ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በቅድስት ማርታ ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ ሆነው አስተምህሮ በሰጡበት ወቅት ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በቫቲካን በቅድስት ማርታ ሕንጻ ውስጥ በሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ ሆነው አስተምህሮ በሰጡበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ እያንዳንዱ ሰው በሕይወት ለመኖር የሚያስፈልገውን መልካም ነገር እንዲመኝ የእግ/ር እርዳታ ያስፈልገዋል አሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዘወትር ረቡዕ እለት በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ ለሚገኙ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኚዎች በተለያዩ አርእስቶች ላይ ተንተርሰው የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደሚያደርጉ ይታወቃል። በእዚህም መሰረት ቅዱስነታቸው በመጋቢት 02/2012 ዓ.ም ያደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ እንደ ተለመደው እና ዘወትር ረቡዕ እለት እንደ ሚያደርጉት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ወይም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የስብሰባ አዳራሽ አለመከናወኑ የተገለጸ ሲሆን ቅዱስነታቸው በአሁኑ ወቅት በጣሊያን እና በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በስፋት በመስተዋል ላይ በሚገኘው የኮሮና ቫይረስ ምክንያት ይህ ቫይረስ እንዳይዛመት ሰዎች በተቻላቸው መጠን በአንድ ቦታ መሰብሰብ የለባቸውም የሚለውን የጤና ባለሙያዎች ምክር ከግምት በማስገባት እርሳቸው በሚኖሩበት የቅድስት ማርታ ቤት ከሚገኘው ቤተ መጸሐፍት ውስጥ በቪዲዮ ያስተላለፉት ሳምንታዊ አስተምህሮ እንደ ነበረ ተገልጹዋል። በእዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው በወቅቱ ያደረጉት አስተምህሮ ከእዚህ ቀደም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አምስት ላይ በተጠቀሰውና ኢየሱስ በተራራ ላይ ባደረገው ስብከት ዙሪያ ላይ ቀደም ሲል ያደርጉት ከነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረ ለመረዳት የተቻለ ሲሆን “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና” (ማቴ 5፡6) በሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ተንተርሰው ባደረጉት አስተምህሮ ማላታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በመጋቢት 02/2012 ዓ.ም ያደረጉትን የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ጌታችን ብጹዕን እንሆን ዘንድ በሰጠን አስደናቂ የደስታ መንገድ ላይ ማሰላሰላችንን እንቀጥላለን እናም “ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና” (ማቴ 5፡ 6) ወደ ተሰኘው አራተኛው የብጽዕና መንገድ እንመለከታለን።

እኛ በመንፈስ ድህነት እና በሐዘን የሚገኘውን የብጽዕና መንገድ ተመልክተናል፤ አሁን ከርሀብ እና ጥማት ጋር የተገናኘ ሌላ ዓይነት ድክመት እንመለከታለን። ረሃብ እና ጥማት መሰረታዊ የሆኑ የሰው ልጆች ፍላጎቶች ናቸው፣ በሕይወት የመኖር ያለመኖር ሕልውናን ይመለከታሉና። ይህ የግድ መሰመር አለበት ጉዳይ ነው፣ ይህ አጠቃላይ የሆነ ፍላጎት ጥያቄ አይደለም፣ ነገር ግን እንደ አመጋገብ ያሉ አስፈላጊ እና ዕለታዊ ፍላጎቶች ናቸው።

ነገር ግን ለፍትህ መራብ እና መጠማት ማለት ምን ማለት ነው? እኛ በእርግጠኝነት በቀል ስለሚፈልጉት ሰዎች እያወራን አይደለም፣ በተቃራኒው ቀደም ሲል ባየናቸው የብጽዕና መንገዶች ላይ እንደተመለከትነው ትህትናን ይመለከታል። በእርግጠኝነት ኢፍትሐዊነት የሰውን ዘር ይጎዳል፣ የሰው ልጅ በአስቸኳይ እኩልነትን፣ እውነት እና ማህበራዊ ፍትህ ይፈልጋል፣ እናስታውስ በዓለም ውስጥ በሚገኙ ሴቶች እና ወንዶች ላይ እየደረሰ የሚገኘው ክፉ ነገር ወደ እግዚአብሔር አብ ልብ ይደርሳል። በልጆቹ ሥቃይ የማይሠቃይ አባት የትኛው ነው?

ቅዱሳት መጻህፍት እግዚአብሔር ስለሚያውቀውና ስለሚጋራው የድሆች እና የተጨቆኑ ሰዎች ሥቃይ ይናገራሉ። የኦሪት ዘፀአት መጽሐፍ እንደሚናገረው የእስራኤል ልጆች ለደረሰባቸው ጭቆና ያስሙትን የግፍ ጩኸት አዳምጡዋል፣ ሐዘናቸውን ተካፍሉዋል ። የእስራኤል ሕዝቦች ያሰሙትን የስቃይ ድምጽ አዳምጦ የኦሪት ዘጸሃት መጽሐፍ እንደ ሚነግረን (3:7-10) - እግዚአብሔር ሕዝቡን ነፃ ለማውጣት ወረደ። ነገር ግን ጌታ ለእኛ የሚናገርው የፍትህ ጥማት እና ረሃብ እያንዳንዱ ሰው በልቡ ውስጥ ከሚሸከመው የሰብዓዊ ፍትህ ፍላጎት የበለጠ ጥልቅ ነው።

