ፈልግ

ቅዱስነታቸው በጳውሎስ ስድስተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሻ የተገኙትን አዳጊ ሕጻናት ሲባርኩ፣ ቅዱስነታቸው በጳውሎስ ስድስተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሻ የተገኙትን አዳጊ ሕጻናት ሲባርኩ፣ 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ፣ “የምንኩስና ሕይወት ጥሪ እንዲያብብ እንጸልይ”።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራችስኮስ ጥር 20/2012 ዓ. ም. በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ የመሰብሰቢያ አዳራሻ ተገኝተው፣ በሥፍራው ለተገኙት በርካታ ምዕመናን፣ መንፈሳዊ ነጋዲያን እና የአገር ጎብኝዎች ሳምንታዊ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ካቀረቡ በኋላ ለእንግዶቹ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታቸውን አቅርበውላቸዋል። ቅዱስነታቸው ያለፈው እሁድ በፖላንድ አገር ተከብሮ የዋለውን የምንኩስና ሕይወት ቀን በማስታወስ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ገዳማዊያን እና ገዳማዊያት በክርስቶስ ኢየሱስ ስም ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው የሆኑትን ለማገልገል ብለው የጀመሩት ሕይወት በየዕለቱ በታማኝነት እና በትጋት ይኖሩ ዘንድ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን ፍቅሩን በታማኝነት መመስከር የሚችሉበትን ኃይል እና ብርታት እንዲያገኙ በጸሎታችን እናግዛቸው ብለው፣ ይህን የተቀደሰ ጎዳና የሚከተሉ የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እግዚአብሔር እንዲያበዛልን በጸሎት እንጠይቅ በማለት ሳምንታዊ የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮአቸውን ደምድመዋል።

29 January 2020, 17:27