ፈልግ

የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች በአሬቻ የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች በአሬቻ  

ከእግዚአብሔር ጋር በጸሎት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ሊኖረን ይገባል!

የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት እና የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች በጋራ በመሆን በየወቅቱ እንደ አስፈላጊነቱ ሱባሄ እንደ ሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህ መሰረት አሁን የምንገኝበትን የዐብጾም ምክንያት በማድረግ ከባለፈው የካቲት 22/2012 ዓ.ም ጀምሮ በደቡብ ጣሊያን በምትገኘው አሬቻ በመባል በሚታወቀው ስፍራ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የቅርብ የሥራ ተባባሪዎች እና  የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር የበላይ የመስተዳድር አካላት የዐብይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ሱባዔ በማድረግ ላይ እንደ ሚገኙ ተገልጹዋል። የእዚህ አመታዊ ሱባዔ መሪ የሆኑት በጳጳሳዊው የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሚሽን ውስጥ የነገረ መለኮት ትምህርት ምሁር የሆኑት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑ አባ ፔትሮ ቦቫቲ እንደ ሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህ ሱባዔ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ እና ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅ ግንኙነት የነበረው ሰው መሆኑን በሚገልጽ ጭብጥ ዙሪያ ላይ ያተኮረ አንደ ነበረ ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኋ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በእዚህ ሱባዔ የመጀመሪያ ቀን ላይ አባ ፔትሮ ቦቫቲ ባደረጉት እስተንትኖ እንደ ገለጹት “ከእግዚአብሔር ጋር ምስጢራዊ የሆነ ቅዱስ ግንኙነት ያለህ ሰው ወይም የእግዚአብሔር ወዳጅ ልትሆን ትችል ይሆናል፣ ይሁን እንጂ አንድ ፍጡር ከእግዚአብሔር ፈጣሪው ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዲመሠርት የሚያደርገው ብቸኛው “ልምምድ” ጸሎት ነው ማለታቸው የተገለጸ ሲሆን አንድ የተበላሸ መንፈሳዊ መንገድ እንዴት መጠገን እንደ ሚቻል አስረድተዋል።

የዝምታ እንቅስቃሴ

አንድ ጸሎት በሚገባ ተገቢ በሆነ መልኩ ማደረግ ይቻል ዘንድ “መለኮታዊ ዱካዎችን” የሚከተል “መንገድ” ያስፈልጋል በማለት የገለጹ ሲሆን እግዚአብሔርን በሚገባ ለማወቅ እና ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ለመጠበቅ ይቻል ዘንድ ከእርሱ ጋር በእውነተኛ የጸሎት መንፈስ መገናኘት ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል። የእውነተኛ ጸሎት ብቸኛው ፍሬ የእግዚአብሔርን ፍቅር መቅመስ እንደ ሆን የገለጹት አባ ፔትሮ በእዚህ የእግዚአብሔብር ፍቅር ተመርተን  በትጋት እና በልግስና የእርሱን ፍቅር ለሌሎች ማስተላለፍ እንደ ሚገባን ገልጸዋል። በእዚህ ዓይነት መልኩ ከእግዚአብሔር ጋር ግንኙነት የማንመሰርት ከሆንን እውነተኛ መንፈሳዊ የሆነ ሕይወት ለመኖር እንቸገራለን ብለዋል።

በመጽሐፍ ቅዱስ ወስጥ የተጠቀሰው እና ሙሴ በሚቃጠለው ቁጥቋጦ ፊት ለፊት ቆሞ እግዚአብሔርን እንደ ተገናኘው ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ቀረቤታ ይበልጡኑ ለማጠናከር ሙሴ የነበረውን ዓይነት ተሞክሮ ሊኖረን ይገባል ያሉት አባ ፔትሮ ሙሴ ያመጣውን ዓይነት ተመሳሳይ መንፈሳዊ ለውጥ ለመጎናጸፍ የበኩላችንን ጥረት ማደረግ ይጠበቅብናል ብለዋል። ከእግዚአብሔር ጋር የጠበቀ ወዳጅነት ለመመሥረት አሉ አባ ፔትሮ ቦቭቲ እንደተናገሩት በሚቃጠለው ቁጥቋጦ አማካይነት ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር የመሰረተውን ግንኙነት  ለመላበስ “የእሳት ልምድ ተደጋጋሚ ሙከራ ማድረግ አስፈላጊ ነው” ያሉ ሲሆን ይህ የሚቃጠለው ቁጥቋጦ የሰው ልጅ ድክመቶች፣ ኋጢአቶች እና መከራዎች እንደ እንድ ቁጥቋጦ ለሕይወት አስፈላጊ በሆነ የኃይል ማለትም እሳት በሚቃጠሉበት ወቅት ወደ አዲስ ሕይወት እንደ ሚለወጡ ገልጸዋል።

ይህንን በምናከናውንበት ወቅት በድክመታችን የተነሳ ባጠፋነው ጥፋት ምክንያት በነፍሳችን ላይ የተቃጣውን ቅጣት ለማስወገድ በማሰብ ቅጣታችንን በተወሰነ መልኩ ተገቢ በሆነ የአምልኮ ልምምድ በማደረግ መልሰን ጸጋን ለመጎናጸፍ የምናደርገው ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ኢየሱስ ወደ ዓለም ያመጣልንን የልብ ቅንነት በእውነተኛ መንገድ ለመተግበር እና እኔ የመጣሁት በምድር ላይ እሳት ላመጣ ነው” ብሎ የተናገረውን የእርሱን ቃል የደህንንነት ምስጢር ጋር መተባበር ነው ብለዋል።

ቤተክርስቲያኗ እራሷን በመንፈሳዊነት ለማደስ ሁል ጊዜ ትናፍቃለች፣ እርሷ በእርግጠኝነት ሥነምግባራዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃዎች ብቻ በመውሰድ እነዚህ መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት አይችላም፣ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በመንፈሳዊ ሕይወት የተሞሉ ስሜቶችን እና ሰማዕታት ይፈልጋል በማለት አስተንትኖዋቸውን የቀጠሉ አባ ፔትሮ እንደ ምእመናን ያለብንን ኃላፊነት በመገንዘብ አሁን ማድረግ ያለብን ነገር በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ እንደተገለፀውን በስውር፣ በጽናትና በስምምነት፣ በጸሎት እና በትዕግስት በመጠባበቅ በጸሎት መንፈስ በመጠንከር በትዕግሥት እርሱን መጠባበቅ እንደ ሚገባ ጨመረው ገልጸዋል።

02 March 2020, 15:38