ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በሚገኘው የቅድስት ማርታ ቤት ውስጥ  

የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመዋጋት ይቻል ዘንድ በዓለም ዙሪያ የሚካሄዱ ጦርነቶች ማብቂያ ሊበጅላቸው ይገባል!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 20/2012 ዓ.ም በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ላይ ተንተርሰው አስተንትኖ ካደረጉ በኋላ እንደ ተለመደው እና ዘወትር እሁድ እለት እንደሚያደርጉት “ የእግዚአብሔር መልአክ ማርያምን ያበሰረበትን “የብስራተ ገብርኤል” ጸሎት ከደረሙ በኋላ ለዓለም ባስተላለፉት ሳምንታዊ መልእክት ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት በአሁኑ ወቅት በጣሊያን እና እንዲሁም በመላው ዓለም እየተከሰተ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክኛት የሰው ልጅ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደ ገባ የገለጹ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ዓለማችንን በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ውስጥ የከተተውን የኮሮና ቫይረስ በትኩረት መዋጋት ይችል ዘንድ በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ በዓለም ዙሪያ በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተደረጉ የሚገኙ ጦርነቶች ሁሉ ያበቁ ዘንድ ጥሪ ማቅረቡን ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ይህንን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያቀረበውን ጥሪ ሁሉም ሰው ገቢራዊ ያደርገው ዘንድ ቅዱስነታቸው ጥሪ አርበዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ይህንን ጥሪ የተቀበላችሁ እና በተግባር ላይ ያዋላችሁ ሰዎችን በሙሉ ላመሰግን እወዳለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው እናም ሁሉንም የጦርነት እና የጥላቻ ተግባራትን በማስቆም  ለሰብአዊ ዕርዳታ መስጫ መንገዶችን መፈጠር፣ ለዲፕሎማሲ ተግባራት ራሳን ማዘጋጀት እና ክፍት ማደረግ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ትኩረት መስጠት እንደ ሚገባ ቅዱስነታቸው በሳምንታዊ መልእክታቸው አክለው ገልጸዋል።

ወረርሽኙን በተመለከተ እየተደረገ የሚገኘው የጋራ ቁርጠኝነት የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናችንን ሁላችንም ግንኙነታችንን በማጠናከር በሽታውን ለመዋጋት ያለንን ፍላጎት ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ሊያደርግ ይችላል በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአገር መሪዎች እና በሌሎች ባለድርሻ አካላት መካከል የሚነሱትን ተቀናቃኞቻቸውን ለማሸነፍ የሚያደርጉትን ሩጫ ጋብ እንዲያደርጉ እንደሚረዳ ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። ግጭቶች በጦርነት አይፈቱም! ተቀናቃኞቻችንን እና ተፎካካሪዎቻችንን ማሸነፍ የምንችለው በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ብቻ ሊሆን እንደ ሚገባው ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል።

በዚህ አስቸጋሪ እና አሳሳቢ በሆነ ወቅት ተጋላጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙትን፣ በአረጋዊያን መጠሊያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን፣ እንዲሁም በማረሚያ ቤቶች ውስጥ እና ሰዎች ሰብሰብ ብሎ በሚኖሩበት ስፍራዎች ውስጥ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ በጸሎቴ ላስባቸው እፈልጋለሁ ያሉት ቅዱስነታቸው “በተለይ እኔ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ ያሉትን ሰዎች መጥቀስ እፈልጋለሁ” በጸሎቴ ከእነርሱ ጋር መሆኔን ላረጋግጥ እፈልጋለሁ ብለዋል። “የተጨናነቁ እስረኞችን ችግር በተመለከተ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን (ኦፊሴላዊ ሪፖርት) በቅርቡ ባነበብኩበት ወቅት ሁኔታው አሳዛኝ ወደ ሆነ እልቂት ሊያመራ እንደ ሚችል ተረድቻለሁ” በማለት መልእክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ለዚህ ከባድ ችግር ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እና ለወደፊቱ አደጋዎችን ለማስወገድ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ እጠይቃለሁ” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ቡራኬያቸውን ሰጥተው ሳምንታዊ መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

29 March 2020, 17:25