ፈልግ

የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች በጋራ አሬቻ  የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች በጋራ አሬቻ  

መንፍሳዊ ጥሪ “እግዚአብሔር ለእኛ የሚናገርበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው”!

የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች በጋራ በመሆን በየወቅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ሱባሄ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት አሁን የምንገኝበትን የዐብይ ጾም ምክንያት በማድረግ ከባለፈው የካቲት 22/2012 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ጣሊያን በምትገኘው አሬቻ በመባል በሚታወቀው ስፍራ የእርሳቸው የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች እና  የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበለይ የመስተዳድር አካላት የዐብይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ሱባዔ በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን የእዚህ አመታዊ ሱባዔ መሪ የሆኑት በጳጳሳዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሚሽን ውስጥ የነገረ መለኮት ትምህርት ምሁር የሆኑት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑ አባ ፔትሮ ቦቫቲ እንደ ሆኑ ቀድም ሲል መግለጻችን የሚታወስ ሲሆን በእዚህ ሱባዔ ሁለተኛ ቀን ላይ የተካሄደው አስተንትኖ ሙሴ እግዚአብሔር በአደራ የሰጠውን ሕዝብ ወደ ተስፋይቱ ምድር በመራበት ወቅት ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ፍላጎት ውጪ የመሄድ ፈተና ገጥሞዋቸው እንደ ነበረ በሚገልጸው ጭብጥ ዙሪያ ላይ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን እኛም በሕይወት ጉዞ ላይ በምንራመድበት ወቅት የሚያጋጥሙንን የሕይወት ፈተናዎች በእግዚአብሔር ኃይል እና ርዳት የምንወጣበትን መንገድ እንዲያሳየን እርሱን ልንማጸነው ይገባል ብለዋል።

የእዚህ ዝግጅት እቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን 

ሰኞ ከሰዓት በኋላ የካቲት 23/2012 ዓ.ም በተካሄደው የሁለተኛ ቀን ሱባዔ አስተንትኖ ላይ በጳጳሳዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሚሽን ውስጥ የነገረ መለኮት ትምህርት ምሁር የሆኑት የኢየሱሳዊያን ማሕበር እባል የሆኑ አባ ፔትሮ ቦቫቲ ባደረጉት አስተንትኖ እንደ ገለጹት እግዚአብሔር እያንዳንዳችንን በተናጠል እንደሚጠራን የገለጹ ሲሆን መነፍሳዊ ጥሪ “እግዚአብሔር ለእኛ የሚናገርበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው” ብለዋል ፡፡ በሕይወታችን ውስጥ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ምልክት ስለሆነ፣ የጌታን ድምጽ ለማስታወስ በተደጋጋሚ ወደ “ዳግም መወለድ” ቅጽበት መመለስ አለብን በማለት ጨምረው የገለጹ ሲሆን እርሳቸው በወቅቱ ያደረጉት አስተንትኖ ከኦሪት ዘጸሃት 3; 1-12፣ ማቴ 16 13-23; እና መዝሙር 63 ላይ ተወስደው በተነበቡ የመጸሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ያተኮረ እንደነበረ ተገልጹዋል። “እግዚአብሔር ግለሰቦች ከፍ ወዳለ የኑሮ ደረጃ ሊመራቸው ይበልጥ ለወዳጆቻቸው፣ ለእህት እና ለወንድሞቻቸው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ሁል ጊዜ በሥራ ላይ ነው” ብለዋል።

“እግዚአብሔር በድካም ጊዜያት እና ሕይወታችን ውዝግብ ውስጥ በገባችበት ወቅት እንኳን ሳይቀር እኛን ይጠራናል፣ እነዚህ እኛ ሳናውቃቸው እና ሳንገነዘባቸው ላቅ ወዳለ እግዚአብሔር ብቻ የሚገልጥ እና ሊፈጽመው ወደ የሚችል ምኞት የሚመራን መንገድ ነው ያሉት አባ ፔትሮ መንፈሳዊ ጥሪ መገለጥ እንጂ ራስን በራስ መወሰን አይደለም ብለዋል።