በተመሳሳይ “በተራራው ላይ በተደርገው ስብከት” በመቀጠል “ጽድቃችሁ ከፈሪሳውያንና ከኦሪት ሕግ መምህራን ጽድቅ ልቆ ካልተገኘ መንግሥተ ሰማይ መግባት አትችሉም” (ማቴ 5፡20) በማለት ኢየሱስ ከሰዎች መብት ወይም ከግል ፍጽምናው ስለሚበልጥ ፍትህ ተናግሯል። የእዚህ ዓይነቱ ፍትህ የሚመጣው ደግሞ ከእግዚአብሔር ነው(1 ቆሮ 1፡30)።

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከሥጋዊ ጥማት ይልቅ ጥልቅ ጥማትን እናገኛለን፣ ይህም የሕልውናችን ስር መሠረት ነው። መዝሙረ ዳዊት እንዲህ ይላል “ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ አንተን ከልብ እሻለሁ፤ ውሃ በሌለበት፣ በደረቅና በተራቈተ ምድር፣ ነፍሴ አንተን ተጠማች፤ ሥጋዬም አንተን ናፈቀች” (መዝ. 63፡2)። የቤተክርስቲያን አባቶች በሰዎች ልብ ውስጥ ስለሚኖረው ፍሬያማ ስለሚያደርግ እረፍት ይናገራሉ። ቅዱስ አውጉስጢኖስ እንዲህ ይላል “ጌታ ሆይ ፣ አንተ ለራስህ ሠራህን፣ እናም ልባችን በአንተ እረፍ እስኪያገኝ ድረስ ሰላም አያገኝም” በማለት ተናግሩዋል። ውስጣዊ ጥማት ፣ ውስጣዊ ረሃብ ፣ አለመረጋጋት አለ።

በማንኛውም ሰው ልብ ውስጥ እጅግ በጣም የተበላሸ እና ከመልካም ተግባር ሩቅ ቢሆንም፣ በጨለማ ውስጥ እና በስህተት ፍርስራሽ ውስጥ ቢገኝም እንኳ ብርሃኑን የሚናፍቅ እንድ ትንሽዬ ነገር ይገኛል፣  ሁል ጊዜ ለእውነትና መልካም ለሆኑ ነገሮች ጥማት አለ፣ ይህም ለእግዚአብሔር ያለንን ጣማት ያሳያል። ለእርሱ ያለንን ጥማት የሚያነሳሳው ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ እርሱ አቧራችንን የሚያጸዳ ሕያው የሆነ ውሃ ነው፣ እርሱም በተፈጠርንበት ወቅት ሕይወትን የሰጠ እስትንፋስ ነው።

በዚህ ምክንያት ነው ቤተክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት የእግዚአብሔርን ቃል ለማወጅ ወደ ሁሉም ሰዎች የተላከችሁ። ምንም እንኳን ባያውቁትም አስፈላጊ ለሆነው የሰው ልጅ ልብ ሊቀርብ የሚችል ትልቁ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ታላቅ ፍትህ ነው።

ለምሳሌ ያህል አንድ ወንድና አንዲት ሴት ሲጋቡ አንድ ታላቅ እና የሚያምር ነገር ለማድረግ ይፈልጋሉ፣እናም ይህንን ጥማት ልማርካት በህይወት ጎዳና ላይ የሚያደርጉትን ጉዞ ከቀጠሉ በጸጋ ድጋፍ በችግሮች መካከል ወደፊት የሚሄዱበትን መንገድ ያገኛሉ። ወጣቶችም እንኳ ሳይቀር ተርበዋል፣ እናም ይህንን ረሃብ ማጣት የለባቸውም! ለፍቅር፣ ለርህራሄ፣ በቅን ልቦና እና አንጸባራቂ በሆኑ ፈጋግታዎች ተሞለተው ይኖሩ ዘንድ እነዚህ ነገሮች በልጆች ልብ ውስጥ ተጠብቀው ይኖሩ ዘንድ መንከባከብ ያስፈልጋል!

እያንዳንዱ ሰው በጣም አስፈላጊ የሆነውን ፣ በትክክል ምን እንደሚፈልግ፣ በህይወት ለመኖር የሚያስፈልገው መልካም ነገር ምን እንደ ሆነ፣ በተመሳሳይ መልኩም በሕይወቱ ሁለተኛ ደረጃ ሊሰጣቸው የሚገባቸው ነገሮች ምን እንደ ሆኑ፣ ተረጋግቶ መኖር የሚያስችለው ነገር ምን እንደ ሆነ እዲያጣራ ተጠርቷል።

በእዚህ የተራራው ላይ ስብከት ኢየሱስ የፍትህ ረሃብ እና ጥማት እንዲኖረን ያሳስበናል፣ የማያስፍረን አንድ ጥማት አለ፣ ይህም የእግዚአብሔር ጥማት ነው፣ የእግዚአብሔር ጥማት ግቡ መልካምነቱም  ከእግዚአብሔር ልብ ጋር ይዛመዳልና፣ ፍቅር ከሆነው ከእርሱ መንፈስ ቅዱስ ጋር ይዛመዳል፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ በልባችን ውስጥ ከዘራው ዘር ጋር ይዛመዳልና፣ ቢራብም ሁል ጊዜ ርሃቡን ያረካዋል። እሱን ለማግኘት፣ እግዚአብሔርን ለማየት እና ለሌሎች መልካም ለማድረግ ያስችለን ዘንድ ትክክለኛ የሆነውን ፍላጎት የፍትህ ጥማት እንዲኖረን ጌታ ይህንን ጸጋ ይስጠን።

ይህንን ዝግጅት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!
11 March 2020, 16:21