ ሙከራ ነው።

ይህ መከፋፈል ሊፈጠርበት የሚገባው ወቅት አይደለም። በሁሉም የዓለም ማዕዘኖች ላይ በመካሄድ ላይ የሚገኙ ጦርነቶች ማብቂያ ያገኙ ዘንድ የሚመለከታቸው ኃላፊነት የተጣለባቸው አካላት ክርስቶስ በብርሃኑ ይሙላቸው።  ይህ የጦር መሳሪያ የምናመርትበት ወቅት ሊሆን አይገባም።  ይልቁኑ የጦር መሳሪያ ለማምረት የሚውለው ገነዘብ የብዙሃኑን ሕይወት ለማዳን ሊውል ይገባል። ይልቁንም በሶሪያ ውስጥ እንዲህ ያለ ታላቅ ደም መፋሰስ ያስከተለውን ረጅም ጦርነት መቋጫ እንዲያገኝ ማደረግ ያስፈልጋል። እስራኤል እና ፍልስጤማውያን ሁለቱም በሰላም የሚኖሩበት ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት የሚያስችል ውይይት የሚጀምሩበት በዚህ ጊዜ ይሁን። በዩክሬን ምስራቃዊ አካባቢዎች በሚኖሩት ሰዎች ላይ የሚደርሰው ሥቃይና መከራ ያብቃ። በተለያዩ የአፍሪካ አገራት በብዙ ንጹሀን ሰዎች ላይ የተፈጸሙት የሽብር ጥቃቶች መቋጫ ይበጅላቸው።

ይህ የምንዘናጋበት ወቅት አይደለም። እያጋጠመን ያለው ቀውስ ከእዚህ ቀድም በተለያዩ ከፍተኛ ስቃዮች ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን የምንዘነጋበት ወቅት ሊሆን አይገባውም። በኢስያ እና በአፍሪካ አሕጉር በተለያዩ ሰብዓዊ ችግር ውስጥ የሚገኙትን መዘንጋት አይኖርብንም፣ ሕይወት ሰጪ የሆነው ጌታ እንዲቀርባቸው ጸሎቴ ነው።   በጦርነት ፣ በድርቅ እና በረሃብ ምክንያት ለተፈናቀሉ ብዙ ስደተኞችን ልብ ያሙቅልን። አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች፣ በተለይም ሕጻናት እና አረጋዊያን በከፍተኛ ሁኔታ ታጭቀው የሚኖሩባቸው የስደተኛ መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት ሰዎች ፣ በተለይም በሊቢያ፣ በግሪክ እና በቱርክ መካከል ድንበር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ጌታ በብርሃኑ እንዲረዳቸው እንጸልያለን። በቬንዙዌላ ውስጥ ከባድ የፖለቲካ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እና የጤና ሁኔታ ለሚሰቃየው ህዝብ ዓለም አቀፍ እርዳታ ሊፈቅድ የሚቻልበት ተጨባጭ እና አስቸኳይ መፍትሄዎችን ማግኘት ይችሉ ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢው በሆነ መልኩ ይሰሩ ዘንድ እንማጸናለን።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች

ግዴለሽነት ፣ በራስ ወዳድነት፣ መለያየት እና መዘንጋት በእዚህ አስቸጋሪ ወቅት ልንሰማቸው የምንፈልጋቸው ነገሮች አይደለም። እነዚህን ቃላት ለዘላለም ማገድ እንፈልጋለን! ፍርሃትና ሞት ሊያሸንፉ ያሉን ሊመስለን ይችል ይሆናል፣ ጌታ ኢየሱስ በሕይወታችን ውስጥ እንዲገባ እንፍቀድለት ። ሞትን ቀድሞ ያሸነፈው እና የዘለአለም የድህንነት መንገድ ለእኛ የከፈተልን ክርስቶስ የሰው ልጆችን መካራ አስወግዶ በክብር ወደ ተሞላው ቀን በብርሃን ተሞልተን ወጨረሻ ወደ ሌለው ብርሃን ውስጥ እንድንገባ ይምራን።

12 April 2020, 18:00