ሙሴ እና እግዚአብሔር በተገናኙበት ወቅት ይቃጠል በነበረው ቁጥቋጦ ዙሪያ ላይ ያደርጉት ወደ ነበረው እስተንትኖ በመመለስ እስተንትኖዋቸውን የቀጠሉት አባ ፔትሮ ሙሴ ወደ ቅዱሱ ሥፍራ እየቀረበ መሆኑን እንኳን አላወቀም ነበር ብለው እየተከሰተ ስለነበረው ነገር በራሱ መነፈሳዊ ጥሪ ትንቢታዊ የሆነ ገጽታ እንዳለው ያመለክታል ብለው “እሱ ሁል ጊዜ የእግዚአብሔር መገለጥ ነው፣ በጭራሽ እራስን የማወቅ ወይም በራስ የመወሰን ችሎታን” አያመለክትም ብለዋል።

እግዚአብሔር በስም ሲጠራው ሙሴ “እነሆኝ” ብሎ የራሱን “የግንዛቤ እና የመታዘዝ ጉዞ” በመክፈት የግል ምላሹን መስጠት እንደቻለ ጨምረው ገልጸዋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች ይህንን አሁን የያዝነውን የዐብይ ጾም ምክንያት በማደረግ በጳጳሳዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሚሽን ውስጥ የነገረ መለኮት ትምህርት ምሁር የሆኑት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑ አባ ፔትሮ ቦቫቲ መሪነት በመካሄድ ላይ በሚገኘው ሱባዔ በሶስተኛው ቀን ማለትም ማክሰኞ የካቲት 24/2012 ዓ.ም የተደረገው አስተንትኖ የእግዚአብሔርን ጸጋ መቃወም እንደማይገባ በሚገልጽ ጭብጥ ዙሪያ ላይ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ከኦሪት ዘጸሃት  5;1-23፣ ማቴ 13 1-23; እና መዝሙር 78 ላይ ተወስዶ በተነበበው የእግዚአብሔር ቃል ላይ መሰረቱን ያደረገ እንደ ነበረ ተገልጹዋል።

የሱባዔው መሪ የሆኑት አባ ፔትሮ እንደ ገለጹት እስራኤላውያንን ከባርነት ነፃ ለማውጣት በሙሴ በኩል እግዚአብሔር ለፈርሆን ያቀረበውን ጥሪ ፍርሆን አለመቀበሉን በዋቢነት የገለጹ ሲሆን በወቅቱ ፈርሆን “እግዚአብሔር ማነው?” የሚል ጥያቄ ማቅረቡን አስታውሰው የእግዚአብሔር ቃል “ሁሉንም ተቃዋሚዎች ለማጥፋት የሚችል ኋይል አለው ብለዋል።

የእስራኤል አምላክ ግን አሉ እባ ፔትሮ ቦቫቲ “የባዕዳን፣ የተጨቆኑትን እና የተጎሳቆሉ ሰዎች መብቶችን ልያበለጽግ እና በአመለካከት ላይ ለውጥ ሊያመጣ” እንደሚችል የገለጹ ሲሆን እኛ እሁን ባለንበት ዓለም ውስጥ በእብሪት በተሞላ መልኩ የእግዚአብሔር ፍላጎት፣ ጸጋውን እና መንፈስ ቅዱስን መቃወም” እየተለመደ የሚገኝ ጉዳይ ነው ብለዋል።

በዘመናችን ውስጥ የሚታየው እብሪተኝነት እግዚአብሔርን እና ነቢያቱን ለመታዘዝ አሻፈረን እንድንል ያደርገናል ያሉት እባ ፔትሮ ምንም እንኳን የሀብት፣ የባህል፣ ወይም አስገዳጅ ሀይል የመጠቀም ወጥመዶች ውስጥ የሰው ልጅ ባይገባም በራስ የመወሰን መብት፣ በግል ምርጫ እና በግል በሚወስነው ውሳኔ ምክንያት የሰው ልጅ ወደ እብሪተኛነት በመቀየር ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራሱን ላለማስገዛት በመወሰን በራሱ መንገድ ላይ ለመጓዝ ተነሳስቱዋል፣ እርሱ የሰው ልጅ የመረጠው መንገድ ደግሞ ወደ ሞት እንጂ ወደ ሕይወት የሚወስድ መንገድ አይደለም ብለዋል።

02 March 2020, 15:44