ፈልግ

Pርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን ከምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ለጥናት እና ለጉብኝት ወደ ሮም  የመጡ ካህናት እና መነኩሳት ጋር Pርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቫቲካን ከምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ለጥናት እና ለጉብኝት ወደ ሮም የመጡ ካህናት እና መነኩሳት ጋር  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ “ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ለደስታ እና ለጋራ ጥቅም የሚሆናቸው የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይዘዋል” አሉ!

ከምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ተውጣተው ለጥናት እና ለጉብኝት ወደ ሮም ከተማ የመጡ ወጣት ካህናት እና መነኩሳት ጋር በየካቲት 13/2012 ዓ.ም ከርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጋር በቫቲካን መገናኘታቸው ተገልጹዋል። በግንኙነቱ ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ ባደረጉት ንግግር እንደ ግለጹት “ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ለደስታ እና ለጋራ ጥቅም የሚሆናቸው የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይዘዋል” ማለታቸው ተገልጹዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅቶቻችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየካቲት 13/2012 ዓ.ም በቫቲካን ከምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ተውጣተው ለጥናት እና ለጉብኝት ወደ ሮም ከተማ የመጡ ወጣት ካህናት እና መነኩሳት ጋር በተገናኙበት ወቅት ያደረጉትን ንግግር ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው አሰናድተነዋል ተከታተሉን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ!

“ከእግዚአብሔር አብ፣ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስም ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን” (2ቆሮ 1፡2)። እነዚህን የሐዋሪያው ጳውሎስ ቃላት ተጠቅሜ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ሞቅ ያለ ሰላምታዬን እያቀረብኩኝ የእናተ ጉብኝት ያሳደረብኝን ደስታ ከእናተ ጋር ለመካፈል እወዳለሁ። ከእናተ ጋር ሁነው እዚህ የተገኙትን ሊቀ ጳጳስ በርሳማኒ እና ጳጳስ ኤል-ሶሪያን ከልብ በመነጨ መልኩ ለእነርሱም ሰላምታዬን አቀርባለሁ። በአናንተ በኩል ለተከበሩ እና ውድ ወንድሞቼ ለሆኑት የምስራቃዊ ኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናት ሃላፊዎች ልዩ ሰላምታዬ እንዲደርሳቸው እፈልጋለሁ።

እያንዳንዱ ጉብኝት ያሉንን ስጦታዎቻችንን እንድንጋራ ያደርጋል። የእግዚአብሔር እናት ኤልሳቤጥን ጎበኘቻት፣ የተቀበለችሁን እግዚአብሔርን ስጦታ ለእርሷም አጋራቻት። ማርያም ሰላምታ ባቀረበችላት ወቅት በማህፀኗ ውስጥ ያለው ጽንስ በደስታ ዘለለ፣ እርሷም በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተሞልታ የአጎቷን ልጅ ባረከች (ሉቃ 1 39-42)። እንደ ማርያምና ኤልሳቤጥ ሁሉ አብያተ ክርስቲያናት ለደስታ እና ለጋራ ጥቅም የሚሆናቸው የተለያዩ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይዘዋል። እኛ ክርስቲያኖች እርስ በራሳችን ስንጠያየቅ እና በጌታ ፍቅር አንዳችን ሌላውን ስንገናኝ እነዚህን ስጦታዎች መለዋወጥ በመቻላችን ተባርከናል። መንፈስ ቅዱስ በሌሎች ውስጥ የዘራውን እንደራሳችን ስጦታ አድርገን መቀበል እንችላለን። ስለዚህ የእናተ ጉብኝት ስለካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ያላችሁን እውቀት ለማሳደግ እድል የሚሰጣችሁ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እኛም ካቶሊኮች እናንተ የምታመጡልንን የመንፈስን ቅዱስ ስጦታ የማግኘት ዕድል ይሰጠናል። እዚህ መገኘታችሁ ይህንን ስጦታ እንድንጋራ እድሉን ይሰጠናል እናም የደስታ ምንጭ ይሆናል።

ሐዋሪያው ጳውሎስ “በክርስቶስ ኢየሱስ ስለ ተሰጣችሁ ጸጋ ዘወትር ስለ እናንተ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” (1 ቆሮ 1፡4) በማለት ይናገራል። እኔም በተመሳሳይ መልኩ ዛሬ በተሰጠን የእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት አመሰግናለሁ። ለተሰጠን ጸጋ እውቅና መስጠት፣ ቸር ለሆነው ለእግዚአብሔር ሥራ እውቅና መስጠት፣ በውስጣችን ያለው የመልካም ነገር ምንጭ እርሱ እንደ ሆነ ማመን፣ ሁሉም ነገር የሚጀምረው ከእዚህ ነው። ይህ የክርስትና የሕይወት እይታ ውበት ነው። ሐዋሪያው እንዳስተማረው ወንድሞቻችንን የመቀብያው ተገቢ የሆነው መንገድ ይህ ነው። ስለዚህ በህይወታችሁ ለተቀበላችሁት ጸጋዎች እና ቱፊቶች፣ ለክህነት እና ለምንኩስና ሕይወታችሁ “እነሆኝ” በማለት አዎንታዊ ምላሽ በመስጠታችሁ እና ለምስራቃዊ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ምስክርነት በመስጠታችሁ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። እናተ ብዙን ጊዜ በአሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ፣ በአመፅ እና በጦርነት በተሰቃዩ አካባቢዎች እንኳን ሳይቀር እምነታችሁን በክርስቶስ ደም ያተማችሁ፣ የእምነት እና የተስፋን ዘር መዝራታችሁን የቀጠላችሁ አብያተ ክርስቲያናት ናችው።

ሁለችሁም በቆይታቸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና የሮሜ ከተማ ጥሩ ተሞክሮ እንደ ነበራችሁና እንደ እንግዳ ሳይሆን በወንድሞች መኋል የምትገኙ ወንድሞች ሆናችሁ እንደ ተሰማችሁ እና ጥሩ ተሞክሮ እንደ ነበራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። በመካከላችን ባለው የወንድማማችነት ፍቅር ጌታ ደስ ይለዋል። በእናተ ጉብኝት  እና በእግዚአብሄር እገዛ ለወደፊቱ የእናተን መሰመር በመከተ ለመጎብኘት የሚመጡ ወንድሞች የደስታ ምንጭ ሆኖ ለጌታ ክብር እንዲጡ የሚያደርጋቸው ይሆን። የእናተ እዚህ መገኘት ትንሽዬ የሆነ አጋጣሚ የሚመስል ቢሆንም ኢየሱስ በጥልቅ የሚመኘውን ሙሉ ኅብረት ለማምጣት የሚችል ፍሬያማ ዘር ይሁን (ዮሐ. 17፡ 21)።

ውድ ወንድሞች ስለጎበኛችሁን በድጋሚ እያመስገንኩኝ በጸሎቴ እንደ ማስባችሁ ቃል እገባለሁኝ። ለእኔ እና ለተሰጠኝ ተልዕኮዬ ጽሎት እንደ ምታደርጉልኝም እተማመናለሁ። ጌታ ይባርካችሁ፣ የእግዚአብሔር እናት ትጠብቃችሁ። እናም አሁን እያንዳንዳችን በገዛ ቋንቋችን “አባታችን ሆይ”! የሚለውን ጸሎት አብረን እንጸልይ።

21 February 2020, 16:00