ፈልግ

የማሊ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ። የማሊ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን ተገናኙ። 

የማሊ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር ተገናኙ።

የማሊ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ በየካቲት 05/2012 ዓ.ም በቫቲካን ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን በወቅቱ ባደረጉት ቆይታ በሃይማኖት አክራሪነት እና ሽብርተኝነት ምክንያት በሰባዊነት ላይ እየደርሰ ስለሚገኘው ቀውስ እና ይህንን ቀውስ ተከትሎ ሕዝቡ በከፍተኛ ድህነት እየተሰቃየ እንደ ሚገኝ መነጋገራቸው የተገልጸ ሲሆን ሳህል በመባል በሚታወቀው ማሊን ባካተተው ቀጣና ውስጥ የምግብ ዋስትና አለመኖር፤ ይህንን ተከትሎ በምዕራብ አፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ መጠን የሚታያወን የስደተኞ ፍልሰት፣ በተጨማሪም የሰላም ማስከበር ሁኔታን በተመለከተ መወያየታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የማሊ ሪፖብሊክ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ቡባካር ኬታ ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር ከነበራቸው ቆያት በመቀጠል የቫቲካን ዋና ጸሐፊ ከሆኑ ከካርዲናል ጴትሮ ፓሮሊን ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ቫቲካን ከሌሎች አገራት ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በዋነኝነት የሚመሩት ዋና ጸሐፊ አቡነ ፓውል ሪቻርድ ጋላገር በስፍራው ተገኝተው ውይይቱን መታደማቸውም ተገልጹዋል።

በመልካም ሁኔታ በተካሄደው ውይይት አሁን ያለው ጥሩ የሁለትዮሽ ግንኙነቶች ለማጠናከር ይበልጡኑ ሁለቱም አገራት ማለትም ቫቲካን እና ማሊ ተባብረው መስራት እንደ ሚኖርባቸው የተነጋገሩ ሲሆን የሀገሪቱ ውስጣዊ ሁኔታ በተለይም የሰብአዊ እና የደኅንነት ሁኔታን በተመለከተ በማሊ ሕዝቦች ላይ አደጋ መጋረጡን የአገሪቷ ፕቴዚዳንት የገለጹ ሲሆን የሃይማኖት አክራሪነት እና የሽብርተኝነት መስፋፋት የቀጠናው ስጋት መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።

በመቀጠልም በሳህል ቀጠና ውስጥ እየጨመረ የመጣው የምግብ ዋስትና አለመኖር ፣ የስደተኞች ፍልሰት እና በምዕራብ አፍሪካ የሰላም ጥበቃን ጨምሮ በአንዳንድ የክልል እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ንግግር እና ውይይት ካደረጉ በኋላ ውይይቱ መጠናቀቁ ተገልጹዋል።

13 February 2020, 15:35