ፈልግ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ በባንግላደሽ በሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ውስጥ፣ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ በባንግላደሽ በሚገኝ አንድ የሕክምና ማዕከል ውስጥ፣ 

ር. ሊ. ጳ ፍራንችስኮስ፣ ቅድስት ድንግል ማርያም የሕሙማንን አደራ እንድትቀበል በጸሎት ተማጸኑ።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ የካቲት 3/2012 ዓ. ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ28ኛ ጊዜ ተከብሮ የዋለውን የሕሙማን ቀን ምክንያት በማድረግ ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘንድ ባቀረቡት ጸሎታቸው የሕሙማንን አደራ እንድትቀበል፣ ፈውስንም እንድታስገኚላቸው በማለት መማጸናቸው ታውቋል።  

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የካቲት 3 ቀን ዓመታዊ የሉርድ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል በመላዋ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ዘንድ ተከብሮ የሚውልበት ዕለት መሆኑ ይታወሳል። የካቲት 3/2012 ዓ. ም. ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀን ለ28ኛ ተከብሮ መዋሉ ታውቋል። ይህንንም በማስታወስ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዛሬ ጠዋት ባስተላለፉት የቲዊተር መልዕክታቸው በየቤቱ በተለያየ በሽታ ተይዘው ለሚሰቃዩት ሕሙማን እንክብካቤን በማድረግ ላይ የሚገኙ ቤተሰቦችን እና የሕክምና ማለሞያዎችንም በጸሎታቸው አስታውሰዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ቅዱስ ማቴ. 11: 28 ላይ እንደጻፈው “እናንት ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ” የሚለውን ጠቅሰው፣ ይህም ኢየሱስ ክርስቶስ በተለያየ ችግር ውስጥ ወድቆ ለቆሰለው የሰው ልጅ በሙሉ ያሳየው የምሕረት እና የርህራሄው ጥሪ መሆኑን አስረድተዋል።

የስጋ ፈውስ ለሁሉ ሰው ሊዳረስ ይገባል፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለሕሙማን ሊደረግ የሚግባ ትክክለኛ የእንክብካቤ ዓይነትን አስመልከት በጻፉት መልዕክታቸው፣ ፈውስ እና እንክብካቤ የሚያሻቸው ሕሙማን ብቻ ሳይሆኑ ከስጋዊ ሕመም እንዲፈወሱ አስፈላጊውን የሕክምና አገልጎት በመስጠት ላይ የሚገኙት እና ዕለታዊ እንክብካቤን በማድረግ ላይ የሚገኙትን ወላጅ ቤተሰብ ከፈጣሪ የተቀበሉትን የፍቅር አገልግሎት ጥሪያቸውን በታማኝነት እንዲያበረክቱ፣ መለኮታዊ ትዕዛዝን መሠረት በማድረግ፣ ቅዱስ ለሆነው ለሰው ልጅ ነፍስ ሊሰጥ ገሚገባውን ክብር እንዳያጓድሉባቸው አደራ ብለዋል።

“ኤውታናሲያ” እና ነፍስን ከስጋ የመለየት የሕክምና ዘዴ ተቀባይነት የለውም፣

የሕክምና አገልግሎት በጥልቀት ማሰብንና ጥንቃቄን ይጠይቃል ያሉት ቅዱስነታቸው የሕክምና አገልግሎት ታካሚውን፣ የታካሚውን ቤተሰብ እና ሐኪሙንም ትልቅ ጥንቃቄን ይጠይቃል ብለው “ኤውታናሲያ”እና ነፍስን ከስጋ የመለየት የሕክምና ዘዴ ተቀባይነት የለውም ብለው ሕሙማን ከበሽታቸው የመፈወስ ዕድል የመነመነ ቢሆን እንኳ የሐኪሞች ዋና ተልዕኮ አንድ ሕሙማን ሕይወቱ እስከምታልፍ ድረስ የሚያስፈልገውን እንክብካቤ ሳያጓድሉ፣ ፍቅር በታከለበት አኳኋን እርዳታን መስጠት ነው ብለዋል።

ድሆች በቂ ሕክምናን የማግኘት መብታቸው ይከበር፣

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንችስኮስ ዛሬ ለ28ኛ ጊዜ ተከብሮ የዋለውን ዓለም አቀፍ የሕሙማን ቀን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ድሆች እና አቅመ ደካሞች በቂ የሕክምና አገልግሎትን የማግኘት መብታቸው እንዲከበርላቸው፣ ማሕበራዊ ፍትህን እንዲያረጋግጡላቸው መንግሥታትን እና ማሕበራዊ ተቋማትን አደራ ብለው በተለይም በሕክምና አሰጣጥ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ለሕሙማን ፍቅርን እና ርህራሄን በመግለጽ፣ የደጉ ሳምራዊ ምሳሌነታቸውን እንዲያሳዩ አደራ ብለዋል።

ይህን ዘገባ በድምጽ ለማዳመጥ ከዚህ ቀጥሎ የሚገኘውን “ተጫወት” የሚለውን ምልክት ይጫኑ!
11 February 2020, 16:58